ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ የፖለቲካ መሰረተ ልማት
ዮናስ
የነጻ ኢኮኖሚ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መሠረት ሲጣል የግጭትና የብጥብጥ ምንጭ የነበረውን ድህነትና ኋላቀርነት ደረጃ በደረጃ ለማስወገድ የሚያስችሉ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ፕሮግራሞች የተነደፉ መሆኑ እሙን ነው። የዴሞክራሲ ጥያቄ በአገራችን ቁልፍ የትግል አጀንዳዎች መካከል አንዱ ሲሆን፤ የአገራችን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በተለያየ ወቅት በተደራጀና ባልተደረጃ መልኩ ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈሉበት መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ስለሆነም ነው ዜጎች ተነፍጓቸው የቆዩትን የመናገር፣ የመጻፍ፣ የመሰብሰብና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመደራጀትና ከቦታ ቦታ በነጻነት የመዘዋወር ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የህግ ጥበቃና እውቅና የተሰጣቸው። ከሁሉም በላይ፤ የዴሞክራሲ ባህልና እሴት ግንባታ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኝ ስለነበር ይህንኑ ክፍተት ለመሙላትና አስተሳሰቡ ስር እንዲሰድ የፖለቲካውን መሰረተ ልማት ማስፋፋት አስፈላጊ ስለነበር፤ የተለያዩ የዴሞክራሲ ተቋማት ተደራጅተው ወደ ስራ ገብተዋል። ከነዚህ ተቋማት መካከል ምክር ቤቶች፣ የምርጫ ቦርድ፣ የሚዲያ ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክና የሙያ ማህበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወዘተ ይገኙበታል።
የህዝብ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነት በሕገመንግስቱ ከተደነገገ ጀምሮ ከፌዴራል እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ የህዝብ ምክር ቤቶች ተደራጅተው በህግ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛሉ። በተለይም በፌዴራል ደረጃ የተቋቋሙት ሁለቱ የህዝብ ተወካች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች በየአምስት አመቱ በሚደረገው አገር አቀፍ ምርጫ በዜጎች ቀጥተኛና ነጻ ምርጫ አብላጫ ድምጽ ያገኙ ፓርቲዎችና ግለሰቦች የሚሳተፉበት ነው። የተወካዮች ምክር ቤት ፖሊሲና ህግ የማውጣት፣ አስፈጻሚ አካሉን የስራ መርሃ ግብርና በጀት የማጽደቅ፣ ስራ አፈጻጸም የመከታተልና የመቆጣጠር፣ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩን ሹመት የማጽደቅ፣ በክልሎች ሰብአዊ መብቶች ሲጣሱ በክልሉ ጋባዥነት ወይም በራሱ ተነሳሽነት ጣልቃ በመግባት የማረጋጋትና መፍትሄ የመስጠት ወዘተ ሃላፊነት የተሰጠው ተቋም ነው።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥራ ሲጀምር ስለ ዴሞክራሲያዊ ምክር ቤቶች አደረጃጀትና አሠራር በቂ ልምድ እና አሠራር ያልነበረው ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ በራሱ ጥረት እንደ አዲስ እያሟላ ለመሄድ ይገደድ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ብቃት ያለው እና አሳታፊ አደረጃጀት እና አሠራር ያካበተ ተቋም ለመሆን በቅቷል፡፡ ይህም ምክር ቤቱ ባለፉት 2ዐ አመታት ከጊዜ ወደ ጊዜ አቅሙን በመገንባት ህግ የማውጣት፣ በአስፈጻሚ አካል አፈጻጸም ላይ ህገ መንግሥታዊ የክትትልና የቁጥጥር ኃላፊነቱን ተግባራዊ ማድረግና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እንዲሁም የህዝብን ውክልና በተሻለ መንገድ ለመወጣት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህም ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የመንግሥትን ፖሊሲና ስትራቴጂ ወደ ተግባር ለመተርጎም ያስቻሉ እንዲሁም የዜጎችን መብቶች አሟልተው የሚያስጠብቁ ህግጋት ፀድቀው ወደ ሥራ ከመግባታቸውም ባሻገር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ የተጠያቂነት አሰራር እንዲረጋገጥ በማስቻል ላይ ይገኛል፡፡
ሌላው በምክር ቤቶቻችን የተመዘገበው ስኬት የሴቶች የፖለቲካ አመራርና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እየተመነደገ መምጣቱና ብዝሃነትን በተለይም የጾታ ብዝሃነትና እኩልነት የተቀበለ አሰራር ተዘርግቶ ተጨባጭ ውጤት መመዝገብ መቻሉ ነው።
ሁለተኛው ተቋም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሲሆን መላ የአገራችን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችን የወከሉ አባላት የሚገኙበትና ከየክልሉ በየብሄረሰቡ ቁጥር ተመርጠው የሚገኙበትና ሕገመንስግት የመተርጎም፣ የፌዴራል መንግስቱን በጀትና ለክልሎች ድጎማ ቀመር የማውጣትና የማጽደቅ፣ በክልሎች መካከል ግጭት ሲቀሰቀስ ጣልቃ በመግባት ግጭቶቹ መፍትሄ እንዲያገኙ የሚሰራ ተቋም ነው። ምክር ቤቱ በሀገራችን የሚገኙ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦችን ያቀፈ ሆኖ እያንዳንዱ ብሔረሰብ በአንድ ወኪል፣ በአንድ ሚሊዮን የህዝብ ቁጥር ተጨማሪ አንድ የምክር ቤት አባል እንዲኖረው ተደርጎ የተቀረፀ ነው። በዚህም መሰረት በአሁኑ ወቅት እነዚህኑ አባላት ይዞ የተሰጡትን ሕገመንግስታዊ ተግባርና ኃላፊነቶችን በመወጣት ላይ ይገኛል። ምክር ቤቱ ከሁሉ በፊት ህገመንግስቱን የመተርጎም ኃላፊነት የተሰጠው ሲሆን ባለፉት ተከታታይ የምክር ቤት ዘመኖችም ይህንኑ ቁልፍ ሕገመንግስት የመተርጎም ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
የአገራችን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር የዘመናት ጥያቄ በወሳኝ መልኩ ምላሽ ያገኘ ቢሆንም አልፎ አልፎ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውና የተለየ ማንነት አለን ብለው የሚያምኑ ብሄሮች በየአካባቢው የሚያነሷቸውን ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎችና አቤቱታዎችን ምክር ቤቱ ተቀብሎ ሲፈታ ቆይቷል። ሕገመንግስታዊ መሰረት ያላቸው ሆነው የተገኙ በተለያዩ ጊዜያት የቀረቡ የማንነት ጥያቄዎች (ለምሳሌ የስልጤ፣ የአርጎባነ እና የቅማንት) የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተናጠልና ከክልሎች ጋር በመነጋገር ምላሽ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ በሌላ በኩል በተለያዩ አካላት የሚነሱ ጥያቄዎች ሕገመንግሥታዊ መሠረት የሌላቸው ከሆኑ ሕገመንግሥታዊ ያለመሆናቸውን ከህገመንግሰቱ መርሆዎች በመነሳት ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ የፌዴራል መንግሥት ለክልሎች የሚሰጠውን ድጎማና የጋራ ገቢዎች የሚከፋፈሉበትን ቀመር የመወሰን ሥልጣንና ተልእኮ የተሰጠው በመሆኑ ለሕዝቦች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት እና ፍትሃዊ የሀብት ተጠቃሚነት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
ሌላኛው እና ወሳኝ ከሆኑት የፖለቲካ መሰረተ ልማት ዘርፎች መካከል ሊጠቀስ የሚገባው ተቋም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ነው።
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ካለፉት ተከታታይ ምርጫዎች የማስፈጸም አቅሙን እያጎለበተ በመሄድ በቋሚነት በየአምስት አመቱ በሚደረጉ ብሄራዊና ክልልዊ ምርጫዎች ህዝቡ የህጋዊ ስልጣን ባለቤትና ሉአላዊነት እንዲረጋገጥ በማድረግ ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ የራሱን አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ተቋም ነው። ቦርዱ ከተቋቋመበት ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜው ከሚፈጠሩና በተግባር ከታዩ መልካም ተሞክሮዎቹና የዓለም አቀፍ ምርጥ ልምዶች በመቀመር ከምዝገባ እስከ ድምፅ መስጫና የመጨረሻ ውጤት መግለጫ ድረስ በሳይንሳዊና በተደራጀ መንገድ የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ሲወጣ ቆይቷል፤ በመወጣትም ላይ ይገኛል። ቦርዱ የፖለቲካ ስልጣን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ፣ በህዝብ ድምጽና ከምርጫ ሳጥን ብቻ የሚረጋገጥ እንደሆነ በተከታታይ ምርጫዎቹ እንዲረጋገጥ በማድረግ ላይ ይገኛል። በአዲሲቷ ኢትዮጵያ በነውጥና በውጭ ሃይል ድጋፍና ግርግር ስልጣን ሊያዝ እንደማይቻልና በጉልበት ስልጣን የመያዝ አማራጭ የተዘጋ መሆኑን ሊያሳይ በሚያስችል መንገድ በርካታ ጫናዎችና ስም ማጥፋት ዘመቻዎችን በብቃት ተቋቁሞ መመከት የቻለና በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ የሃገሪቱን ህዳሴ እያቀላጠፉ ከሚገኙ ተቋሞች መካከል አንዱና ወሳኙ ነው።
ባጠቃላይ፣ እነዚህ ተቋማት በየጊዜው ከሚገጥሟቸው ችግሮች እየተማሩ የሃገሪቱን ህዳሴ በወሳኝ መልኩ ማረጋገጥ እንዲችሉ፤ ከኪራይ ሰብሳቢነት የፀዱና ከኪራይ ሰብሳቢ ሃይሎች ጋር የማይደራደሩ እንዲሆኑ በህዝብ ተሳትፎ መታገዝ ያለባቸው ሲሆን በመንግስትም በኩል አቅማቸውን መገንባት ወሳኝና ቁልፍ ተግባር ሊሆን ይገባል።