Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ህወሓት የክልሉን ሕዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገለፀ

0 530

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ የክልሉን ሕዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገለፀ፡፡

ድርጅቱ ከመስከረም 22 እስከ 28/2010 ሲያካሄድ የቆየውን የማዕከላዊ ኮሚቴ ጉባኤ አጠናቋል፡፡

በጉባኤው የ2ዐዐ9 የድርጅትና የመንግሥት ሥራዎችና የተጀመሩ የጥልቅ ተሀድሶ ሂደቶች አፈፃፀምን ገምግሟል፡፡

ጉባኤው በጥልቅ ተሀድሶ የተለዩትን የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መርምሯል፡፡

“”እየታደስን እንሰራለን እየሰራን እንታደሳለን”” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ ጉባኤ በመርህ ላይ የተመሠረተ አንድነት በማጠናከር የክልሉ ሕዝብ ጥያቄዎችን በቁርጠኝነት ለመመለስ እንደሚሰራም ነው የተገለፀው፡፡

በትግራይና በአማራ ክልሎች መካከል ከግጨው ጋር በተያያዘ የወሰን መካለል ጉዳይ በጊዜው ሳይፈታ መቆየቱ ችግር ማስከተሉን ገምግሞ፣በአሁኑ ጊዜ በሁለቱም ድርጅቶችና ሕዝቦች ትብብር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታቱን መግለጫው ጠቅሷል፡፡

ጠባቦችና የትምክህት ኃይሎች የተለያየ ስልት በመጠቀም የፌዴራል ሥርዓቱን ለማፍረስ የሚያደርጉት እንቅስቃሴንም ትኩረት ሰጥቶ ተመልክቶታል፡፡

በቅርቡ የኦሮሚያና የኢትዮጵያ ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ምክንያት በደረሰው የሕይወትና ንብረት ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡

ፓርቲው ችግሩን መርህን ማዕከል ባደረገ መልኩ መፍትሔ እንዲያገኝ ከድርጅቶች ጎን በመሆን እንደሚሰራ ገልጿል፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴው የሴቶችን፣ ወጣቶችን እንዲሁም ምሁራን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትጋት እንደሚሰራም በመግለጫው ጠቅሷል፡፡

የተጀመረውን የሕዳሴ ጉዞ ከዳር ለማድረስ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮችና ፈተናዎችን በፅናት ለመታገል ቆርጦ እንደተነሳም በኢቢሲ በላከው መግለጫ  አስታውቋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy