Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

“በሕገ-መንግስታችን  የደመቀ  ሕብረ-ብሄራዊነታችን ለህዳሴያችን”

0 386

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

“በሕገ-መንግስታችን  የደመቀ  ሕብረ-ብሄራዊነታችን ለህዳሴያችን”

አባ መላኩ

ታላቁ መሪያችን አቶ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት የኢፌዴሪ ህገመንግስትን አስመልክተው የተናገሩትን አንድ ነገር ላስታውስ።  ሕገ-መንግስታችን  የህዝቦቻችን  የዘመናት ትግል ውጤት ነው፤ ይህ  ሰነድ  የአገራችንን የዘመናት ችግሮች እልባት  እንዲያገኙና  አዲሲቷ ኢትዮጵያ እንድትመሰረት አድርጓል። አዲሲቷ ኢትዮጵያ የህዝቦቿ ድምር ውጤት ሆናለች። የኢትዮጵያ ባህል ማለት የኢትዮጵያ ህዝቦች ባህሎች ድምር ውጤት ሆኗል። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ታሪክ ማለት የህዝቦች ታሪክ ተደምሮ ሆኗል።

ይህን የህዝቦችን  በርካታ ድምር ልዩነቶችን ማስተናገድ የሚያስችል ስርዓት አስፈላጊ ነው። እንደእኔ እንደኔ እንደኢትዮጵያ ያለ በርካታ ልዩነቶች የሚስተዋሉበት  አገር  ፌዴራላዊ ሥርዓትን መከተል ብቸኛውና የመጨረሻው አማራጭ ይመስለኛል።  የኢትዮጵያ ህልውን አደጋ ላይ የሚወድቀው  ልዩነትን ማስተናገድ የቻለውን  የፌዴራል ስርዓት ላይ ጣት መቀሰር ሲጀመር ነው። ኢትዮጵያ የብዙ ፍላጎቶች የሚንፀባረቁባት አገር እንደመሆኗ ብዘሃነቷን ማስተናገድ የማይቻላት ከሆነ የአገሪቱ ህልውና አደጋ ላይ የሚወድቅበት ሁኔታ እንደሚፈጠር መገመት የሚከብድ አይደለም።

ጽንፈኛ ሃይሎች ባለፉት 27 ዓመታት ሙሉ  ትናንሽና ጊዜያዊ ግጭቶችን  በማጎን አጠቃላይ የፌዴራሉ ስርዓት ድክመት  አድርጎ ለማቅረብ በርካታ መሯሯጦች አድርገዋል። አሁንም በማድረግ ላይ ናቸው። ጽንፈኛው ሃይል ጥፋት እንጂ የአገር ስኬቶችና  የህዝቦች ተጠቃሚነት አይታዩትም። ትናንሽ የፌዴራል ስርዓቱ ድክመቶችን የሚነቅሰው የጽንፈኛው የዳያስፖራ ፖለቲከኛ መነጽር ዝሆን ዝሆን  የሚያካክለው የፌዴራል ስርዓቱ ስኬቶች ለመመስከር ምነው ሰነፈ?  

የፌዴራል ሥርዓቱ  ሕገመንግስታዊ  መሰረት  ያለው፣  የህዝቦችን  እኩልነት ያሰፈነ፣  በህዝቦች  መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ፣  ጠንካራ አንድነት ያነገሰ፣ የህግ የበላይነት  የተረጋገጠበት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ ዴሞክራሲያዊ  ስርዓት ነው።  ኢትዮጵያ  የፌዴራል ሥርዓት መከተል  በመቻሏ  የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ  መብቶች ተጠብቀዋል።  ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው ማስተዳደር፣ ሃይማኖታቸውን  በነጻነት ማስፋፋት፣ ቋንቋቸው  መጠቀምና ባህላቸውን ማሳደግ፣ በማንነታቸው መኩራት፣  ዘላቂ ሰላም   ተረጋግጧል፤ ሁሉም በየደረጃው ፍትሃዊ  ተጠቃሚ የሚሆንበት ሁኔታ ተመቻችቷል።

ህብረ-ብሄራዊነትንም ማስተናገድ እንዲቻል ሕገ-መንግሥታችን አመቺ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። በአገራችን ብዝሃነትን ለማጠናከር መከናወን ካለባቸው ተግባራት መካከል የፌዴራል ሥርዓቱ እንዲጎለብት ማድረግ ነው። ብዘሃነትን ማስተናገድ ማለት በአብሮነትና በመቻቻል፣ ልዩነቶችን በማጣጣም አብሮ መኖር ማለት ነው። ልዩነት መኖር ተፈጥሯዊ ነው። በልዩነቶቻችን ውስጥ ያለውን አንድነት የውበትና የጥንካሬ ምንጭ ለማድረግና ለማጎልበት በቁርጠኝነት መሥራትን ይጠይቃል። መቻቻል ለአብሮነት የሚያስፈልግ የጋራ እሴት ቢሆንም ተቻችሎ ለመኖር ግን አንዱ የሌላውን እምነት፣ ምንነትና ማንነት በጥልቀት ማወቅ ጠቃሚ ነው። ከእነዚህ መተዋወቂያ መንገዶች ውስጥ አንዱ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች  ቀን ነው።  

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሚያዝያ 21 ቀን 1998 ዓ.ም ባካሄደው ሦስተኛ የፓርላማ ዘመን አንደኛ ዓመት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሕገ መንግሥቱ የፀደቀበትን ቀን ተንተርሶ በየዓመቱ ህዳር 29 የኢትዮዽያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ወይም የሕገመንግስት ቀን ተብሎ በአገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት እንዲከበር ወስኗል። በዚህም መሠረት  ዘንድሮ ለ12ኛ ጊዜ  በሰው ልጆች መገኛ  በሆነችው  አፋር ክልል  አሳይታ “በሕገመንግስታችን የደመቀ ህብረብሄራዊነታችን ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል   ይከበራል።

የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክብረ በዓል የሆነው ህዳር 29 ለህዝቦች የእርስ በርስ ትውውቅ እንዲጎለብት ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል። የህዝቦች የእርስ በርስ ትውውቅ ደግሞ ለፌዴራል ስርዓቱ መጠናከር አይነተኛ ሚና አለው። ከዚህ በፊት የተከበሩትን የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችንና ህዝቦች ቀን የተከበሩበትን ቦታና  መሪ ቃሎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

የመጀመሪያው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በ1999 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተከበረ ሲሆን መሪ ቃሉም “ሕገ መንግሥታዊ ቃል ኪዳን የአብሮነታችን መገለጫ ነው” የሚል ነበር። ሁለተኛው በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ብሄራዊ ክልል አስተናጋጅነት በሀዋሣ ከተማ በ2000 ዓ.ም በድምቀት ሲከበር መሪ ቃሉም “ልዩነታችን ውበታችን፤ ውበታችን አንድነታችንና ጥንካሬያችን ነው” የሚል ነበር።

ሦስተኛው ደግሞ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት በአዲስ አባባ በ2001 ዓ.ም የተከበረ ሲሆን መሪ ቃሉም “ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን በማጠናከር ልማታችንን እናፋጥናለን” የሚል ነበር። አራተኛው በምሥራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች አዘጋጅነት ማለትም ኦሮሚያ፣ አፋር፣ ኢትዮጵያ ሶማሌ፣ እና ሐረሪ ክልሎች እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በጋራ በድሬዳዋ ከተማ በ2002 ዓ.ም የተከበረ ሲሆን መሪ ቃሉም “መቻቻል ለዴሞክራሲያዊ አንድነትና ልማት” የሚል ነበር ።

አምስተኛው በአዲስ አበባ በ2003 ዓ.ም የተከበረ ሲሆን መሪ ቃሉም “የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዘን የሀገራችንን ህዳሴ ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ እናደርሳለን” የሚል ነበር። ስድስተኛው ደግሞ በ2004 ዓ.ም በትግራይ ብሄራዊ ክልል አስተናጋጅነት በመቀሌ ሲከበር መሪ ቃሉ “ሕገ-መንግሥታችን ለብዝሀነታችን ለአንድነታችንና ለህዳሴያችን” የሚል ነበር። ሰባተኛው በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት ባህር ዳር በ2005 ዓ.ም ተከብሯል።  መሪ ቃሉም “ብዙም አንድም ሆነን በመለስ ራዕይ በሕገ-መንግሥታችን ለህዳሴያችን” የሚል ነበር።  ስምንተኛው ደግሞ  በኢትዮጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት በጅግጅጋ ሲከበር መሪ ቃሉም “ሕገ-መንግሥታችን ለህዳሴያችን” የሚል ነበር።

ዘጠነኛው የታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በሚከናወንበት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግሥት በአሶሳ “በሕገ-መንግሥታችን የደመቀው ኢትዮጵያዊነታችን ለህዳሴያችን”  በሚል መሪ ቃል ተከሯል። አሥረኛው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን  በጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት በጋምቤላ ከተማ በ2009 ዓ.ም ሲከበር  መሪ ቃሉም “በብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተሳትፎ የላቀ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን” በሚል ነበር።  የአምናው በዓል  “ሕገ-መንግሥታችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችንና ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል የተከበረው በምሥራቅ የአገራችን ክፍል በሐረሪ ክልላዊ መንግሥት አዘጋጅነት በሐረር ከተማ  ነበር።  የዘንድሮውን የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች  በዓል “በሕገ-መንግስታችን የደመቀ ህብረ-ብሄራዊነታችን ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል  የሰው ልጅ መገኛ የሆነችው አፋር ክልል  ለማክበር  በዝግጅት ላይ ነች። አሳይታም ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን ለመቀበል ደፋ ቀና በማለት ላይ ነች።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy