Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አዲስ አበባ ብቻ   ሳትሆን  ሁሉም  በለውጥ  ምህዋር ውስጥ ናቸው!

0 377

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አዲስ አበባ ብቻ   ሳትሆን  ሁሉም  በለውጥ  ምህዋር ውስጥ ናቸው!

ወንድይራድ ሃብተየስ

አዲስ አበባ  ፈርሳ እንደገና በመገንባት ላይ  ያለች  ከተማ ሆናለች።  በአዲስ አበባ ሁሉም ነገር አዲስ በአዲስ ሆኗል።  የአገራችን፣  የአፍሪካና የዓለም  መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ስሟን በሚመጥን ደረጃ በየቀኑ አዲስ እየሆነች እያበበች  ነው። ዘመናዊ  የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በከተማዋ  መጀመር፣  የሚያማምሩና ደረጃቸውን  የጠበቁ  መንገዶች ግንባታ በሁሉም የከተማዋ ክፍል  መታየት፣  የጋራ  መኖሪያ የቤቶች ልማት በስፋት መካሄድ ፣ በየጊዜው የሚበቅሉ  የሚመስሉ  በሁሉም የከተማዋ  አካባቢዎች እየተገነቡ ያሉ የሚያማምሩ ሰማይ ጠቀስ  ህንፃዎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ሆቴሎች ግንባታ  በአጠቃላይ  የርካታ የአገርና የውጭ ቀጥታ   ኢንቨስትመንት   መናሃሪያ   እየሆነች  ያለች  ከተማ – አዲስ አበባ።

አዲስ አበባ  ከኒዎርክና  ጄኔቭ  በመለጠቅ  ሶስተኛዋ የዓለማችን ዲፕሎማቲክ ከተማ ነች። በአዲስ አበባችን  በየዕለቱ በርካታ አህጉራዊና ዓለም ዓቀፋዊ ኮንፍረንሶች፣ ጉባዔዎችና ሰብሰባዎችን ወዘተ ይካሄዱባታል። መዲናችን ከዲፕሎማቲክ  መናሃሪያነቷ  ባሻገር  የኢንቨስትመንትና  ንግድ  መዕከልም  በመሆን ላይ  ትገኛለች።  ኢትዮጵያ ጠንካራ መንግስትና  አስተማማኝ  ሰላም ያለባት አገር በመሆኗ   አዲስ አበባባችን ለዓለም ዓቀፍ  ለኮንፍረንሶችና  ስብሰባዎች ተመራጭ ከተማ ከመሆኗ ባሻገር  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ   የኢንቨስትመንት  ማዕከል  በመሆን ላይ   ነች።     

አዲስ አበባ በማያቋርጥ የለውጥ ዑደት ውስጥ የገባች ከተማ በመሆኗ በበርካታ ዲፕሎማቶች፣ ተመራማሪዎችና ሳይንቲስቶችን፣ የውጭ ባለሃብቶች   እንዲሁም የተለያዩ የአህጉራትና የዓለም  ኃያላን አገራት መሪዎች መገናኛና መምከሪያ  ከተማ  ሆናለች። አዲስ አበባ የሰላም አምባ ነች።  አዲስ አበባችን  ከየትኛውም  የአፍሪካ አገሮች  የተሻለ   ወንጀል የሌለባት፣ የውጭ አገር ዜጎች  በነጻነት የሚንቀሳቀሱባት፣ ኑሮ ርካሽ የሆነባት ከተማ ነች። በበርካታ የውጭ አገር ዜጎች  ዘንድ ከተማችን ተመራጭ  ነች። ይህ የሆነው ጠንካራ መንግስትና እንግዳ ተቀባይ የሆነ ነዋሪዎች ስላሏት ነው።

በተለያየ ምክንያት አዲስ አበባን የመጎብኘት እድል ያጋጠማችው የውጭ ዜጎች የከተማዋን በፍጥነት መለወጥ  ይመሰክራሉ።   በከተማዋ ጫፍ እስከ ጫፍ እጅግ ፈጣን በሆነ ሁኔታ እየተካሄደ ያለው መጠነ ሰፊ የመሰረተ ልማት አቅርቦት ፣ የትላልቅ ህንፃዎች ግንባታና እንዲሁም ዘመናዊ የከተማ የባቡር አገልግሎት እንዲሁም አገሪቱን  ከወደብ የሚያገናኝ  ዘመናዊ  የባቡር መስመር መዳረሻ መሆኗ፣  ከትላልቅ  የማሳለጫ መንገዶች  እስከ  ውስጥ ለውስጥ  መንገድ  ግንባታዎች፣ እጅግ በርካታ የጋራ የመኖሪያ  ቤቶች ልማት፣  ሪል ስቴቶች  በመካሄድ ላይ በመሆናቸው  አዲስ አበባ  በፍጥነት  ማደግ በመጀመሯ  ነዋሪዎቿ  ዘበናዊ የአኗኗር  ዘይቤን እየተለመዱ መጥተዋል።   

አሁን ላይ  በአዲስ አበባ  ብቻ  ሶስት  ግዙፍ  የኢንዱስትሪ ፓርኮች በመገንባት ላይ ናቸው።  በእነዚህ ዘመናዊ  የኢንዱስተሪ ፓርኮች  ከማንኛውም  የአካባቢ ብክለት የጸዱ ሲሆኑ  በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች  ቀጥታ  የስራ ዕድል የሚፈጥሩ  ሲሆን  ለበርካታ  ተጨማሪ  ዜጎች  ደግሞ  በተዘዋወዋሪ ወይም ቀጥተኛ  ያልሆነ ገቢ  የሚያስገኙ  ናቸውሉ።  አሁን ላይ  በርካታ  የምዕራባዊያን  ኩባንያዎችን ጨምሮ  የቻይና፣ የጃፓን፣ ኮሪያ እንዲሁም የቱርክና የመካከለኛው ምስራቅ አገራትን  ኩባንያዎች  ከፍተኛ  መዋለ ንዋያቸውን በማፍሰስ  ላይ ናቸው።  

በአንድ ወቅት የአጃንስ  ፍራንስ ፕሬስ የዜና አገልግሎት የአዲስ አበባ ቋሚ ወኪል የሆነችው ጋዜጠኛ ጄኔ ቬግ   አዲስ አበባን በተመለከተ  “Boosting Ethiopia’s economic growth with building boom” በሚል ርእስ  ያወጣችውን ዘገባ  ላይ  እንዲህ  ብላ ነበር።   “በከተማዋ የሚካሄዱ  ግንባታዎች ከተማዋን  ግዙፍ የግንባታ ዞንነት ቀይሯታል”  በተመሳሳይ የአልጃዚራ ቴሌቭዥንም  ፈርሳ  እየተገነባች ሲል  የአዲስ አበባን  መሰረታዊ  ለውጥን ዘግቦት ነበር።  

የአዲስ አበባ በበርካታ  የግንባታ ስራዎች  ተጠምዳለች።  አዲስ አበባ በተለያዩ ምክንያቶች  በውጭ አገራት እንግዶች በየጊዜው የመጎብኘት እድል ያላት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በከተማዋ በመከናወን ያሉ  ግንባታዎች ይበልጥ ትኩረት ያገኙ ቢመስሉም ዛሬ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለው ዘርፈ ብዙ ዕድገት ግን በመላ አገሪቱ ባሉ ከተሞችና ገጠሮች ተመጣጣኝ በሆነ ሁኔታ  ለውጥ  በማስመዝገብ ላይ መሆናቸው  ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው።  የክልል ከተሞች  ከአዲስ አበባ ባልተናነሰ በለውጥ ምህዋር  ውስጥ ናቸው።  ኢትዮጵያ  የፌዴራል  ስርዓት  ከመከተሏ  ጋር ተያይዞ የአገሪቱ    ዕድገት በማዕከል የታጠረ  አይደለም።   የፖለቲካው ስርዓት ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚያዊ  ስርዓትም  ያልተማከለ በመሆኑ ዕድገቱ  በሁሉም አካባቢዎች  የሚታይ  ነው።  ይህ የፌዴራል ስርዓት  እውን  ከሆነ ጀምሮ   በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ተመጣጣኝ የሆነ ዕድገት በመመዝገብ ላይ ነው።

ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት ስር የሰደደ ድህነት ውስጥ ትገኝ የነበረች አገር የኢፌዴሪ መንግስት በቀረጻቸው ትክክለኛና አሳታፊ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ሳቢያ አገሪቱን ፈጣን  የዕድገት ምህዋር ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። ይህን ፈጣንና   ተከታታይ  ያለውን  የኢኮኖሚ  እድገት  ማስቀጠል ከተቻለ   አገራችን  እ. ኤ. አ በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ የመሰለፉ ራእይ  እንደሚያሳካ በዕርግጠኝነት  መናገር ይቻላል።  የመዕከላዊ ስታስቲክስ  ኤጀንሲ  ትንበያ እንደሚያመላክተው   ኢትዮጵያ የህዝብ ብዛት  አሁን ላይ  ወደ መቶ ሚሊዮን እንደሚጠጋ   ነው።  ይህን ያህል   የህዝብ ብዛት ይዞ   የዜጎችን   የነፍስ ወከፍ ገቢ ከ791 ዶላር በላይ ማድረስ  የአገሪቱ  ኢኮኖሚው ምን ያህል እንዳደገ  የሚያሳይ ነው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከምስራቅ አፍሪካ አገሮች ግዙፉ ኢኮኖሚ ለመሆን በቅቷል። ለውጥ ይህ ነው፤ ዕድገት ይህ ነው።    

በቅርቡ  በዓለም ዓቀፍ ደረጃ  በቢራ ጠማቂነቱ  የሚታወቀው  መቀመጫውን አምስተርዳም ያደረገው  ሄይንከን ኩባንያ  የአገራችንን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት  በመመልከት በመቶ ሚሊዪኖች ዶላር በመመደብ  የመንግስት  የቢራ ፋብሪካዎችን (ሐረርንና በደሌን)  ከመግዛት ጎን ለጎን በአዲስ አበባ   አዲስና እጅግ ዘመናዊ  ፋብሪካ  ከመገንባቱ   ባሻገር  በነባሮቹም ላይ   የማስፋፊያ ስራዎችን በማከናወን ገበያውን እጅግ አሳድጓል።   በተመሳሳይ የብሪታንያው  ዲያጆ የተሰኘው  ኩባንያም  በርካታ መዋለንዋይ በመመደብ የሜታ ቢራ  ፋብሪካን  በመግዛት የማስፋፋት ስራ አከናውኖ  ገበያውን  ተቀላቅሏል። እነዚህ ኩባንያዎች የአገሪቱን ቀጣይ ዕድገት ታሳቢ በማድረግ ነው ይህን ያህል ወጪ እያወጡ ፋብሪካቸውን እያስፋፉ የሚገኙት።

የውጭ ቀጥታ   ኢንቨስትመንትን   ለመሳብ እጅግ ወሳኝ ከሚባሉት ጉዳዮች መካከል    ቀዳሚው  ለህይወትና  ሃብት   ዋስትና የሚሆን  መንግስት፣ አስተማማኝ ሰላም፣  የመሰረተ ልማት አቅርቦት  (በተለይ  መንገድና  መብራት )፣   የገበያ አማራጭ (የህዝብ ብዛት)፣ የሰለጠነ የሰው ሃይል   ናቸው።  በእነዚህ መስፈርቶች መሰረት  አገራችን  ትክክለኛ  የኢንቨስትመንት መዳረሻ  እንደምትሆን  በዕርግጠኝነት መናገር ይቻላል። አሁን ላይ  አዲስ አበባችን ብቻ ሳትሆን ሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በፈጣን የለውጥ ምህዋር ውስጥ ገብተዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy