Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአምቦ ከተማ የታየው ሁከት ክልሉን የብጥብጥ ማእከል ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ያቀነባበሩት ሴራ ውጤት ነው- የክልሉ መንግስት

0 585

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ወጣቶች ከሁከት እና ብጥብጥ አካላት ቅስቀሳ በመራቅ የክልሉን ሰላም እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረበ።

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በአምቦ ከተማ የተከሰተው ግጭት ክልሉን የሁከት አውድማ ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ባሰራጩት የሀሰት መረጃ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል።

ባለፉት ሁለት ቀናት በአምቦ ከተማ በተፈጠረ ግጭት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ከአምቦ ከተማ አስተዳደር ባገኘነው መረጃ መሰረትበግጭቱ ምክንያት የስምንት ሰዎች ህይወት አልፏል።

ሶስት ተሽከርካሪዎችም ሙሉ በሙሉ መውደማቸውንን ነው የተገለፀው።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ፥ የክልሉ መንግስት በግጭቱ ምክንያት በደረሰው ሰብኣዊ እና ቁሳዊ ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገልፅዋል።

ግጭቱ “ከፊንጫ ወደ አዲስ አበባ ህገ ወጥ ስኳር እየተጓጓዘ ነው” በሚል የሀሰት መረጃ ምክንያት የተፈጠረ ነው ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ግጭቱን ከመጠንሰስ እስከ መተግበር ድረስ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ እንድሚያቀርብም አረጋግጠዋል።

አቶ አዲሱ ባለፈው ሳምንት በቡኖ በደሌ ዞን የተፈጠረውን ጨምሮ ትናንት እና ከትናንት በስቲያ በአምቦ ከተማ የታየው ክስተት የኦሮሚያ ክልልን የሁከት እና ነውጥ ማእከል ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ያቀነባበሩት ሴራ ውጤት ነው ብለዋል።

አዲሱ የክልሉ መንግስት አመራር ከክልሉ ህዝብ ጋር ካደረጋቸው ምክክሮች በመነሳት የኪራይ ሰብሳቢነት መገለጫ በሆነ ሙስና፣ ምዝበራ፣ ህገ ወጥ ንግድ (ኮንትሮባንድ) እና በህገወጥ ገንዘብ ዝውውር ላይ ጠንካራ እርምጃ መወስድ መጀመሩን ሃላፊው ገልፀዋል።

መንግስት በኢንቨስትመንት ስም ተይዘው ለብዙ ዓመታት ሳይለሙ ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን ማልማት ካልቻሉ ባለሃብቶች በመንጠቅ ለክልሉ ወጣቶች በማከፋፈል የህዝቡን ጥያቄ መመለስ መጀመሩንም አስታውሰዋል።

ይህ እርምጃ ብዙሃኑን የክልሉን ህዝብ ቢያስደስትም የሙሰኞችን ህገ ወጥ ጥቅም በማስቀረቱ እነዚህ ሃይሎች ክልሉን የሁከት ማእከል ማድረግ ላይ ተጠምደዋል ብለዋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሁከት መፍጠር እና መረጋጋትን ማሳጣት የህገ ወጥ ተግባራቸው እስትንፋስ ማስቀጠያ መሆኑን የሚያውቁት እነዚህ አካላት ክልሉን የሁከት ማእከል ለማድረግ ገንዘብ መድበው እየተንቀሳቀሱ ነው፤ የአምቦው ግጭትም ምንጩ ይሄው ነው ብለዋል።

አቶ አዲሱ ለመላው የኦሮሞ ህዝብ ባስተላለፉት መልእክት፥ ህዝቡ ለሁከት እና ነውጥ የሚቀሰቅሱ አካላት ክልሉን ወደ ትርምስ ከመክተት እና ለህገ ወጥ ድርጊታቸው ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር የዘለለ አላማ እንደሌላቸው ሊረዳ ይገባል ብለዋል።

ከሰላም በስተቀር ለክልሉ ህዝብ ዋስትና የለም ያሉት አቶ አዲሱ፥ ከሁከት እና ብጥብጥ፣ ከሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት በስተቀር ሌላ ጥቅም እንደማይገኝ የሚያቀው ህዝብ ከማንም በላይ ለሰላም ጥበቃ እንዲነሳም ጥሪ አቅርበዋል።

 

 

በዳዊት መስፍን

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy