Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ወንድማማችነታችንን እናጠናክር!

0 336

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ወንድማማችነታችንን እናጠናክር!

ኢብሳ ነመራ

ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ የኦሮሞና የአማራ ህዝቦች የጋራ የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በዚህ የምክክር መድረክ ላይ  የተሳተፈው የኦሮሚያ ልዑክ  ከክልሉ 20 ዞኖችና 18 ከተሞች የተወጣጡ አባገዳዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ምሁራንና ታዋቂ አርቲስቶች የተካተቱበት 250 ያህል ሰዎችን የያዘ ቡድን ነው። የኦሮሚያ የልኡካን ቡድን በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ነበር። በምክክር መድረኩ ላይ 1 ሺህ 5 መቶ ያህል ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ መድረኩ በሁለቱ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳና አቶ ገዱ አንድአርጋቸው ነበር የተመራው፤

የኦሮሞና የአማራ ህዝብ ትውውቅ አዲስ አይደለም። ምናልባት  ግማሽ ሚሌኒየም ያህል እድሜ አስቆጥሯል። ሁለቱ ህዝቦች ሰፊ ወሰን ይጋራሉ። በስተሰሜን ኦሮሚያና በስተደቡብ አማራ ሁለቱ ህዝቦች ከታላቁ የአባይ ወንዝ ማዶና ማዶ ናቸው። አባይን ይጋራሉ። አባይ ያስተሳስራቸዋል። ሰሞኑን በሁለቱ ህዝቦች የጋራ መድረክ ላይ ለመሳተፍ የተጓዘውን የኦሮሚያ የልኡካን ቡድን አማሮች የአባይ ወንዝ ድልድይ ላይ ነበር የተቀበሉት፤

ሁለቱ ህዝቦች በዚህ ረጅም እድሜ ባስቆጠረው ግንኙነታቸው በርካታ እሴቶችን ተጋርተዋል። እንደማንኛውም ተዋሳኝ ህዝብ በጋብቻ ተሳስረዋል። በጋብቻ ትስስር በደም ተዋህደዋል። በተለይ የኦሮሞ ህዝብ ሌሎች ህዝቦችን የራሱ አድርጎ በሚይዝበት የጉዲፈቻ፣ ጡት ማጥባት (haarma hodhaa)፣ ሞጋሳ ስርአት በርካታ የአማራ ተወላጆችን ጎሳ ሰይሞ የራሱ አድርጓቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የኦሮሚያ ክልል የሃገሪቱ ማዕከላዊ አካባቢዎችንም የሚሸፍን በመሆኑና የሃገሪቱ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ/ፊንፊኔ መገኛም በመሆኑ ለመንግስትና ለሌሎች ስራዎች፣ ለንግድ ወዘተ. የመጡ በርካታ የአማራ ብሄር ተወላጆች ከኦሮሞዎች ጋር በጋብቻና ሌሎች የስጋ ዝምድናን ያህል በሚያቀራርቡ ባህላዊ ግንኙነቶች ተዛምደዋል።

በአሁኑ ጊዜ በመላ የኦሮሚያ ክልል በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ይኖራሉ። ከእነዚህ የአማራ ተወላጆች መካከል ኦሮሚኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሆኑ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። አብዛኞቹ ኦሮሚኛ ቋንቋ አቀላጥፈው ይናገራሉ። በሌላ በኩል እስከ 20 በመቶ የሚደርሱ ኦሮሞዎችም አማርኛ ቋንቋ አቀላጥፈው ይናገራሉ።

ኦሮሞዎችና አማሮች ነጻነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ውስጥ ደምቆ የሚታይ የጋራ ድርሻ ያላቸው ህዝቦች ናቸው። በታሪካዊው የአድዋ ጦርነት ላይ ሁለቱ ህዝቦች ጎን ለጎን ቆመው ተዋግተው ደማቸውን አፍስሰዋል። በአንድ ጉድጓድ ተቀበረው አጥንታቸው ተቀላቅሏል። ጠላታቸውን ድል ነስተው ተመሳሳይ የአሸናፊነትን አኩሪ ታሪክ ተጋርተዋል። በአምስቱ ዓመት የአርበኝነት ታሪክም በተመሳሳይ አብረው ተዋግተዋል። የሃገሪቱ የቅርብ ጊዜ ታሪክ በሆነውን በሶማሊያ በተቃጣው ወረራ ላይም ለመከላከል አንድ ሆነው ለሀገራቸው ተዋድቀዋል። በጸረ ደርግ ትግል ውስጥም እንዲሁ አብረው ተሰልፈዋል። አሁን ኦሮሚያን የሚያስተዳድረው ኦህዴድ የተጸነሰው የአማራ ክልልን በሚያስተዳድረው ኢህዴን/ ብአዴን ውስጥ መሆኑን ልብ ይሏል። የኤርትራን ወረራ ለመከላከል፣ የአልሸባብን ጥቃት ለመደምሰስ፤ እንዲሁም የአፍሪካንና የምስራቅ አፍሪካን ቀጠና ሰላም ለማስከበር አብረው ናቸው። እርግጥ ይህ ታሪክ የኦሮሞዎችና የአማራዎች ብቻ አይደለም። ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችም ይጋሩታል።

እንግዲህ፣ ግማሽ ሚሌኒየም ያህል እድሜ ያስቆጠረ ትስስርና የጋራ ታሪክ ያላቸውን የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች እንደአዲስ ማስተዋወቅ ለምን አስፈለገ? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።

በቅድሚያ የኦሮሞና የአማራ ብሄሮች ከተቀሩት የሃገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር አብረው ለመኖር ተስማምተው ያጸደቁት የኢፌዴሪ ህገመንግስት መግቢያ ላይ ባሰፈሩት መሰረት አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመመስረት ቃል ገብተዋል። የሰሞኑ የሁለቱ ብሄሮች የጋራ የምክክር መድረክ ይህን ተግባራዊ የማድረግ አካል ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ የምክክር መድረኩ የኢፌዴሪ ህገመንግስት፣ እንዲሁም የኦሮሚያና የአማራ ክልላዊ መንግስታት ህገመንግስታትም ድጋፍ ያለው ነው።

የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀጽ 88 ፖለቲካ ነክ ዓላማዎች በሚል ርዕስ ስር፣ በንኡስ አንቀጽ 2፤ “መንግስት የብሄሮችን፣ ብሄረሰቦችንና ህዝቦችን ማንነት የማክበርና በዚሁ ላይ በመመርኮዝ በመካከላቸው እኩልነት፣ አንድነትና ወንድማማችነትን የማጠናከር ግዴታ አለበት ይላል።” ይሄው ጉዳይ በተመሳሳይ አገላለጽ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ህገመንግስት አንቀጽ 103 ላይ እንዲሁም በአማራ ክልላዊ መንግስት ህገመንግስት አንቀጽ 109 ላይ ሰፍሮ ይገኛል።

የፌደራል መንግስት ይህን የህገመንግስት ድንጋጌ በተለያዩ መድረኮች የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ቀን ጨምሮ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ረገድ በቂ ስራ ተሰርቷል ማለት ግን አያስደፍርም። እውነት ለመናገር ባለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን ያህል ታሪካችን ከአንድነታችን ይልቅ በልዩነታችን ላይ ነው የሰራነው። በልዩነት ውስጥ ያለንን ወይም ሊኖረን የሚገባንን አንድነት ችላ ብለነዋል።  

የኦሮሚያና የአማራ ክልላዊ መንግስታትም በህግመንግስታቸው አንቀጽ 103 እና 109 ላይ የሰፈሩትን ድንጋገጌዎች በምን አኳኋን በየክልላቸው ተግባራዊ እንዳደረጉ መረጃ ባይኖረኝም፣ የሰሞኑን የጋራ የምክክር መድረክ በህገመንግስታቸው መሰረት በራሳቸው ተነሳሽነት ከየክላቸውን ተሻግረው በመሃከላቸው ያለውን አንድነትና ወንድማማችነት ለማጠናከር የወሰዱት እርምጃ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ሆኖ ይሰማኛል። እርግጥ ነው የዚህ አይነት የጋራ የምክክር መድረክ ሲካሄድ የኦሮሞና የአማራ ህዝቦች አዲስም የመጀመሪያም አይደለም። ከዚህ ቀደም በአማራና በትግራይ ክልሎች መካከል ተካሂዷል፤ በመቀሌ ከተማ፤ በቅርቡም በጎንደር ከተማ ተመሳሳይ መድረክ እንደሚዘጋጅ ሰምተናል።

በሌላ በኩል፤ አሁን ባለንበት ወቅት በኦሮሚያና በአማራ ክለሎች አንድነትና ወንድማማችነት ላይ ያጠላና በአፋጣኝ ሊታከም የሚገባው ችግር ይታያል።

በኦሮሞና በአማራ ህዝቦች መካከል የረጅም ጊዜ ትስስር ቢኖርም፣ ይህ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ በኋላ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በተፈጠሩ አጋጣሚዎችና ጥቃቅን ድርጊቶች  የተነሳ ቅያሜ እያጠላበት መጥቷል። በቀደሙት ስርአቶች በሃገሪቱ የብሄር ጭቆና የነበረ መሆኑ ገሃድ እውነት ነው። በዚህ ጭቆና በሃገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ላይ አስከፊ የሰብአዊ መብትና ነጻነት ጥሰቶች ተፈጽመዋል። ይህ የብሄር ጭቆና አንድ ብሄር በሌላው ወይም በሌሎች የፈጸመው አይደለም። ከዚህ ይልቅ አንድ ጨቋኝ  አምባገነናዊ ስርአት በህዝቦች፤ ይልቁንም በሁሉም ህዝቦች ላይ የፈጸመው ነው። በመሆኑም በተፈጸመው ብሄራዊ ጭቆና አንድ ብሄር ያውም የአማራው ብሔር በደምሳሳው ተጠያቂ ሊሆን አይችልም።

ይሁን እንጂ፤ ይህ እውነታ በተዛባ ሁኔታ እየቀረበ፣ አማራ እንደ ጨቋኝ፤ የተቀሩት ደግሞ የኦሮሞን ብሄር ጨምሮ እንደተጨቋኝ እንዲታዩ የተደረገበት ሁኔታ አለ። ከዚህ በተጨማሪ ጥቂት ትምክህተኞችና ጠባብ ብሄረተኞች በሁለቱም በኩል ይህን እየተጓተቱ፤ በተለይ በሁለቱ ብሄሮች ወጣቶች ዘንድ በጥርጣሬ የመተያየት ዝንባሌ ፈጥረዋል፤ እንዲዳብርም ሰርተዋል። ይህ በጥርጣሬ የመተያየት ዝንባሌ ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋ መጥቷል። ይህን እየሰፋ የመጣው በጥርጣሬ የመተያየት አዝማሚያ አንዳንዴ ለፖለቲካ ዓላማቸው ለመጠቀም በሚያራግቡ ወገኖች አቀጣጣይነት ግጭት ሆኖ ለመውጣት የሚቃጣው ያለመግባባት ጥንስስ መፈጠሩም ገሃድ እውነት ነው። አልፎ አልፎም ይህ ጥንስስ ግጭት ሆኖ የወጣባቸው አጋጣሚዎች አሉ።

በመሆኑም፤ ይህን በማይገባው አኳኋን እየሻከረ የመጣ የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት ማከምና ማዳን አስፈላጊ ነው። ሰሞኑን በኦሮሞና በአማራ ህዝቦች መካከል የተካሄደው የወንድማማችነት ኮንፈረንስም ይህን መሸካከር አክሞ ነባሩን መልካም ግንኙነት የማደስ እርምጃ ነው። እናም ድንቅ ነው!

በአጠቃላይ፤ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መካከል ከለው አንድነት ይልቅ ልዩነት ደምቆ የታየበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህ ደግሞ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ ከሆነው ህገመንግስት መሰረታዊ ሀሳብ ጋር የማይጣጣም ነው። በመሆኑም፤ በህገመንግስቱ አንቀጽ 88 ላይ፤ እንዲሁም በየክክላዊ መንግስታት ህገመንግስት ላይ በሰፈረው መሰረት እኩልነትን፣ አንድነትንና ወንድማማችነትን የሚያጠናክሩ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል። በአማራና በትግራይ ክልሎች ጀምሮ በኦሮሚያና በአማራ ክልል የቀጠለው ወንድማማችነትን የማጠናከር መድረክ፣ እንደአስፈላጊነቱ በተለይ ክፍተት በተፈጠረባቸው ብሄሮች እና/ወይም ክልሎች መካከል ሊካሄድ ይገባል። ከምንም በላይ አንድነታችንንና ወንድማማችነታችንን እናጠናክር!  

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy