Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

መንግስትና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን የማጎልበት ጥረቱ

0 501

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

መንግስትና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን የማጎልበት ጥረቱ

                                                          ቶሎሳ ኡርጌሳ

የኢፌዴሪ መንግስት የአገራችንን የዴሞክራሲ ስርዓት ለማጎልበት በርካታ ጥረቶች አድርጓል፡፡ እነዚህ ጥረቶች የአገራችን ህዝቦች የሞት ሽረት ጉዳይ ነው፡፡ ህዝቦች በራሳቸው ይሁንታ ያጸደቁት ህገ መንግስት በግልፅ እንደተደነገገውም ስልጣን በሕዝብ ድምፅ እንጂ በሌላ መንገድ የሚገኝ እንዳልሆነ ተደንግጓል፡፡

በዚህም የፖለቲካ ፖርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ይህን ዕውነታ ተረድተው የዴሞክራሲን ምንነት በውል ተረድተው በምርጫ በመሳተፍ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደቱ የነበራቸው ድርሻ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡

ዳሩ ግን እዚህ ላይ ሳይጠቀስ የማይታለፈው ዋነኛ ጉዳይ፤ የሀገራችን የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ 26 ዓመት ብቻ የስቆጠረ ለጋ በመሆኑ፣ የዴሞክራሲያዊ ባህል ግንባታ ሂደቱ ስር እንዲሰድና እንከን አልባ ርብርብ ተደርጓል ማለት አይቻልም፡፡ ሆኖም መሰረታዊ የዴሞክራሲ ተግባራትን በማከናወንና ዴሞክራሲው እንዲጎለብት ረጅም ርቀት መጓዝ ተችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፋት ዓመታት የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ስርዓትን በሂደት በመገንባት ድህነትን ለማሸነፍ ባደረግነው ርብርብ አንፀባራቂ ሊባል የሚችል ውጤት ተገኝቷል፡፡ ሆኖም ልዩነታችን አንድነታችን ሆኖ ካልቀጠለ፤ በመነቋቆርና በመነካከስ ከቀጠልን እንደዚህ ቀደሙ ለዘመናት ወደ መጣንበት የድህነት አረንቋላ መዘፈቃችን አይቀርም፡፡ እናም ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ ወሳኝ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡

እርግጥ የሀገራችን የህዳሴ ጉዞ ሊረጋገጥ የሚችለው በመጎልበት ላይ የሚገኘው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ባህል ግንባታችን ያለ አንዳች እንቅፋት ሳይሸራረፍ ሲቀጥል ነው፡፡ እናም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታችን መጠናከርና ማበብ ጤናማ እና ገንቢ ሚና የሚጫወቱ የፖለቲካ ፖርቲዎች መኖር አለባቸው፡፡

መንግስት በአገሪቱ ዴሞክራሲን የሚያጠናክሩ ፖርቲዎች መኖር እንዳለባቸው ያምናል፡፡ ተደጋግሞ እንደሚነገረውም የመንግስት ፍላጐት የሀገራችን የመድብለ ፖርቲ ስርዓት ዳብሮ እና ጐልብቶ ማየት የዘወትር ፍላጐቱ መሆኑ ነው፡፡ ሁሉንም የሀገራችንን ህዝቦች የሚወክሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድምፃቸው እንዲሰማ ጥረት እያደረገ ነው፡፡

የሀገራችን የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ባህል ግንባታ ጤናማነቱ ተጠብቆ ሊጓዝ የሚችለው ጤናማ እና ገንቢ ሚና የሚጫወቱ የፖለቲካ ፖርቲዎች ተሳትፎ እየጐለበተ ሲመጣ ነው፡፡ በመሆኑም በተለይም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ራሳቸውን በማብቃትና ከጅምላዊ አካሄድ በመታቀብ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ማበብ ሀገራዊ ግዴታ ያለባቸው ይመስለኛል፡፡

በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ህዝቡ እንዲያስተዳድሩት የሚፈልጋቸውን ይመርጣል እንጂ፣ እንዳለፉት ስርዓቶች የሚያስተዳድሩት ራሳቸውን መርጠው አሊያም በገዥ ፓርቲ ተመርጠው የሚሄዱበት አሰራር ዶሴው ተዘግቷል።

አንዳንድ ‘በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን’ የሚሉ ተቃዋሚዎች ግን ይህን የተዘጋ ዶሴ ከ26 ዓመት በኋላ አዋራውን አራግፈው ሊጠቀሙበት ሲፈልጉ ይስተዋላል። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ምህዳር ግን ይህን ዶሴ የሚያስተናግድበት ቦታ የለውም። ምክንያቱም ምናልባትም ገዥው ፓርቲና መንግስት ‘ከስልጣናችን ቆርሰን እንስጥ’ ቢሉ እንኳን ስርዓቱ ይህን እንዲያደርጉ የሚፈቅድላቸው ስላልሆነ ነው።

እንደሚታወቀው በየትኛውም ዴሞክራሲያዊ ሀገር ውስጥ አንድ በህዝብ የተመረጠ ፓርቲ የሚያከናውናቸው ማናቸውም ተግባር የህዝብን ውክልና መሰረት ባደረገ መልኩ ነው። ህዝቡ የሚፈልገውን ለማስፈፀም እንጂ እርሱ የሚፈልገውን ነገር በህዝቡ ላይ ለመጫን አይደለም።

ሁላችነም እንደምንገነዘበው አገራችን ለዴሞክራሲ ገና ጀማሪ ናት። በዚህም ሳቢያ ስለ ዴሞክራሲ ፅንሰ ሃሳቦች የሚነሱ ጉዳዩች በሁሉም ወኖች በኩል ህፀፆችን መፍጠራቸው አይቀርም።

በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት ብሎም መቻቻልን የመሳሰሉ የዴሞክራሲ እሴቶችን በተገቢውና በፈጠነ ሁኔታ ገቢራዊ ማድረግ ያስቸግር ይሆናል። ፅንሰ ሃሳቦች አዲስ በመሆናቸውም በአስተማማኝ ሁኔታ ይተገበሩ ዘንድ ጊዜን ምርኩዝ ያደርጋሉ። ብዥታምን ሊፈጥሩ ይችላሉ። ሆኖም ለተግባራዊነታቸው ከሂደት መማር ይቻላል።

በሌላ በኩልም ያለፉት ስርዓቶች በሀገራችን ህዝቦች መካከል ፈጥረውት ያለፉት ፀረ-ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦች በቀላሉ የሚሽሩ አይደሉም። ፀረ-ዴሞክራሲያዊ እሳቤዎችን በዴሞክራሲያዊነት ለመቀየርም አስተሳሰብንና ስለ ዴሞክራሲ ያለንን አመለካከት መለወጥ ይገባል። በህዝቦች ውስጥ ለዘመናት ሲፈጠሩ የነበሩትን የተዛቡ ግንኙነቶች በጥቂት ዓመታት ውስጥ መቀየርም አይቻልም።

የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጊዜንና የአስተሳሰብ ልህቀትን ይጠይቃል። ይህ ሁኔታም ምናምባትም ችግሮችን በዴሞክራሲያዊ ማዕቀፍ ውስጥ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችን ሊያሰናክል ይችላል። እናም ዴሞክራሲው እንዲሰፋ እነዚህን ሁለት ተግዳሮቶች መፍታት ይገባል።

ይህን ዕውን ለማድረግም የህዝቡ ወኪሎች የሆኑት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ ይገባል። የህዝብ ወኪል የሆነ ፓርቲ ምንግዜም ማሰብ ያለበት ህዝቡን ነው። ሌላ ማንንም አይደለም። ህዝቡን ወክሎ ሲወያይም ዴሞክራሲው እንዲጎለብት የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ነው።

በአሁኑ ወቅት የአገራችንን ዴሞክራሲ ለማጐልበት የተለየ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። ከዚህ አኳያ አንዱ ቀዳሚ ስራ በገዥው ፓርቲና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል በሚደረግ ድርድር የምርጫ ህጉን የማሻሻል ጉዳይ ነው።

መንግስት ይህን ለመተግበር ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ድርድርና ውይይት እያካሄደ ነው። ድርድሩና ውይይቱ ሰጥቶ በመቀበል መርህ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለፓርላማ መናገራቸው ይታወሳል።

በተለይም ከምርጫ ህጉ ጋር ተያይዞ በተደረገ ድርድር የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ጋር የተገናኘው ጉዳይ መቋጨቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ አብራርተዋል። ይህም የአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በተለይም የተቃዋሚዎች ጋር በተያያዘ ተገቢውን ርቀት መጓዙን የሚያሳይ ነው።

ከዚህ ጎን ለጎንም ሲቪክ ማህበራት በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል። ከእነዚህ ውስጥ መንግስት ከሲቪክ ማህበራቱ ጋር ያካሄዳቸው ውይይቶች ተጠቃሽ ናቸው። ሲቪክ ማህበራቱ ለሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መጠናከር የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ እየተደረገ ነው። ይህም ማህበራቱ መንግስት በሞት ሽረትነት እውን እንዲሆን በማድረግ ላይ የሚገኘው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ፍሬ እንዲያፈራ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ነው።

በአጠቃላይ መንግስት የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በፅኑ መሰረት ላይ እንዲቆም ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው። ይህም የኢትዮጵያ መንግስት ዴሞክራሲን እውን ለማድረግ ሁሌም ዝግጁ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy