Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የምንዛሪ መጠኑ ከ44 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል ተያዘ

0 2,317

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የምንዛሪ መጠኑ ከ44 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የአሜሪካ ዶላር ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል መያዙን በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጥቅምት 8 ቀን 2010 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ተነስቶ በሀረር ባቢሌ መግቢያ ቶጎ ጫሌ ኬላ አካባቢ ድምሩ 1 ሚሊየን 625 ሺህ 100 የአሜሪካ ዶላር ወደ ውጭ ሊወጣ ሲል ተይዟል፡፡

ዶላሩ ከሃረር ከተማ በሚኒባስ ሲጓጓዝ የነበረ ሲሆን፥ ከሃረር እስከ ቶጎ ጫሌ ድረስ በተለምዶ ኮስትር ተብሎ በሚጠራው ተሽከርካሪ ከተጓጓዘ በኋላ በህብረተሰቡ ጥቆማ ቶጎ ጫሌ ኬላ ላይ ተይዟል፡፡

ተጠርጣሪዎቹም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን፥ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የትምህርት እና ኮሙዩኒኬሽን ቡድን አስተባባሪ አቶ ፍስሃ አብርሃም ገልጸዋል፡፡

በተያያዘም 580 ሺህ 509 የሳዑዲ ሪያል፣ 32 ሺህ 750 የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ ገንዘብ፣ 1 ሺህ 851 የኳታር ገንዘብ እንዲሁም በተጨማሪነት 31 ሺህ 164 የአሜሪካ ዶላር ቶጎ ጫሌ ኬላ ላይ መያዙንም ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል በዚሁ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ዋጋቸው 319 ሺህ 720 ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቃጠሎ መወገዳቸውን ተገልጸዋል፡፡

በቃጠሎ ከተወገዱት መካከል ምግብ ነክ ሸቀጣ ሸቀጦች፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅና ጫማ፣ የመዋቢያ ኮስሞቲክሶች፣ የጽዳት መጠበቂያ ዕቃዎች እና የሞተር ዘይቶች ይገኙበታል።

እቃዎቹ የአገልግሎት ዘመን ያለፈባቸው፣ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው እና ወደ ሃገር ውስጥ እንዳይገቡ ክልከላ የተደረገባቸው መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy