Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የከፍታ ዘመናችን ማረጋገጫ

0 310

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የከፍታ ዘመናችን ማረጋገጫ

                                                        ታዬ ከበደ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአገራችን የከፍታ ዘመን አንዱ ማረጋገጫ ሆኖ የሚቀጥል ፕሮጀክት ነው። ግድቡ የአገራችን ህዝቦች ድህነትን ድል ለማድረግ ተስፋ አድርገው የሚያከናውኑት ፕሮጀክት ነው።

የግድቡ ግንባታ በአሁን ሰዓት የሚገኝበት ደረጃ የደረሰው ዜጎች ለከፍታ ዘመናቸው ማረጋገጫ የሚሆኑትን ኢንዱስትሪዎች እየገነቡ በመሆኑ ለኢንዱስትሪዎቹ ማንቀሳቀሻ የሚሆን የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን ለመሸፈንና ከፍላጎታቸው ከተረፈም የቀጠናውን አገራት ፍላጎት ለማሟላት መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ ውጭ ኢትዮጵያዊያን ምንም ዓይነት ፍላጎት የላቸውም።

በዓባይ ወንዝ ላይ ማናቸውንም ዓይነት የልማት ስራዎች የማከናወን መብት አለን። ዓባይን ለፍትሐዊነት እንጠቀምበታለን። አንዲት ሀገር የገዛ ወንዟን የመጠቀም መብት የሚከለክል አንዳች ዓለም አቀፍ የውኃ አጠቃቀም ህግ የለም፡፡ ለዘመናት አንቆና ቀስፎ የያዘን አስከፊ ድህነታችን እንኳንስ ዓባይን ያህል ለታላቅ የልማት ፕሮጀክት የሚውል ወንዝን ልንገድብ ይቅርና እዚህ ግባ ሊባሉ የማይችሉ የልማት ስራዎች ለመከወን የተቸገርን መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡

የዓለም የስልጣኔ ባለቤት የነበርን ህዝቦች በልማቱ ኋላ ቀርተን መታየታችን ታላቅ ሃፍረት ነው፡፡ ለምን ቢሉ ድህነትን ያህል አስከፊና አሳሳቢ ጉዳይ ባለመኖሩ ነው። በታሪክ የሚነገረው የስልጣኔ ባለቤትነታችን እንዴት እንደከሰመ ምስጢሩን ለማወቅ ከባድ ቢሆንም፤ ቀደም ሀገሪቱን ሲያስተዳድሩ የነበሩ ነገስታትና ፈላጭ ቆራጭ አምባገነን መሪዎች ተጠያቂ ለመሆናቸው ግን አያጠያይቅም፡፡

የዓባይ ወንዛችንን ለዘመናት በዘፈን እንጉርጉሮ ከማወደስና ከመርገም በቀር ምንም ሳንፈይድለት ኖረናል፡፡ በእጃችን ያለውን ወርቅ ሳናጌጥበት ለዘመናት ዘልቀናል፡፡ ዓባይ የበረሃው ሲሳይ ከመሆን አልፎ ለእኛ ምናችንም አልነበረም፡፡ በዓይናችን እየተመለከተው የቁልቁል ተፋሰስ ሀገሮች ከመጥቀም በላይ አፈራችንንና ማዕድናችንን ለእነዚህ ተፋሰስ ሀገራት እየገበረ ዘመናትን ተሻግሯል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎንም በየወቅቱ የግብፅን መንበረ- ስልጣን የሚቆናጠጡ መሪዎቿ ሀገራችን የገዛ ወንዟ እንዳትጠቀም የተለያዩ እኩይ ሴራዎችን ሲከውኑ መኖራቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡

ይህ ወንዙን በብቸኝነት የሚጠቀሙበት አሮጌ ስትራቴጂ ግን የአሁኑ ትውልድ መሪዎቻቸው ድረስ መሻገሩን ከሰሞኑ የሀገሪቱ ተቋማት ‘በዓባይ ወንዝ ላይ ያለንን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ ማንም ሊነካው አይችልም’ ካሉት አስገራሚ አባባል ለመገንዘብ አያዳግትም።

ሆኖም አንዲት አገር የገዛ ወንዟን የመጠቀም መብት የሚከለክል አንዳች ዓለም አቀፍ የውሃ አጠቃቀም ህግ የለም፡፡ ለዘመናት አንቆና ቀስፎ የያዘን አስከፊ ድህነታችን እንኳንስ ዓባይን ያህል ለታላቅ የልማት ፕሮጀክት የሚውል ወንዝን ልንገድብ ይቅርና እዚህ ግባ ሊባሉ የማይችሉ የልማት ስራዎች ለመከወን የተቸገርን መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡

የዓለም የስልጣኔ ባለቤት የነበርን ህዝቦች በልማቱ ኋላ ቀርተን መታየታችን ታላቅ ሃፍረት ነው፡፡ ለምን ቢሉ ድህነትን ያህል አስከፊና አሳሳቢ ጉዳይ ባለመኖሩ ነው። በታሪክ የሚነገረው የስልጣኔ ባለቤትነታችን እንዴት እንደከሰመ ምስጢሩን ለማወቅ ከባድ ቢሆንም፤ ቀደም ሀገሪቱን ሲያስተዳድሩ የነበሩ ነገስታትና ፈላጭ ቆራጭ አምባገነን መሪዎች ተጠያቂ ለመሆናቸው ግን አያጠያይቅም፡፡

የዓባይ ወንዛችንን ለዘመናት በዘፈን እንጉርጉሮ ከማወደስና ከመርገም በቀር ምንም ሳንፈይድለት ኖረናል፡፡ በእጃችን ያለውን ወርቅ ሳናጌጥበት ለዘመናት ዘልቀናል፡፡ ዓባይ የበረሃው ሲሳይ ከመሆን አልፎ ለእኛ ምናችንም አልነበረም፡፡ በዓይናችን እየተመለከተው የቁልቁል ተፋሰስ ሀገሮች ከመጥቀም በላይ አፈራችንንና ማዕድናችንን ለእነዚህ ተፋሰስ ሀገራት እየገበረ ዘመናትን ተሻግሯል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎንም በየወቅቱ የግብፅን መንበረ- ስልጣን የሚቆናጠጡ መሪዎቿ ሀገራችን የገዛ ወንዟ እንዳትጠቀም የተለያዩ እኩይ ሴራዎችን ሲከውኑ መኖራቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡

ይህ ወንዙን በብቸኝነት የሚጠቀሙበት አሮጌ ስትራቴጂ ግን የአሁኑ ትውልድ መሪዎቻቸው ድረስ መሻገሩን ከሰሞኑ የሀገሪቱ መሪዎች ‘በዓባይ ወንዝ ላይ ያለንን ታሪካዊ መብት ለማስጠበቅ ጉዳዩን ወደ መንግስታቱ ድርጅት እንወስደዋለን’ ካሉት አስገራሚ አባባል ለመገንዘብ አያዳግትም—ኢትዮጵያ በወንዙ ለብቻዋ የመጠቅም ፍላጎት ያላት በማስመሰል ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማደናገር በመሞከር።

ይህ ግን ኋላ ቀር አስተሳሰብ ነው። ኋላ ቀር አስተሳሰባቸውን እውን ለማድረግ በየጊዜው የሀገሪቱን መንበረ ስልጣን የሚቆናጠጡ መሪዎች አገራችን የዓባይ ወንዝን እንዳትጠቀም የተለያዩ ስትራቴጂ ነድፈው ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸው አይዘነጋም። ዛሬም ተመሳሳይ ሁኔታ የገጠመን ይመስላል።

ግብፆች ኢትዮጵያ ወንዙን እንዳትጠቀምበት ባለ በሌለ አቅማቸው ሲረባረቡ ቆይተዋል፡፡ በገዛ ወንዟ እንዳትጠቀም እንደ ምክንያት የሚያነሱት ደግሞ፤ ወንዙን መጠቀም ከጀመረች ግብጽ ለከፍተኛ አደጋ ትጋለጣለች ከሚል መሰረተ-ቢስ ስጋት በመነሳት ነው።  

እንደ እውነቱ ከሆነ ግብጾች በአንድ በኩል የዓባይ ውኃ ለሁሉም የማይበቃ አድረገው ሲያዩ፤ በሌላ በኩል ግን እጅግ አባካኝ በሆነ መንገድ ሲጠቀሙበት ይታያሉ፡፡ ለዚሁ በዋናነት ማሳያ ሊሆን የሚችለው በአስዋን ላይ የተገነባው ግድብ፣ በምድረ በዳ ላይ የተገነባና ለትነት በእጅጉ የተጋለጠ በመሆኑ በየዓመቱ ከ10 ቢልዮን ሜትሪክ ቶን በላይ ውኃ በትነት እንደሚባክን መረጃዎች መግለጻቸው ነው፡፡

ይህ ብክነት በተከዜ ወንዝ ላይ በዓመት ከሚፈሰው የውኃ መጠን የላቀ ነው፡፡ ጉዳዩን በዝርዝር ያጠኑ ባለሙያዎች እንደሚያስረዱትም፤ በዓባይ ወንዝ ላይ ያሉ ጥቅሞች በተለይም የኢትዮጵያና የግብጽ ጥቅሞች የሚጣጣሙ መሆናቸውን ይናገራሉ። ሁለቱም አገሮች ተጠቃሚ የማይሆኑበት ምክንያት የለም።   

ኢትዮጵያ በዓባይ ተፋሰስ ላይ ያለውን የተፈጥሮ መመናመን ብታስወግድ፣ በዝናብ እየታጠበ በመሄድ በግብጽና በሱዳን ግድቦች ላይ ደለል እየሞላ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥረውን አፈር መቆጣጠር ትችላለች፡፡ በዚህም ኢትዮጵያና ግብፅ እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበት ዕድል ሰፊ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ሱዳን በየዓመቱ የሚደርስባትን የጎርፍ መጥለቅለቅ ማሰወገድ ትችላለች፡፡ እንዲሁም የታችኛው የተፋሰሱ ሀገሮች ርካሽ የኤሌትሪክ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። ውኃው ለትነት በከፍተኛ ደረጃ ስለማይጋለጥም ቢያንስ ሶስት ቢልዮን ኪዮቢክ ውሃ ሊቆጠብና ለተፋሰሱ ሀገሮች ጥቅም ሊውል መቻሉም መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

ታዲያ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የግብፅ ባለስልጣናት እነዚህ ጥቅሞች ሊጣጣሙ የማይችሉ አስመስለው ኢትዮጵያ የአባይ ወንዝን እንዳትጠቀም ከጤነኛ አመለካከት ያልመነጩ የተለያዩ የተለያዩ ሃሳቦችን ሲያቀርቡ ኖረዋል፡፡ ብድርና እርዳታ እንዳታገኝ ሲያደርጉት የነበረው ጥረት የዚህ ሁኔታ መገለጫ ነው።

ይሁን እንጂ ዛሬ ሀገራቸን የማንንም እገዛ ሳትሻ ህዝቦቿን በማስተባበር ዋና ዋና የልማት ትልሞችን በራሷ አቅም የማከናወን አቅም አላት። ምስጋና የህዝቦችን ተጠቃሚነት ከፍ በማድረግ የአገሪቱን ምጣኔ ሃብት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ እንዲሆን ላደረጉት የመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ይሁንና። በዚህ አቅማቸውም ዛሬ ኢትዮጵያዊያን የህዳሴ ግድቡን የከፍታ ማረጋገጫቸው አድርገው እየገነቡት ነው—የተፈጥሮ ሃብታቸውን የመጠቀም መብታቸውን አውን አድርገው።  

በአሁኑ የህዝቦችን የልማት አስተሳሰብ በእጅጉ ተለውጧል፡፡ ዛሬ ‘በቅኝ ገዥ ውሎች እንተዳደር’ የሚለው የግብጾች አስተሳሰብ ተቀባይነት የለውም። በአገራችን የተገነባው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት የህዝብን ተሳትፎ በሚያረጋግጡና ዋጋ ባላቸው ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እየተመራ የሀገሪቱን የከፍታ ጉዞ ለማረጋገጥ አየሰራ ነው፡፡  በዚህም በህዝብ ተሳትፎ የሚገነቡ ታላላቅ ፕሮጀክቶች በመገንባት ላይም ይገኛል፡፡ የህዳሴው ግድብም ከእነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ ነው።

እርግጥ ነው በአንድ ወቅት አንቀላፍተን የነበረን ህዝቦች አሁን ልማታዊ መንግስታችን በፈጠረው መነቃቃት ከእንቅልፋችን ነቅተን ያንን የቀድሞ ስልጣኔያችንን ለመመለስ በአዲስ መንገድ ጎዞ ጀምረናል፡፡ የከፍታ ጉዟችንን ለማደላደል እየሰራን ነው። የህዳሴው ግድብ ገድሞ የዚህ የከፍታ ዘመናችን ማረጋገጫ ሆኖ ይቀጥላል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy