Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢንቨስትመንት ዛሬ

0 527

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢንቨስትመንት ዛሬ

                                                  ደስታ ኃይሉ

በአሁኑ ወቅት የአገራችን የኢንቨስትመንት በተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል። የዘርፉን አፈፃፀም ተስፋ ሰጪና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትንም በተገቢው መንገድ በመሳብ ላይ ይገኛል። ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የአገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች ዘርፉን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ባለፉት ጊዜያት የሀገራችንን ምቹ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ላይ የሚገኙት የቻይና፣ የቱርክ፣ የህንድ፣ የአውሮፓ፣ የአረብ ሀገሮች ትልልቅ ኩባንያዎችና ባለ ሀብቶች ከመኖራቸው ባሻገር፤ እንደነ ሳምሰንግ፣ በጂኦተርማል ሃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት ላይ ለመሰማራት በዝግጅት ላይ የሚገኘው ግዙፉ የአሜሪካ ኩባንያ፣ በማዕድን ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩት የካናዳና የአወስትራሊያ ኩባንያዎችና ሌሎች ፍላጎት ያላቸው ኢንቨስተሮች በመበራከታቸው አሳማኝ አስረጅ በመሆናቸው ነው።

ለኢንቨስትመንት ፍሰት ሰንሰለት ዋነኛው ምክንያት የኢፌዴሪ መንግስት በሀገራችን የተፋጠነ ልማት ለማምጣት የሚያስችል ትክክለኛ ፖሊሲና ስትራቴጂ ከመንደፉም ባሻገር፤ በተግባር መተርጎም መቻሉም ይመስለኛል፡፡ እርግጥ በሀገራችን እየተመዘገበ ለሚገኘው ለውጥ በዋናነት ሊጠቀስ የሚችለው ጉዳይ የጠራ መስመር የያዘ፣ ሀገራዊውን ወቅታዊና ተጨባጭ ሁኔታ በማገናዘብ በተግባር ላይ የሚያውል አመራርና በህዝባዊ ተሳትፎ የተደገፈ አቅጣጫን የሚከተል የልማታዊ መንግስት መኖሩ የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይመስለኝም፡፡

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ መዋዕለ ንዋያቸውን በማፍሰስ፣ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብ የተለያዩ ማበረታቻዎችን በማመቻቸት በሩን ከፍት በማድረግና በተለያዩ አለም አቀፋዊ መድረኮች ተጨባጭ ሁኔታውን በማስረዳት በርካታ ባለሃብቶችን በመሳብ ላይ ነው፡፡

ዛሬ ላይ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በተለይም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግና ኢንዱስትሪ ዘርፎች የተሰማሩ የውጭ ባለሀብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መምጣት ችሏል፡፡ ሀገሪቱ ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኗን የተገነዘቡ በርካታ የውጭ ኩባንያዎችና ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ከፍተኛ ፍላጎት የማሳየታቸው ምስጢርም ይኸው ይመስለኛል።

አገራችን በምትከተለው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ትክክለኛ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ በግሉ ባለሃብት መሰራት የሚገባቸውና በመንግስት ሊከናወኑ የሚገቡ ተግባራት ተለይተው በመካሄዳቸው በሁለቱም በኩል ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው። የሀገር ውስጥም ይሁን የውጭ ባለሃብቶችን የሚሰማሩባቸውን ዘርፎች በመለየት አንፃራዊ በመሆነ መንገድ ለሀገሪቱ ዕድገት የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ተደርጓል።

የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገቱ አንቀሳቃሽ ሞተር መሆኑ በመንግሥት ታምኖበት በፍትሃዊ ውድድር ላይ እንዲመሰረት በመደረጉ ባለፉት 26 ዓመታት በርካታ ሐገራዊ ባለሃብቶች ተፈጥረዋል፡፡ እነአዚህ ባለሃብቶች በዓለም የገበያ ውድድር ውስጥ ጠንካራ አቅም እንዲኖራቸው ቀጣይነት ያላቸው ድጋፎች እየተደረገላቸው ነው።

በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ባለሃብቶቹ የሃብት ባለቤት እንዲሆኑና ለዜጎች የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ ሁኔታዎች ተመቻችተውላቸው በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሻራቸውን ማሳረፍ ችለዋል። ብዙዎቹ ሀብት እንዲያፈሩ እና ለብዙ ዜጎች የስራ እድል እንዲፈጥሩ ከማስቻሉም በላይ በኢኮኖሚው ውስጥ የራሳቸውን አሻራ ማሳረፍ ችለዋል።

የሀገር ውስጥን ባለሃብቶች ከውጭ ባለሃብቶች ጋር በማቀናጀት ለመፍጠር የተቻለው የገበያ ትስስርም ምቹ የኢንቨስትመንት መሰረትን ጥሏል ማለት ይቻላል። ከእነዚህ ውስጥ የወጪ ንግድ የብድር ዋስትና ሥርዓት መተግበር፣ የውጪ ምንዛሪ ተመን ማስተካከልና የምንዛሪ ዋጋው በገበያ እንዲወሰን ማድረግ በዋነኛነት የሚጠቀሱ ምቹ ሁኔታዎች ናቸው።

የኤክስፖርት ምርትን ከቀረጥ ነፃ ማድረግ፣ ለኢንቨስትመንት ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ የካፒታል ዕቃዎችና ግብዓቶች ያለ ቅድመ- ሁኔታ የሚገቡበትን ዕድል የመፍጠር ብሎም ባለሃብቶቹ ለስራቸው የሚሆን መሬት በሊዝ እንዲያገኙ መደረጉ ተጨማሪ አመቺ መደላድሎች ነበሩ። እነዚህ በመንግስት በኩል አቨስትመንትን ለማበረታታት የተወሰዱ እርምጃዎች የቅጭ ባለሃብቶች ሀገራችን ላይ ዓይናቸውን እንዲጥሉ ያደረጉ ተግባራት ናቸው።

እዚህ ላይ አንድ ዕውነታን ማንሳት አግባብነት ያለው ይመስለኛል። ይኸውም ሀገራችን የትምህርት፣ የጤና፣ የመንገድና የንፁህ መጠጥ ውሃ መሰረተ-ልማቶች ሙሉ ለሙሉ ያልተሟሉባት በመሆኗ ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ ከሀገራዊው ዕድገት ጋር የሚመጣጠን ግንባታዎች ለማካሄድ በመንግስት በኩል እንደሚካሄደው በተመሳሳይ ሁኔታ የግሉ ባለሃብት ሊከናወን አለመቻሉ ነው። የግሉ ዘርፍ የኦኮኖሚ ዕድገቱ አንቀሳቃሽ ሞተር መሆኑ በመንግሥት ታምኖበት በፍትሃዊ ውድድር ላይ እንዲመሰረት በመደረጉ ባለፉት ዓመታት በርካታ ሃገራዊ ባለሃብቶች እንዲፈጠሩ ቢደረግም፤ ባለሃብቱ ሊሰማራባቸው በማይችላቸው ዘርፎች መንግስት በተመረጠ አኳኋን ጣልቃ ገብቶ ልማቱን በዋነኝነት በማንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

እነዚህ ድምር ውጤቶች የሀገራችን መፃዒ ዕድል አመላካች ይመስሉኛል። መንግስት የሚከተለው የኢንቨስትመንት ፖሊሲ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን ያሳደገና የስራ ዕድል የፈጠረ ብቻ አይደለም። ይልቁንም የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት እንደ የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ሁሉ ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ማምጣት የሚችሉ የውጭ ባለሃብቶችም ወደ ሀገራችን እንዲተሙ አድርጓቸዋል።

ታዲያ ይህ በጎ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዳይደናቀፍ በመንግስት ፈፃሚዎች በኩል ብርቱ ጥረት መደረግ ይኖርበታል። በተለያዩ ወቅቶች የውጭ ባለሃብቶች የሚያሰሙትና ሆን ተብሎ በአስፈፃሚዎች የሚፈፀም የሚመስሉ አላስፈላጊ ውጣ ውረዶችን ማስቀረት ይገባል።

ከዚህ ጎን ለጎንም በኢንቬስትመንት ስም ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ምንም ዓይነት እሴት መጨመር ያልቻሉ ባላሀብቶችን ሚዛኑን በጠበቀና ፍሰቱን በማያስተጓጉል መልኩ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል።

መንግስት ለሀገራችን ኢንቨስተሮች ሙሉ ዋስተና ይሰጣል። ማንኛውም ባለሃብት እዚህ ሀገር ውስጭ ለሚያፈሰው መውአለ ነዋይ መንግስት ኃላፊነት ወስዶ የሚሰራ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ይህ ሁኔታም በሀገራችን ውስጥ የተጀመረው የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዳይስተጓጎል አድርጎታል።  

ይህ የመንግሥት ተግባር እንዲጠናከርና በተለይም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ወደ አገራችን እንዲገባ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት። ኢንቨስትመንት ለዜጎች ስራን የሚፈጥርና ገቢያቸውም በዚያው ልክ እንዲሻሻል ያደርጋል። ገቢው የተሻሻለ ዜጋም የህይወት ዘይቤውን በመለወጥ ሌሎች የደረሱበት ደረጃ ይደርሳል።  

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy