Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የውጭ ዜጎች ወሳኝ ኩነት ምዝገባ አፈፃፀም መመሪያ ስራ ላይ ዋለ

0 1,174

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የውጭ ዜጎች ወሳኝ ኩነት ምዝገባ አፈፃፀም መመሪያ ስራ ላይ መዋሉ ተገለፀ።

መመሪያው የውጭ ሀገር ዜጎች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጋብቻ፣ የልደት፣ የፍች፣ የጉዲፈቻ እና የሞት ሰነዶችን በኢትዮጵያ ማግኘት ያስችላቸዋል።

መመሪያው በፌደራል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የተዘገጀ ሲሆን፥ በመመሪያው መሠረት ሰነዶችን ከአዲስ አበባ እና በክልል መስተዳደሮች ማግኘት ይቻላል።

ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት የውጭ ሀገር ዜጎች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ የጋብቻ፣ የልደት፣ የሞት፣ የፍች እና የጉዲፈቻ ሰነዶችን ኢትዮጵያ ውስጥ ማውጣት ስለማይችሉ ውጭ ሀገር ለመሄድ ይገደዱ እንደነበር ይታወሳል።

በሀገራችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ እና በግል ኩባንያዎች ተቀጥረው የሚሠሩ ዜጎች ሰላሉ፥ እንዲሁም አዲስ አበባ የዲፕሎማሲ መዲና በመሆኗ የህብረተሰቡን እንግልት ለማስቀረት የተዘጋጀ መመሪያ መሆኑ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy