Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያና ሱዳን ዲፕሎማቶች በደቡብ ሱዳን ሰላም ዙሪያ ከሪክ ማቻር ጋር ተወያዩ

0 493

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያና ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደቡብ አፍሪካ ከሚገኙት የተቃዋሚ ሃይሉ መሪ ሪክ ማቻር ጋር በደቡብ ሱዳን ሰላምን ማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ተመካክረዋል፡፡

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁና የሱዳኑ አቻቸው ኢብራሂም ጋንዱር ከቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ጋር ውይይቱን ያካሔዱት በሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን ግጭት አስመልክቶ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች የደረሱትን ስምምነት ለመተግበር ይቻል ዘንድ  ከፍተኛ የተሃድሶ ፎረም ለማካሄድ የሚቻልበትን መንገድ ለማመቻቸት ነው፡፡

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን መግለጫ ዋቢ አድርጎ ሱዳን ትሪቡን እንዳስነበበው ስብሰባው  በደቡብ ሱዳን ሰላምን  የማረጋገጡ ጉዳይ አጣዳፊና አስፈላጊ መሆኑ ከስምምነት ላይ የተደረሰበት ፍሬያማና አወንታዊ ነበር፡፡

መግለጫው ሁለቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ሪክ ማቻር የተወያዩባቸውን ዝርዝር ጉዳዮችና የደረሱበትን ስምምነት በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ አለመስጠቱንም ነው ዘገባው ያመለከተው፡፡

የሁለቱ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት የሱዳን ሰላም ልዩ መልዕክተኛ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ፕሬዝዳንት ጋርም ኢጋድ የደቡብ ሱዳንን የሰላም ሂደት  ማደስ በሚቻልበት ዝርዝር ሁኔታ ላይ መምከራቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡

ባለፈው ሃምሌ የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት አዲስ አበባ ባካሔደው የደቡብ ሱዳንን የሰላም ሂደት የተመለከተ አስቸኳይ ስብሰባው  ሁሉም ተቀናቃኝ ኃይሎች በሀገሪቱ የተቀሰቀሰውን ግጭት ለመፍታት የደረሱትን ስምምነት እንዲያከብሩ፣ ከጸብ ጫሪነት እንዲታቀቡና በተሃድሶ ፎረሙ ትኩረት እንዲሰጣቸው የሚፈልጓቸውን ጉዳዮች የተመለከተ ተጨባጭ ፕሮፖዛል እንዲያስገቡ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy