ethiopian news

Artcles

ግልፀኝነት የነገሰበት አሰራር እየጎለበተ ነው!

By Admin

September 01, 2017

ግልፀኝነት የነገሰበት አሰራር እየጎለበተ ነው!

                                                        ደስታ ኃይሉ

መንግስት የህግ የበላይነትን መቼም ቢሆን ለድርድር የማያቀርብ መሆኑን የኋላ ታሪኩ ያስረዳል። የትኛውም አካል የመንግስት የስራ ኃላፊም ሆነ ሌላ ተጨባጭ ማስረጃ እስከተገኘበት ድረስ ከተጠያቂነት ሊድን አይችልም።

ይህ አሰራር የነበረና ወደፊትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው። በአሰራሩም እንደ ማንኛውም ዴሞክራሲያዊ አገር ግለፀኝነት የነገሰበትን ሁኔታን እያሰፈነ ነው። ይህ አሰራርም በህዝቡ የነቃ የሳትፎ አሁን ካለው እመርታ ይበልጥ ጎልብቶ የህግ የበላይነትን ማረጋገጡ አይቀርም።

በኢፈፌዴሪ ህገ መንግስት ላይ ማናቸውም የመንግስት ስራዎች ግልፀኝነትን ማዕከል አድርገው መከናወን እንዳለባቸው ተደንግጓል። ህገ መንግስቱ የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅ ሲል ከህግ አግባብ ውጪ ስልጣን መያዝ የተከለከለ መሆኑን ደንግጓል። ይህም የህገ መንግስቱን አንቀፅ 56 ላይ ተገልጿል። በዚህ አንቀፅ መሰረት በምክር ቤተ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጣምራ ድርጅት የፌዴራሉን መንግስት የህግ አስፈፃሚ አካል እንደሚያደራጁና እንደሚመሩ ተገልጿል።

ይህም የትኛውም አካል ህገ መንግስቱ ላይ ከተደነገገው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ውጪ ነፍጥ አንግቦ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመጣል የሚያደርጋቸው ማናቸውም ተግባራት ህገ ወጥ መሆኑን ያሳያል። በመሆኑም ከህገ መንግስቱ አኳያ በዚህ ተግባር ላይ የተሰለፉ ማናቸውም የፖለቲካ አሊያም የሽብር ድርጅቶች ህገ ወጥ ናቸው።

ከእነርሱም ጋር የሚደረግ ማናቸውም ግንኙነት ወይም የእነርሱን አጀንዳ በማራመድ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ የሚደረጉ ጥረቶች የህግ የበላይነትን መፃረር እንደሆነ ግንዛቤ ሊያዝ የሚገባ ይመስለኛል። ምክንያቱም እነዚህ ሃይሎች ከህግ የበላይነት ጋር ሆድና ጀርባ በመሆናቸው ነው።

ለምሳሌ ያህል አንድ ሰው በሀገራችን የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ውስጥ በአሸባሪነት የተሰየሙትን ኦነግንና ግንቦት ሰባት የመሳሰሉ የሽብር ቡድኖችን ከደገፈ ወይም የእነርሱን ዓላማ ለማሳካት በተለያዩ መንገዶች ከተንቀሳቀሰ ከህግ የበላይነት ጋር እየተጋጨ መሆኑን ግንዛቤ ሊይዝ ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ የሽብር ቡድኖች ህገ መንግስቱን ተፃርረው ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ እየተንቀሳቀሱ በመሆናቸው ነው። እናም እነርሱን አለመደገፍ የህግ የበላይነትን ማክበር ሲሆን፣ የእነርሱን ህገ ወጥ ዓላማ በማናቸውም መንገድ መደገፍ ደግሞ የህግ የበላይነትን መፃረር መሆኑን መረዳት ይገባል።

የህግ የበላይነት መከበር ለሀገር ሰላምና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማሳለጥ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል። የህግ የበላይነት ከሌለ ሰላም የሚባልን ነገር ማሰብ አይቻልም። ሰላም ከጠፋ ደግሞ ስለ ልማትና ዴሞክራሲ ማሰብ አይቻልም። ፀረ-ልማትዊነትና ፀረ-ዴሞክራሲያዊነት ቦታውን ይረከባሉ። ይህ ሁኔታ ደግሞ እንደ እኛ ሰላምን፣ ልማትንና ዴሞክራሲን የህልውናው ጉዳይ ላደረገ ሀገር አሜኬላ እሾህ መሆኑ አያጠያይቅም።

ኢትዮጵያ የጀመረችው የዕድገትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ባህል ግንባታ ሂደት ስኬታማ ሆኖ እንዲቀጥል፤ አስተማማኝ ሰላም የሰፈነበት ምህዳርን መፍጠር የግድ ነው። ምክንያቱም ሀገራችን ፈጣን ልማትን ማምጣትና ከተመፅዋችነት መላቀቅ ብሎም ዴሞክራሲን መገንባት የሞት ሽረት ያህል የህልውና ጉዳይ አድርጋ ስለያዘችው ነው። ሰላምን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ለብሔራዊ ደህንነቷ ስጋት የሆኑ እንቅስቃሴዎችን መከላከልና መቆጣጠር ያስችላት ዘንድ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ የሚኖርባት ይመስለኛል።

ሰላም በህግ የበላይነት የምናተርፈው ትሩፋት ነው። በሰላም ውስጥ የምናስባቸውን የልማትና የዴሞክራሲ ስራዎችን ዕውን እናደርጋለን። ህጎች ለአንዱ የሚሰሩ ለሌላው ደግሞ የማይሰሩ ለሆኑ አይችሉም። ሁላችንም በህግ ፊት እኩል እንስተናገዳለን። የህግ የበላይነት ሲኖር ሁላችንም ከሚገኘው ሀገራዊ ጥቅም ተካፋዩች እንሆናለን።

ፌዴራላዊ ስርዓቱ የህግ የበላይነትን በሚገባ የሚያስከብር ነው። የህግ የበላይነትን ተላልፎ የሚገኝ ማንኛውም ዜጋ ተጠያቂ ይሆናል። ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል እንደመሆኑ መጠን፤ በመረጃና በማስረጃ በተረጋገጠበት ጥፋት ልክ ተጠያቂ ይሆናል። ይህ በማንም ላይ የሚሰራ ተግባር ነው።

አንዱን ዜጋ ከሌላው በማበላለጥ የሚከናወን የህግ አሰራር በፌዴራላዊ ስርዓቱ ውስጥ ፈፅሞ ሊኖር አይችልም፤ መቼም ቢሆን። እናም የህግ የበላይነትን ኢትዮጵያ ውስጥ ማስከበር ማለት የህገ መንግስቱን መንፈስ በሁሉም መስኮች ማስፈፀም ማለት መሆኑን የትኛውም ዜጋ ግንዛቤ መያዝ ያለበት ይመስለኛል። ይህም የህገ መንግስቱን የግልፀኝነት አሰራር የሚደግፍ ነው።

የህግ የበላይነትን አለማረጋገጥ ህገ መንግስቱን መፃረር ነው። ምክንያቱም ህገ መንግሰቱ የህጎች ሁሉ የበላይ እንደመሆኑ መጠን፤ እርሱን ተከትለው የሚወጡ አዋጆችን ተፈፃሚ አለማድረግ መልሶ ህገ መንግስቱን መቃወም ነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ አስፈፃሚውም አካል ሆነ ማንኛውም ዜጋ መፍቀድ ያለበት አይመስለኝም።

የህግ የበላይነትን መፃረር ስርዓት አልበኝነትን የሚፈጥር ከመሆኑም ባሻገር፤ ህጎች ለሁሉም ዜጎች እኩል እንዳይሰሩ ያደርጋል። እናም ‘ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል ነው’ የሚለውን ህገ መንግስታዊ መርህ ገቢራዊ ለማድረግ የህግ የበላይነት በማያሻማ ሁኔታ መረጋገጥ ይኖርበታል። ይህ ሲሆንም ግልፀኝነት ይጎለብታል።

የህግ የበላይነት መከበር ለአገር ሰላምና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማሳለጥ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል። ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት የህግ የበላይነት ከሌለ ሰላም የሚባልን ነገር ማሰብ አይቻልም። ሰላም ከጠፋ ደግሞ ስለ ልማትና ዴሞክራሲ ማሰብ አይቻልም። የዴሞክራሲ አንድ ዘውግ የሆነው ግልፀኝነትም በቦታው ላይ አይገኝም።

ፀረ-ልማትዊነትና ፀረ-ዴሞክራሲያዊነት ቦታውን ይረከባሉ። ይህ ሁኔታ ደግሞ እንደ እኛ ሰላምን፣ ልማትንና ዴሞክራሲን የህልውናው ጉዳይ ላደረገ ሀገር አሜኬላ እሾህ መሆኑ አያጠያይቅም።

እርግጥ ኢትዮጵያ የጀመረችው የዕድገትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ባህል ግንባታ ሂደት ስኬታማ ሆኖ እንዲቀጥል፤ አስተማማኝ ሠላም የሰፈነበት ምህዳርን መፍጠር የግድ ነው። ምክንያቱም ሀገራችን ፈጣን ልማትን ማምጣትና ከተመፅዋችነት መላቀቅ ብሎም ዴሞክራሲን መገንባት የሞት ሽረት ያህል የህልውና ጉዳይ አድርጋ ስለያዘችው ነው።

ታዲያ ሰላምን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ለብሔራዊ ደህንነቷ ስጋት የሆኑ እንቅስቃሴዎችን መከላከልና መቆጣጠር ያስችላት ዘንድ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ አለባት። በዚህ መሰረትም ባለፉት ዓመታት የህግ የበላይነት በሁሉም መስኮች ተግባራዊ ሆነዋል። ዴሞክራሲውም ጎልብቷል። የግልፀኝነትና የተጠያቂነት አሰራርም እየተተገበረ ነው። እነዚህን ጉዳዩች አቅቦ መጓዝ ዴሞክራሲውን ያለመልማል። ስርዓቱ በፅኑ መሰረት ላይ ቆሞ በህዝቦች እጅግ የላቀ አመኔታ ይኖረዋል። በጥቅሉ የግልፀኝነት ማበብ የአመኔታ በር ነው ማለት ይቻላል። ስለሆነም ለግልፀኝነት አሰራር ይበልጥ እውን መሆን ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ!