Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረው ግጭት የኪራይ ሰብሳቢዎች ተግባር ነው፡- ጠ/ሚ ኃይለ ማሪያም

0 857

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረው ግጭት የኪራይ ሰብሳቢዎች ተግባር ነው፡- ጠ/ሚ ኃይለ ማሪያም

በኢትዮ ሶማሌና በአሮሚያ አንዳንድ አከባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ኪራይ ሰብሳቢዎች በአካባቢው ያላቸውን ህግ ወጥ ንግድ ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ጥረት የተፈጠረ ግጭት መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማሪያም ደሳለኝ ተናገሩ፡፡

ተፈናቃዮችን ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ የፌደራል መንግስቱ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኪራይ ሰብሳቢዎች በአከባቢው ያለውን የጫት እና የጥቁር ገበያ ንግድን ለመቆጣጠር በሚደረግ ጥረት የብሔር ግጭት መልከ ሊያስይዙት ችለዋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በመሆኑም የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትን እና ተግባራትን መድፈቅ ካልተቻለ በዚህ አካባቢ ወደፊትም ለግጭት መፍትሔ መስጠት እንደማይቻል አሳስበዋል፡፡

መሰረታዊ መፍትሔውም ፖለቲካዊ ብቻ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ በግጭቱ የተሳተፉ አካላትን የመጠየቁ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡

በዚህ አካባቢ መከላከያ ሰራዊት ፈጥኖ ባይደርስ ኖሮ የበለጠ ዕልቂትና መፈናቀል ይከሰት እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

በእነዚህ ወቅቶች ሚዲያዎች ግጭቶችን ለማባባስ የሚሰሩበት አግባብ ተገቢ ባለመሆኑ በሃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ጠ/ሚንስትሩ ለአባገዳዎች፣ ለአገር ሽማግሌዎች፣ ለሀይማኖት አባቶች ለመምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ለአከባቢው ማህበረሰብ ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy