Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ማንም ከዚህ ፕሮጀክት ፊት ሊቆም አይቻለውም!

0 580

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ማንም ከዚህ ፕሮጀክት ፊት ሊቆም አይቻለውም!

ወንድይራድ ሃብተየስ

የአራት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ወጪን የሚጠይቅ ፕሮጀክት በራስ አቅም መገንባት መቻል አገራችን ያህል አቅም መፍጠሯን  የሚያሳይ ጉዳይ ነው። አገራችን ለተከታታይ 15 ዓመታት ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ ዕድገት ያስመዘገበችው እንደአንድንድ የዓለማችን አገራት በነዳጅ ሃብት ላይ ተመስርታ ሳይሆን መንግስት በተገበረው ትክክለኛና ውጤታማ እንዲሁም ህብረተሰቡን አሳታፊ  የሆኑ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን መተግበር በመቻሉ ነው።  አንድ ታዳጊ አፍሪካዊት አገር   በራሷ የውስጥ አቅም  ብቻ እንዲህ ያለ ባለ ብዙ ቢሊዮን ዶላር ወጪን የሚጠይቅ ፕሮጀክት እውን ማድረጓ  የሚያመላክተው ፕሮጀክቱ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍ እንዳለው ነው። በእርግጥ ሁሉም  በኢትዮጵያ የሚካሄዱ  የልማት ስራዎች ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ  ያላቸው ቢሆኑም እንደታላቁ የኢትዮጵያ  የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት  የህዝብን ቀልብ የገዛና ትልቅ ህዝባዊ መነሳሳትን የፈጠረ ፕሮጀክት እስካሁን አልታየም።  እንዲህ ያለ ታላቅ የህዝብ ድጋፍ ባለው ፕሮጀክት  ፊት ማንም የጥፋት ሃይል መቆም እንደማይቻለው ግብጻዊያን ፖለቲከኞች ሊያውቁት ይገባል።

የኢፌዴሪ መንግስት ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ  የመሰረተ ድንጋይ ከተጣለበት ከመጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ የሚያራምደው አቋም ወጥነት ያለውና ሁሉንም የተፋሰሱን አገራት ጥቅም የሚያስጠብቅ ነው። “ፍትሃዊ ተጠቃሚነት”ን የሚያረጋግጥ  መርህን ነው።  የኢትዮጵያ መንግስት በመልካም ጉርብትና የሚያምን ከኢሳያስ መንግስት ውጪ ከሁሉም የአፍሪካ መንግስታት ጋር መልካም ግንኙነትን መመስረት የቻለ ለህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት የሚሰራ በተጨባጭም ማረጋገጥ የቻለ መንግስት ነው። ይህ በተጨባጭ  የሚታይ እውነታ  በመሆኑ  አስረጅ ማቅረብ  የሚያስፈልገው ጉዳይ ባለመሆኑ እዚህ ላይ ባልፈው  መልካም  ይመስለኛል።   

አገራችን  የተፋሰሱን 86 በመቶ በላይ የሆነውን  ወሃ አመንጪ ብትሆንም፤ ከአንዳንድ የግብፅ ፖለቲከኞችና ምሁራኖች ሲሰነዘር የነበረው አስተያየት የሚያስገርም ብቻ ሳይሆን የሚያሳፍርም ጭምር ነው። በተለይ ግድቡ ሲጀመር አካባቢ  አንዳንድ የግብጽ ፖለቲከኞች “ኢትዮጵያ ጠብታ ውሃ መጠቀም አትችልም” “ጠብታ ውሃ በጠብታ ደም” ወዘተ የሚል አስተያየት በእኛ ኢትዮጵያዊያን ላይ ንዴት ብቻ ሳይሆን እልህም ፈጥረውብናል።  የእነሱ ኢ-ፍትሃዊ  አስተያየትና ራስወዳድነት እኛ ኢትዮጵያዊያኖችን የበለጠ እንድንጠነክር እንድንተባበር አድርጎናል። አሁንም አንዳንድ የግብጽ ፖለቲከኞች የሚሰጡት መረን የለቀቀ አስተያየት የእኛ ኢትዮጵያዊያንን ጥንካሬ የሚያሳድግ እንደሆነ ይሰማኛል።

እንደእኔ እንደኔ  ግብጻዊያን ቢቀበሉት  መልካም ነው የምለው የመጀመሪያ  እውነታ  የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ  ፕሮጀክት  ማንም የውጭ ሃይል ሊስቆመው የሚችል ፕሮጀክት አለመሆኑን ነው።  ምክንያቱም ይህ ፕሮጀክት በእያንዳንዱ አገር ወዳድ  ዜጋ ደም ውስጥ ሰርጿል።  የህዳሴው ግድብ  የለውጥ፣ የዕድገት፣ የአንድነት፣ የአብሮነት፣ ወዘተ መንፈስ  በህዝቦች  እንዲጎለብት እያደረገ ያለ ታላቅ ፕሮጀክት ነው። ታላቁ የህዳሴ ግድብ “የይቻላል” መንፈስን በኢትዮጵያዊያን ዘንድ እንዲፈጠር፣ አገራዊ መግባባት እንዲጎለብትና የአገራዊ የገጽታችን እንዲሻሻል ያደረገ  ታላቅ ፕሮጀክት ነው።  በዚህ  ፕሮጀክት ላይ ከአዋቂ እስከ ህጻን፣ ከምሁር እስከ አልተማረው፣ ከሃይማኖት መሪው እስከ ምዕመኑ፣ አገር ቤት ከሚኖረው እስከ ዳያስፖራ ወዘተ አሻራውን በዚህ ፕሮጀክት ላይ ያላሳረፈ አገር ወዳድ ዜጋ የለም። ዛሬ በአገራችን በርካታ ስራዎች እይተከናወኑ ቢሆንም እንደህዳሴው ግድብ የህብረተሰቡን  ቀልብ የገዛ ፕሮጀክት  የለም።

ግብጻዊያን  ግድብን  ለማስቆም ሲሉ በርካታ እንቅስቃሴዎችን አድርገዋል። አሁንም ተቆጥበዋል ለማለት አልደፍርም።  ለአብነት  በቅርቡ በራሳቸው ቴሌቭዥን እንደተመለከትነው  በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጭምር  አሸባሪ ተብለው የተለዩ ድርጅቶች እና አንዳንድ  ጽንፈኛ የዳያስፖራ ፖለቲከኞችን  አደባባይ ሲያሰባስቡና ዲቤ ሲደልቁና ሲያስደልቁ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።  ሚስጢርም አይደለም። እነዚህ አከላት  ለግብጻዊያን ፖለቲከኞች ሊሆን የማይችል የላም አለኝ በሰማይ አይነት  ተስፋ እየሰጧቸውም ነበር።  እነዚህ የጥፋት ሃይሎች  ራሳቸውን አግዝፈው፣  በኢትዮጵያ ውስጥ  ከፍተኛ  የህዝብ ድጋፍ እንዳላቸው  እንዲሁም ህዝቡ  ተከፋፍሏል፤ እኛ  እርዳታና ድጋፍ  ብናገኝ  ግድቡን ማስቆም እንችላለን በማለት  ግብጻዊያን ፖለቲከኞችን እያሳሳቷቸው ነው። ግብጻዊያን የእነዚህን  የጥፋት  ሃይሎች   የበሬ ወለደ  አካሄድ በአግባብ የፈተሹትና የተረዱት አይመስለኝም።  ምክንያቱም  እነዚህ የጥፋት ሃይሎች ለራሳቸው ህዝብ ለራሳቸው አገር  የማይበጁ፣ በሽብር ተግባራቸው  በህዝቡ ተንቀው የተተፉ ሆነው ሳለ በየትኛው መስፈርት ይሆን   ለግብጻዊያን ሊያስቡ የሚችሉት? ሰው ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ ይላል የአገሬ ሰው! እውነት ነው ለአገራቸውና ለህዝባቸው ታማኝ ያልሆኑ አካላት እንዴት ለባዕድ ታማኝ ይሆናሉ ተብለው እንደሚጠበቁ አይገባኝም። በመሆኑም  የግብጽ መንግስት ተቀራርቦ መስራት ያለበት  ከኢትዮጵያ መንግስትና ከህዝብ ጋር እንጂ ከጥፋት ሃይሎች ጋር መሆን  የለበትም። በእርግጠኘነት ግብጻዊያን የእነዚህን የጥፋት ሃይሎች አቋምን ዘግይተውም ቢሆን ይረዱታል ብዬ አስባለሁ።   

ሌላው ግብጻዊያን  አዲሲቷ ኢትዮጵያን ፍጹም አያውቋትም።  ኢትዮጵያ ፍጹም ተቀይራለች። አዲሲቷ ኢትዮጵያ በጠንካራ ህዝቦቿና መንግስቷ  ነገሮችን  በፍጥነት ወደ መልካምነት በመቀየር ላይ ያለች አገር ናት። ይህ ፕሮጀክትም የመቀየር መጀመሪያ አንድ ማሳያ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያን እንደቀድሞው ጊዜያት ይህን ብታደርጊ፤ ይበጅሻል፤ ይህ ይደረግልሻል፤ በሚል  የልጅ ጫወታ ጊዜን ተሻግራዋለች።  አገራችን  ማንም በፈለገው ጊዜና ጉዳይ  እጇን መጠምዘዝ  የሚቻልበት ወቅት አልፏል።  አዲሲቷ ኢትዮጵያ የማንም ጥገኛ አይደለችም። በመሆኑም  የትኛውም ማንም የውጭ ሃይል በውስጥ ጉዳያችን እንዲፈተፍት፣ የሚበጀንንና የማይበጀንን እንዲነግረን አንፈልግም። ኢትዮጵያ በልጆቿ የምትተማመንበት ጊዜ ላይ ደርሳለች። ይህን እውነታ ግብጻዊያን ሊረዱት ይገባል።  

በዓለም ዓቀፍ መስፈርት መሰረት አገራችን  የነፍስ ወከፍ የኤሌክትሪክ ድርሻም እጅግ ዝቅተኛ የሚባል ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት ታላቁን የህዳሴ ግድብ እየገነባ ያለው ይህን የሃይል አቅርቦት ለመቅረፍ  እንጂ ለመስኖ አገልግሎት ለመጠቀም አይደለም። ኢትዮጵያ ከሱዳንና ከግብጽ የተሻለ  ለሃይል ማመንጫነት  የሚያመች አቀማመጥ ያላት አገር እንጂ  በአባይ ተፋሰስ  እንደሱዳንና ግብጽ  ስፋት ያለው  በመስኖ የሚለማ መሬት የላትም። በመሆኑም በውሃው  መጠን ላይ የሚያመጣው ጫና አይኖርም። ይህን እውነታ የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ ገልጾታል። ይሁንና የግብጽ መንግስታት … ልጇን አታምንም  አይነት  አስመስሎባቸዋል። ይህ መታረም ያለበት ሁኔታ ነው።  የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ከድህነትንና ኋላቀርነትን ጋር የጀመሩትን የሞት ሽረት ትግል ከዳር ያደርሳሉ  ከሚባሉት በርካታ ፕሮጀክቶች መካከል ታላቁ የኢትየጵያ የህዳሴ ግድብ አንዱና ቀዳሚው ፕሮጀክት ነው። በመሆኑም የዚህ ፕሮጀክት እውን መሆን የድህነት ትግሉን የሚያጠናክረው በመሆኑ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለዚህ ፕሮጀክት ያላቸው ድጋፍ እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ማንም ይህን ፕሮጀክት ሊያስቆመው እንደማይችል ግብጻዊያን ፖለቲከኞች  ሊያውቁት ይገባል ባይ ነኝ።   

ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ስትገነባ የተፋሰሱን አገራት ፍተሃዊ ተጠቃሚነትንም  ከግምት በማሰገባት እንጂ ከወንዙ ማግኘት የሚገባትን እኩል ተጠቃሚነት የሚለውን ዓለም ዓቀፍ መርህ ተከትላ አይደለም። አባይ በትብብር የሚለማ ከሆነ የተፋሰሱ አገራትን በሙሉ በጥቅም ሊያስተሳስር የሚችል ትልቅ ሃብት ነው። ከላይ እንደተጠቀሰው ኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴው ግድብ ፕሮጀክትን የምትገለገለው ለሃይል ማመንጫ  በመሆኑ በወንዙ የውሃ መጠን ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ እንደማይኖር  ይልቁንም የወንዙን ፍሰት ዓመቱን ሙሉ የተመጣጠነ እንዲሆን ከማድርጉ በላይ የጎርፍ አደጋን እንደሚቀንስ  በዓለም ዓቀፍ ባለሙያዎች ጭምር ተረጋግጧል። ኢትዮጵያ አይነት መልካምድር ያላቸው የተፋሰሱ አገራት በመጪዎቹ  ዓመታት   የአካባቢ ጥበቃ ስራ በስፋት  መስራት ካልቻሉ የወንዙ ህልውና እጅግ አደገኛ ሁኔታ ላይ መውደቁ የማይቀር ጉዳይ ነው። ይህ ደግሞ ሁሉም ተያይዞ የሚጠፋበትን ሁኔታ የሚያስከትል መሆኑን ግብጻዊያን ፖለቲከኞች ሊገነዘቡት ይገባል።   

አንዳንድ የግብፅ ፖለቲከኞችና ምሁራኖች ግብፅ ማንንም ለምና አታውቅም፣ ወደፊትም አትለምንም፣ መብቷን የምታስከብርበት በቂ አቅም እንዳላት ሊነግሩን ወይም ሊያስፈራሩን እየዳዳቸው ነው። ይህ ፉከራና ድንፋታ አያዋጣም፤ ይልቁንም  ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጋር ተቀራርቦ መስራት ትክክለኛና ከውጤት ሊያደርሳቸው  የሚችል መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።  የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ሁሌም ከማም ጋር ለመነጋገር ለመወያየት በሩ ክፍት ነው። ታላቁ የኢትዮጵያን የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን በተመለከተ  እኛ ኢትዮጵያዊያኖችም  በማንኛውም ረገድ ከመንግስታችን ጎን እንደሆንን  ግብጻዊያን ፖለቲከኞች ሊገነዘቡት ይገባል።  

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy