Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ድርቅን ለመቋቋም ምርትና ምርታማነትን እናሳድግ!

0 337

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ድርቅን ለመቋቋም ምርትና ምርታማነትን እናሳድግ!

                                                         ታዬ ከበደ

ኢትዮጵያ ድርቅን ለመከላከልና ድርቅ በሚያጋጥማት ወቅትም ከተረጂነት ለመላቀቅና ራሷን ችላ ከችግሩ ለመውጣት አቅሟን እያዳበረች ትገኛለች፡፡ ይህ የሆነውም የግብርና ምርትንና ምርታማነቷን ማሳደግ በመቻሏ ነው፡፡ ይህ የተፈጠረ አቅም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መላው የአገራችን ህዝብ ግብርናን በማዘመን፣ የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅ እንዲሁም በመንከባከብና ለአፈር እና ለውሃ ጥበቃ የተሰጠውን ትኩረት ማጎልበት ይኖርበታል፡፡

እስካሁን ድረስ የተደረጉት ጥረቶች አገራችን ውስጥ የተፈጠሩ የድርቅ አደጋዎችን መቋቋም የቻሉ ናቸው። እንደሚታወቀው ከታዳሽ ሀይል በተለይም ከውሃ ሀይልን በማመንጨት በተነጻጻሪ ከሌሎች ሀገራት ቀድማ አረንጓዴ ልማትን መተግበር የጀመረችው ኢትዮጵያ፣ ሀገሪቱ ለአየር ንብረት ለውጥ ያላትን ተጋላጭነት ለመቋቋም የአረንጓዴ ልማት ማስፈፀሚያ ስትራቴጂ መቅረጿ አይዘነጋም፡፡

ከአረንጓዴው ልማት ስትራቴጂ መሰረቶች ውስጥ የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን፣ የደን ልማት፣ ታዳሽ ሀይል አማራጭ መከተል እንዲሁም የትራንስፖርት፣ የኢንዱስትሪ የቤት ልማትን በተስማሚ ቴክኖሎጂ መተግበር የሚሉት ጉዳዩች በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው።

የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ፣ ኢትዮጵያ ያቀደችውን የተለጠጠ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማሳካትና የሙቀት አማቂ ጋዞችን መቀነስ የሚያስችሉ አማራጮችና ዕድሎችን መለየት ዋናው አለማው ነበር፡፡ መንግስት በዘርፉ የተሻለ ልምድ ያላቸውን የልማት አጋር አካላትን ለመሳብ ጥረት እንደሚደረግም ስትራቴጂው ያመለክታል፡፡

የልማቱ አማራጭ አብዛኛውን የአገሪቱን ጠቅላላ ምርት ነዳጅና ተመሳሳይ የሀይል ምንጮችን ከውጭ በማስገባት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ሀገሪቱን ለውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ይዳርጋታል፡፡ ከታዳሽ ሀይል በተለይም ከውሃ ሀይልን በማመንጨት በተነጻጻሪ ከሌሎች ሀገራት ቀድማ አረንጓዴ ልማትን መተግበር የጀመረችው ኢትዮጵያ፣ ሀገሪቱ ለአየር ንብረት ለውጥ ያላትን ተጋላጭነት በፍጥነት የአረንጓዴ ልማት ማስፈጽሚያ ስትራቴጂ ቀርጻለች፡፡

የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን፣ የደን ልማት፣ ታዳሽ ሀይል አማራጭ መከተል እንዲሁም የትራንስፖርት፣ የኢንዱስትሪ የቤት ልማትን በተስማሚ ቴክኖሎጂ መተግበር የአገሪቱ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂው መሰረቶች ናቸው፡፡ የስትራቴጂው መሰረቶች አተገባበር እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

የመጀመሪያው የስትራቴጂው መሰረት የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን ነው፡፡ ዘርፉ የአገሪቱ ኢኮኖሚ መሪ ዘርፍ መሆኑና የአብዛኛው የሀገሪቱ ዜጎች መተዳደሪያ መሆኑ ልዮ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል፡፡

የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ ከዚህ ቀደም በተለምዶ እንደሚደረገው የሚታረስ መሬትን ማስፋፋትና የቀንድ ከብቶችን ቁጥር ከማሳደግ ይልቅ የመሬትንና የቀንድ ከብቶችን ምርታማነት ማሳደግ የአረንጓዴ ልማት አቅጣጫ ነው፡፡

የተሻሻሉ የሰብልና የቀንድ ከብት ዝርያዎችን አርሶ አደሩ እንዲጠቀም ማድረግ የግብርና ዘርፍ ማሳደጊያ ሰልት ነው፡፡ የደን ጭፍጨፋን ለመቀነስ በተለይም በተራቆቱና በተጎዱ አከባቢዎች ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እንዲሁም ከፍተኛ የመስኖ ልማት ቴክኖሎጂዎችን ለማስፋፋት ጥረት ተደርጓል፡፡ እነዚህ ጥረቶች ድርቅን የመቋቋም አካል ናቸው፡፡

እርግጥ በተፈጥሮ የአየር መዛባት ምክንያት በሀገራችን የድርቅ አደጋ ሲከሰት አዲስ ነገር አይደለም። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰት ጉዳይ በመሆኑ ምንም ማድረግ አይቻልም። ሆኖም ይህ በየጊዜው ሀገራችንን የሚጎበኛት የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብነት እንዳይቀየር መንግስት ብርቱ ጥረት አድርጓል።

እንደሚታወቀው ባለፉት ዓመታት የመንግስት ትኩረት ምንም ዓይነት የአየር ንብረት መዛባትና ድርቅ  ቢያጋጥምም፤ ህዝባችን  የማይራብበት ሁኔታን በመፍጠር ላይ ሲረባረብ ቆመቆየቱ አይዘነጋም። የኤልኒኖ አደጋ በተከሰተበት ወቅትም አደጋውን በመቀልበስ የልማት አጋር ሀገራትን ድጋፍ እምብዛም ሳያገኝ ችግሩ ወደ ረሃብነት ሳይቀየር መቋቋሙ ይህን ጥረቱን አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ከማንም የተሰወረ ጉዳይ አይመስለኝም።

በእኔ እምነት መንግስት ከአጭር ጊዜ አኳያ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰተውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል በፍጥነት በመድረስና ዕርዳታ ማድረግ እንዲሁም ድጋፉ ልማታዊ  በሆነ አኳሃን ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረጉ ለዜጎቹ ያለውን የኃላፊነትና የተጠያቂነት መንፈስ ስሜትንና ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ነው።

አርሶ አደሩ ከራሱ ተርፎ ለገበያ በማምረት ተጠቃሚ የሚሆንበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ፣ ሀገሪቱም ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ ጎዳና እንዲፈጠር አድርጓል። ለዚህ ስኬት በመንግስት በኩል የተወሰዱት እርምጃዎች በቂ ማሳያዎች ናቸው ማለት ይቻላል።

እንደሚታወቀው ሁሉ ኢትዮጵያ ለእርሻ የሚውል ሰፊ መሬት አላት። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች በአርሶ አደሩ እጅ እንዳለ የሚታሰበው መሬት አነስተኛ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ካለችውም መሬት ቢሆን የሚያገኘው ምርት ዝቅተኛ ነው። አመራረቱም እጅግ ኋላ ቀር ሆኖ ቆይቷል።

ይህን ዕውነታ የተገነዘበው የኢፌዴሪ መንግስት ዘርፈ ብዙ የማሻሻል ጥረቶች አድርጓል። በውጤቱም አነስተኛ ይዞታ ባላቸው አነስተኛ የአርሶ አደሮችን ማሳ ላይ ለውጥ ማምጣት አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ ሰብሯል። አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ትኩረት ከመስጠት ይልቅ ለሰፋፊ እርሻዎች ትኩረት መስጠትና ለውጥ ማምጣትን የሚሰብኩ ወገኖችን አፍ ማስያዝ የቻለ ትክክለኛ መስመርን በመከተል ውጤት ማምጣት ችሏል።

በአርብቶ አደሩም አካባቢ ተመሳሳይ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በመቅረፅና ቀደ ተግባር እንዲገባ በማድረግ ድርቅ ሊፈጥር የሚችለውን አደጋ በአያሌው መቀነስ ተችሏል። ከእነዚህ መንግስታዊ ጥረቶች ውስጥ የአርብቶ አደር የልማት ፓኬጆችን በመቅረፅ ውጤታማ ስራ ተከናውኗል።

አርብቶ አደሩ ከልማዳዊ የአኗኗር ባህል ወጥቶ ወደ ዘመናዊ ህይወት እንዲቀየር፣ ከአርብቶ አደሩ ጋር በመነጋገር ድርቅን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችሉ የመስኖ ልማት ስራዎችን በማስፋፋት ወደ ከፊል አርሶ አደርነት እንዲሸጋገር ብሎም ምርጥ ዝርያዎችን አግኝቶ ተጠቃሚነቱን እንዲያሳድግ፣ የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ውሃዎችን በአግባቡ የማሰባሰብ ስራዎችን እንዲያጠናክርና ሌሎች መሰል ተግባራቶች ተከናውነዋል።

ሆኖም አሁንም ድርቅን በዘላቂነት ለመቋቋም ሌሎች ተግባሮች መፈፀም አለባቸው። በአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂው መሰረት ግብርናውን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ማስፋት ያስፈልጋል። ምርትና ምርታማነት ሲሰፉና ሲጎለብቱ የድርቅ አደጋ በሚያጋጥምበት ወቅትም ቢሆን ትርፍ ምርት ለመያዝ ይቻላል። በመሆኑ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተግባሩን መከወን የድርቅ አደጋን ለመከላከል የሚያስችል ይሆናል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy