Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ትላልቅ ስኬቶቻችንን በትናንሽ ህጸጾች …

0 521

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ትላልቅ ስኬቶቻችንን በትናንሽ ህጸጾች …

ወንድይራድ ኃብተየስ

አሁን አሁን እየተመለከትን ያለነው አንድ መሰረታዊ ችግር ያለ ይመስለኛል።  በቅርቡ በአንዳንድ አካባቢዎች ለተከሰቱ ቀውሶች  በምክንያትነት እየቀረበ  ያለው  የፌዴራል ስርዓቱ  እንደሆነ ተደርጎ ነው።  እንደእኔ እንደእኔ  ይህ አስተያየት ሚዛናዊነት የጎደለው እንደው በጭፍን የሚሰጥ አስተያየት  ይመስለኛል። የፌዴራል ስርዓታችን አገራችንን በስኬት ምህዋር ውስጥ ያስገባት፤ በየትኛውም መስፈርት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ አንድነት፣ ለብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ነጻነትና ዕኩልነት  ቤዛ የሆነ ስርዓት  ነው።  ዓለምን ያስደመሙ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ተጠቃሚ ያደረገ   ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና  ማህበራዊ  ዕድገቶች  የዚህ የፌዴራል ስርዓቱ  ውጤቶች ናቸው። የዚህ ስርዓት በርካታ  ስኬቶች  ተቋዳሽ እንደሆን ሁሉ ትናንሽና ጊዜያዊ  ለሆኑ  ችግሮችም በጋራ መፍትሄ   ማፈላለግ  ተገቢ ነው።  

እውነት እውነቱን እንነጋገር ከተባለ በደርግ ውድቀት ማግስት የነበረውን የአገራችንን ሁኔታ  ስናስታውስ ኢትዮጵያ ከመበታተን  የታደጋት  ይህ  የፌዴራል ስርዓት  አልነበረምን?  በርካታ የታጠቁ ሃይሎች አገሪቱን  ለመቀራመት ባሰፈሰፉበት ወቅት  የፌዴራሉ ስርዓት  ሁሉም ራሱን ማስተዳደር እንዲችል ሁኔታዎች በመመቻቸታቸው አገሪቱን  ከመፍረስ  ታድጓታል።  የአገሪቱንም አንድነት በጽኑ መሰረት ላይ እንዲቆም እንዲሁም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና  ህዝቦች ቁስላቸውን  እንዲረሱት ያደረጋቸው ይህ የፌዴራል አስተዳደር ነው። ይህ የፌዴራል ስርዓት እውን ባይሆን ኖሮ  የዛሬይቱ  ኢትዮጵያ  ትኖር ነበር የሚለው ጥያቄ የሁላችንም ቢሆን መልካም ነው። “A vows made in the storm are  forgotten in the calm” ይላሉ ፈረንጆች። ዛሬ ሁሉም አልፏል፤ ሁሉም ተረስቷል።

አሁን ላይ ምንም ችግሮች የሉም ማለቴ አይደለም። በርካታ ችግሮች ይስተዋላሉ። ይሁንና የችግሮቹ ምክንያቶች መሰረታዊ የሚባሉ ሳይሆኑ መንግስት መስራት የሚገባው የቤት ስራዎቹን በአግባብ ካለመወጣት የመነጩ ናቸው። ለግጭቶች መንስዔዎች  መልካም አስተዳዳር እጦት በተለይ  በህዝብ ደምና ላብ ላይ በመረማመድ  የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት  የሚሯሯጡ  ሃይሎች “ኪራይ ሰብሳቢዎች”  የፈጠሩት  ችግር  ነው። እነዚህን ችግሮች መንግስትና ህዝብ በሰከነ መንገድ ተነጋግረው መፍታት የሚቻሉ ናቸው።

ይህን  ችግር  ከመሰረቱ  መንቀል  ስንችል በየጊዜው  የተለያዩ  ምክንያቶች መደርደር  ተገቢ አይመስለኝም። አህዳዊ ስርዓት ብንከተል  ኖሮ  እነዚህ  ችግሮች በአገራችን ይከሰቱ ነበር ወይም አይከሰቱም  ለማለት  አሁን ላይ መልስ ማግኘት  አይቻልም። እሱን እንተወውና  የፌዴራል ስርዓታችን  ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ  እስትንፋስ ነውና እዚህ ስርዓት ላይ በትንሹም በትልቁም  ጣታችንን መቀሰር  “ከድጡ ወደ ማጡ” እንዳይሆንብን  እሰጋለሁ። በአገራችን  የሚስተዋሉ ጊዜያዊ  ቀውሶችን  ቁጭ ብለን ተነጋግረን ዘላቄታዊ  መፍትሄ  ማስቀመጥ  ስንችል፤ የስኬቶች ጎዳና፣ የአገራችን የህልውና ስትንፋስ የሆነውን የፌዴራል ስርዓታችን ላይ  አሜኬላ ባንጥልበት መልካም ነው። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የፌዴራል ስርዓታችን በርካታ ስኬቶችን አጎናጽፎናል። የትላልቅ ስኬቶች ምንጭ የሆነውን የፌዴራል ስርዓት  በትናንሽ ህጸጾች ባናድበሰብሰው መልካም ነው።

ይሁንና  የፌዴራል ስርዓታችን ገና ለጋ  በመሆኑ  ልንከባከበው  የሚገባ ነው።  የኢትዮጵያ የፌዴራል ስርዓት በጭቆና የኖሩ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው  እንዲያስተዳድሩና  ማንነታቸውን እንዲጠብቁ በማዕከላዊ መንግስትም ፍትሐዊ ውክልና እንዲኖራቸው አድርጓል።  ይህ በመደረጉም ሁሉም  ቡድኖች በብሔራዊ ደረጃ የፖሊሲ አወጣጥ ላይ ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድል አገኝተዋል።  በዚህም አሁን ላይ ህዝቦች በፌዴራል ደረጃ አልተወከልንም የሚል ቅሬታ ሲነሳ አይደመጥም።  

የኢትዮጵያ  የፌዴራል ስርዓት ውስጥ እያንዳንዱ ብሄር፣ ብሄረሰብና ህዝብ ተገቢው ውክልና እንዲኖር በመደረጉም  ኢትዮጵያዊነት   እንደቀድሞው ስርዓቶች በሃይል የሚጫን  ነገር  ሳይሆን በፍላጎትና በምርጫ የሚገኝ ዜግነት   ሆኗል።  በፌዴራል ስርዓታችን  ውስጥ ከሚታዩ ማንነቶች መካከል የክልል ወይም የቡድን ማንነትና ኢትዮጵያዊ ማንነት ናቸው። እነዚህ ሁለት ማንነቶች  ሳይዛነፉ እኩል ሊዳብሩና ሊተገበሩ ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን ችግር ይፈጠራል።  እንደእኔ ኢትዮጵያዊ ማንነትና በብሔር ማንነት  እኩል እንዲዳብሩ፣ ዴሞክራሲያዊ  ብሄርተኝነት  እንዲጎለብት  ተገቢው ስራ አልተሰራም። ይህ በመሆኑም በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች መደነቃቀፍ ተከስተዋል። ዜጎች ከኖሩበት አካባቢ ተፈናቅለዋል፤ ንብረታቸው ተዘርፏል ወዘተ በአጠቃላይ  መልካም ያልሆኑ ነገሮች ተከስተዋል። ይህ ደግሞ እየዋለ ሲያድር  በፌዴራል ስርዓታችን ላይ አሉታዊ ጫና መፍጠሩ አይቀርም።

በቀጣይ የብሄር ማንነቶችንና ኢትዮጵያዊ ማንነትን አስታርቀን መሄድ ካልቻልን ችግሮቻችን ሊወሳሰቡ ይችላሉ። አንዱ በአንዱ መስዋዕትነት የሚገኝ ሳይሆን ሁለቱንም ማታረቅ የሚቻልበት ሁኔታ አለ። ከላይ እንዳነሳሁት መንግስት በዘርፉ  በቂ ልምድና እውቀት ካላቸው ምሁራን ጋር በቅርበት በመስራት ለችግሮች አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል። እኛ ኢትዮጵያዊያን ሁላችንም ከተለያዩ  ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች  ብንሆንም ሁላችንንም በአንድነት የሚያስተሳስር ወፍራም ገመድ አለ- ኢትዮጵያዊነት።  በቅርቡ  የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት  ፕሬዚዳንት  ክቡር  አቶ  ለማ መገርሳ  ኢትዮጵያዊነት  ማንም ተነስቶ  እለቱን የሚያጠፋው  ነገር አይደለም ሲሉ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ትስስር ምን ያህል  ጠንካራ  እንደሆነ ገልጸውታል።    የኢትዮጵያ የፌዴራል ስርዓት ራሱን በራሱ ማስተካከል የሚችልበት አሰራር ያለው በመሆኑ ይህን መንገድ  መጠቀም አስፈላጊ  ነው።

የብሔር ማንነችንን በአካባቢያዊ አስተዳደሮች ልንጠቀምባቸው፣ ቡድናዊ ትስስሮቻችንን ልናጎለብትባቸው እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ደግሞ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሌሎች ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር የምንተሳሰርበት ሊሆን ይገባል። ኢትዮጵያዊ ማንነትን  ሌሎች ማንነቶችን ደፍጥጦ እንዲገኝ አለማድረግ በተመሳሳይ የቡድን ወይም የብሔር ማንነትን ከኢትዮጵያዊ ማንነት  የተለየ አድርጎ  አለማሰብ ተገቢ ነው።  እንደነዚህ ያሉ አስተሳሰቦች ለተሳሳተ የፌዴራሊዝም ስርዓት  እንዲጎለብት ምክንያት ስለሚሆን ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ  ይመስለኛል። ሁሉንም በልክ በልክ የማናስኬደው ከሆነ ዋጋ ያስከፍለናል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህን በአግባብ ተገንዝቦ ፍላጎቶቹን  ማስታረቅ ይኖርበታል። በቅርቡ በአገራችን  አንዳንድ  አካባቢዎች  በተከሰቱ ግጭቶች ቡድናዊ ማንነቶች ከኢትዮጵያ ማንነት እኩል ባለመጎልበታቸው  ሳቢያ  የቡድንተኝነት ስሜት በስፋት ሲራገቡ ተስተውለዋል።  እነዚህን ሁለት ማንነቶች ማመጋገብ የማይቻል ከሆነ   አደገኛ ነገር ሊፈጠር ይችላል።  

በአጽንዖት  ለተመለከተው  አንድ ሰው መርጦ ኦሮሞ ውይም አማራ ወይም ትግሬ ወይም ሶማሌ፣ ወይም ሌላ ብሄር ወይም ማንነት  ሆና ሊፈጠር አይችልም። ይህ በሆነበት ሁኔታ ሚስኪኖችን ማጥቃት፣ መዝረፍና መግደል  እጅግ የወረደ ተግባር ነው።  አንድ ሰው ለህይወቱ ብቻ ሳይሆን ለንብረቱም  መንግስት ዋስትና ሊሆነው ይገባል።  መንግስትም   መንግስት ሊባል የሚችለው የህግ የበላይነትን በሁሉም አካል ላይ እኩል  ማረጋገጥ ሲችል ብቻ ነው። ደካማውን  ከጉልበታሙ መታደግ  የመንግስት  ሃላፊነት  ነው።  ጠንካራ ነን ብዙ ነን የሚለው አካል  በፈለገ ጊዜ  እየተነሳ   አናሳዎችን  የሚገድልና  የሚዘርፍ  ከሆነ   የህግ የበላይነትን  ማረጋገጥ  የቱ  ጋ ነው?  በመሆኑም  የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ህብረተሰቡም  ከመንግስት ጎን በመሰለፍ  የበኩሉን ሚና  ሊወጣ   ይገባል።

እንደእኔ እንደኔ  የኢትዮጵያ ፌዴራል ስርዓት ትናንሽ ህጸጾች  ቢኖሩበትም  የታሰበለትን ትላልቅ ግቦች  አሳክቷል። ለአብነት ለዘመናት የአገራችን ችግር የነበረውን የፖለቲካ ችግሮች  ማለትም የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የማንነትና የዕኩልነት  ጥያቄዎችን ምላሽ ሰጥቷል፤ ሌላው ደግሞ አገሪቱን በፈጣን የልማት ምህዋር ውስጥ እንድትገባ በማድረግ በርካታ የህዝብ  የልማት ጥያቄዎች ተመልሰዋል። በዚህም ህብረተሰቡ  በተጨባጭ ተጠቃሚ  መሆን ችሏል።

በፌዴራል የአስተዳደር ስርዓት  ክልሎች ያለ መዕከላዊ መንግስት አሰባሳቢነት እንዲሁም መዕከላዊ መንግስትም  ያለክልሎች ድጋፍ ውጤታማ መሆን አይችሉም። አንዱ ክልል ቀውስ ሲገጥመው ችግሩ በዚያ ክልል ብቻ የሚቆም ሳይሆን አገር አቀፍ ችግሮችን የሚያስከትል በመሆኑ ሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባለው ለችግሮች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው።  በቅርቡ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ  ክልሎች የተፈጠሩ ችግሮች አገር አቀፍ  ደረጃ  የፈጠሩት ቀውስ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy