Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሕዝቦችን የሚያስተሳስር በዓል

0 503

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሕዝቦችን የሚያስተሳስር በዓል

                                                                ደስታ ኃይሉ

የኢሬቻ በዓል መሰረተ የኦሮሞ ህዝብ ነው። በዓሉ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት፣ ባህሉ በሚያዘው መሰረት በአባ ገዳዎች የሚመራ ታላቅ አከባበር ያለው ስርዓት ነው። በዓለም ከማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ሆኖ የተመዘገበው የገዳ ስርዓት አንድ አካልም ነው። የኢሬቻ በዓል መሰረቱ የኦሮሞ ህዝብ ይሁን እንጂ ሌሎቹን የኢትዮጵያ ሕዝቦች በጋራ የሚያስተሳስር የቱሪዝም መስህብ ጭምር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። ይህም በዓሉ ለህዝብ ጥቅም ህዝቦችን የሚያስተሳስር ነው። ምክንያቱም የአገራችን ህዝቦች ባህልና ወግ የሁሉም ሀዝቦች ባህልና ወግ ድምር ውጤት ስለሆነ ነው።

ይህ የሰላም በዓል ማንኛውም የኦሮሞ ተወላጅ በላቀ ሁኔታ አምላኩን ያመሰግንበታል። አምላኩ ለስህተት፣ ለደባ፣ ለተንኮልና ለውሸት ትዕግስት የሌለው መሆኑን ያስባል። አምላክ በሰማይና በምድር ያለውን ማናቸውንም ነገር ፈጥሮ የሰው ልጅ እንዲጠቀምበትና እንዲያዝበት ስልጣን ስለሰጠው፤ ለዚህ ሁሉ የማይነጥፍ አምላካዊ ስጦታውና ለተደረገለት ሁሉ የኦሮሞ ህዝብ ምስጋና የሚያቀርብበት ቀን ነው። ስሙንም እየጠራ ‘እንኳን ከክረምት ወደ ፀደይ በሰላም አደረስከን’ እያለ ተአምራቱን ከፍ የሚያደርግበትም ታላቅ ዕለት ነው።

በዓሉ በሁሉም የኦሮሞ ተወላጅ ልብ ውስጥ ሰፊ ስፍራ አለው። ከክረምት ወደ ፀደይ በሚደረገው ሽግግር፤ ክረምት በፀደይ ተተክቷልና ደስታ ይገለፃል። የክረምቱ የጨለማ ጉም ተገፎ በብርሃን ተተክቷልና ደማቅ ብርሃን ይታያል። የፀደይ ፀሐይ ያለ ምንም ስስት በሙሉ አቅሟ ልግስናዋን ስለምትቸር ህይወት የደመቀች ትሆናለች።

አገራችን በዩኔስኮ ያስመዘገበችው የገዳ ስርዓት የዴሞክራሲ መሰረትና ሁነኛ ማሳያ ነው። ረጅም ታሪክ ያለው የኦሮሞ ህዝብ የስልጣን መሸጋገሪያ ስርዓትም ነው። የገዳ ስርዓት እንደ ማንኛውም ዘመናዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት፤ የገዳ ስርዓትም ህግ አውጪ፣ ህግ አስፈፃሚና ህግ ተርጓሚ አካላት አሉት።

በዚህ የስልጣን ክፍፍል መሰረትም ስርዓቱ ህዝቡን በባህላዊ መንገድ ያስተዳድራል። በስልጣን ክፍፍሉ ቦታ ውስጥ አባገዳዎች ቀዳሚውን ስፍራ ይወስዳሉ። የላይኛው የስልጣን እርከን የአባገዳው ነው። እናም በየስምንት ዓመቱ አንዴ የሚመረጠው አባገዳ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ መናቻውን ተግዳሮቶችን ይፈታል፤ የሚፈቱበትን መንገዶችንም ያመላክታል።

በስርዓቱ ውስጥ የቤተሰብ፣ የጎረቤት፣ የአካባቢ ወይም የደን ጥበቃ እንዲሁም የግጭት አፈታት ስርዓት እስከ አሁን የተረጋገጡና እየተሰራባቸው የመጡ ህግጋት ናቸው። የዚህ ስርዓት ዋነኛ ተዋናይ የሆኑት አባገዳ በህብረተሰቡ ውስጥ ተሰሚነት ያላቸውና ክብር የሚቸራቸው ናቸው።

ህብረተሰቡ እርሳቸው ያሉትን ነገር በባህሉና በደንቡ መሰረት ይፈፅማል። በአጭር አነጋገር አባገዳው የኦሮሞ ህዝብ ዘውግ ናቸው ማለት ይቻላል። ሁሉም የኦሮሞ ተወላጅ አክብሮትን በመቸር ለአባገዳው ውሳኔ ተገዥ ይሆናል። ፅንፈኛው ሃይል ግን ይህን ተፃርሮ በመቆም አባገዳዎችን የሚቀበል አለመሆኑን በገሃድ አሳይቷል።

በቅርቡ በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሃይቅ ላይ በተካሄደው የኢሬቻ በዓል ታዳሚው በዓሉን በሰላም በማክበር ለፅንፈኞች ቦታ እንደማይሰጥ አሳይቷል። ምክንያቱም እነዚህ ፅንፈኛ ኃይሎች ዛሬ ኢሬቻን በመበጥበጥ የንፁሃን ዜጎች ህይወት እንዲቀጠፍ ካደረጉ፣ ነገ ደግሞ እያንዳንዱ የኦሮሞ ተወላጅ በግልም ይሁን በቡድን የሚያምንበትን እምነት ተፃርሮ እንዲቆምና እርስ በእርሱ እንዲናከስ ከማድረግ እንደማይመለሱ ስላመነ ነው። ይህም የፅንፈኞች ልብና አመለካከት ከኦሮሞ ህዝብ ጋር አለመሆኑን የሚያሳይ ይመስለኛል።

ፅንፈኞቹ እሳቤያቸው ‘ገንዘብ እስካስገኘ ድረስ ማንኛውም የሁከት መንገድ ትክክል ነው’ የሚል በመሆኑም ባህላዊም ይሁን ሃይማኖታዊ ቀኖናዎችን ለመጋፋት አስበው አልተሳካላቸውም። እናም በዕለቱ የበዓሉ ታዳሚ ለአምላኩ ‘እንኳን በሰላም አደረስከኝ’ ብሎ በነቂስ ሲወጣ ሰላሙን እንዲነሱት አልፈቀደላቸውም። በዚህም ባዶ እጃቸውን አጨብጭበው ቀርተዋል።

በእኔ እምነት የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት የዴሞክራሲ መሰረትና ሁነኛ ማሳያ ነው። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ይህ ስርዓት በ1424 ዓ.ም መጀመሩ ይነገርለታል። እንደ ማንኛውም ዘመናዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት፤ የገዳ ስርዓትም ህግ አውጪ፣ ህግ አስፈፃሚና ህግ ተርጓሚ አካላት አሉት። በዚህ የስልጣን ክፍፍል መሰረትም ስርዓቱ ህዝቡን በባህላዊ መንገድ ያስተዳድራል።

በስልጣን ክፍፍሉ ቦታ ውስጥ አባገዳዎች ቀዳሚውን ስፍራ ይወስዳሉ። የላይኛው የስልጣን እርከን የአባገዳው ነው። እናም በየስምንት ዓመቱ አንዴ የሚመረጠው አባገዳ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ መናቻውን ተግዳሮቶችን ይፈታል፤ የሚፈቱበትን መንገዶችንም ያመላክታል።

በስርዓቱ ውስጥ የቤተሰብ፣ የጎረቤት፣ የአካባቢ ወይም የደን ጥበቃ እንዲሁም የግጭት አፈታት ስርዓት እስከ አሁን የተረጋገጡና እየተሰራባቸው የመጡ ህግጋት ናቸው። የዚህ ስርዓት ዋነኛ ተዋናይ የሆኑት አባገዳ በህብረተሰቡ ውስጥ ተሰሚነት ያላቸውና ክብር የሚቸራቸው ናቸው።

ህብረተሰቡ እርሳቸው ያሉትን በባህሉና በደንቡ መሰረት ይፈፅማል። በአጭር አነጋገር አባገዳው የኦሮሞ ህዝብ ዘውግ ናቸው ማለት ይቻላል። ሁሉም የኦሮሞ ተወላጅ አክብሮትን በመቸር ለአባገዳው ውሳኔ ተገዥ ይሆናል።

አባገዳዎች ከስድስት በላይ ለሚሆኑ ክፍለ-ዘመናት የኦሮሞን ህዝብ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ችግሩን ሲፈቱለት የመጡ እንደመሆናቸው መጠን፤ ችግሮች ካሉም መፍትሔ ሊሆኑ የሚችሉት እነርሱ ናቸው።

የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር ሆኖ በከፈለው መስዕዋትነት ያመጣውንና ላለፉት 26 ዓመታት ባህሉን፣ ወጉንና እምነቱን ያለ አንዳች ከልካይ እንዲከውን ያደረገውን ፌዴራላዊ ስርዓትን የሚከተል ነው።

ይህ ህዝብ የዘመናት ታሪኩና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገለጫው የሆነውን ዋርካ ከባንዴራው ላይ ነቅሎ በማውጣት የህዝቡን ታሪክና የአስተዳደር ስርዓት ያለው ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲን የሚያከብር ነው።

የኦሮሞ ህዝብ ዘመን የዘለቀውና ኢሬቻ ጭምር የሚከበርበትና የገዳው ስርዓት መገለጫ የሆነው ዋርካ ያለው ነው። ሁሌም ኦሮሞዎች ባሉበት ቦታ ሁሉ አብሮ ይኖራል። የኦሮሞ ህዝብ እስካለ ድረስ ኢሬቻን አለመለየት አይቻልም። ይህ በዓል ህዝቦችን በጋራ የሚያስተሳስር በመሆኑ የመላው ኢትዮጵያ ባህል ጭምር ነው።

በአጠቃላይ የኢሬቻ በዓል መሰረቱ የኦሮሞ ህዝብ ቢሆንም በድምር ሲታይ ሁሉንም የአገራችንን ህዝቦች የሚያስተሳስር እንዲሁም የአገራችን መገለጫ ነው። የውጭ ዜጎች በዓሉን ሲያስቡ መላው ኢትዮጵያን እያሰቡ ነው። ኢሬቻ የህዝቦች መተሳሰሪያ ሰንሰለት በመሆኑ ወደፊትም ህዝቦችን ይበልጥ ያስተሳስራል።  

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy