Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ያለ ዝናብ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይቻላል!

0 438

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ያለ ዝናብ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይቻላል!

ዳዊት ምትኩ

ዝናብ አጠር አካባበዎች ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ ይቻላል። ለዚህም በአነስተኛ ውሃ አጠቃቀም ዘዴ በቅርቡ በትግራይ ክልል ራያ አካባቢ የተከናወነ ተግባር ምርጥ ማሳያ ነው። ይኸውም በመስኖ ስራ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን ነው።

በመስኖ መጠቀም ምንም አይነት ዝናብ ሳያገኙ ከፍተኛ ምርት ማግኘት እንደሚቻል አርሶ አደሮቹ ጥሩ መማሪያ ናቸው። ይህ ተሞክሮም ወደ ሌሎች አካባቢዎች መስፋፋት ያለበት ይመስለኛል። በተለይም ግብርናውን በማዘመንና በዓመት የሚገኘውም ምርት ከፍ በማድረግ ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል አሰራር ነው።

እንደሚታወቀው ሁሉ መንግስት የማስፋት ስትራቴጂን በመጠቀም በአነስተኛ የአርሶ አደር ማሳ ላይ ለውጥ ማምጣት ተችሏል። ይህም በአነስተኛ ማሳ ላይ ብዙ ምርት ማግኘት ያስቻለ፣ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የላቀ ሚና ተጫውቷል። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተመሰረተው በግብርና ላይ እንደመሆኑ መጠን፤ የአርሶ አደሩ የአመራረት ዘይቤ መለወጡ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል።

በዚህም ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን በበቂ ሁኔታ ማምረት ተችሏል። ይህም አጠቃላይ የሀገሪቱን ምጣኔ ሃብት ዕድገት ከፍ አድርጓል። በተለይ ባለፉት 10 ዓመታት የተገኘው ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት የምርትና ምርታማነት ማደግ ውጤት ነው።

ባለፉት ዓመታት መንግሥት ግብርናውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ተገንዝቦ ሲሰራ ቆይቷል። በያዝነው ሁለተኛው የልማት ዕቅድ ላይም በመጀመሪያው የዕቅድ ዓመት ላይ የተገኘውን አመርቂ ውጤት ይበልጥ አጎልብቶ ለመቀጠል እየተሰራ መሆኑን መረጃዎች ያስረዳሉ።

የግብርና ልማት መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት ይችል ዘንድ በበሁለተኛው አምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትኩረት ተሰጥቶታል። እንደሚታወቀው አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ለእርሻ ሊውል የሚችል ሰፊና ለም መሬት እንዲሁም የአርሶ አደሩ ጉልበት አለ። በሀገሪቱ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ታዲያ ይህ ግብርናው ውጭ ከፍተኛ እምቅ ሃብት ነው። ይህ ሃብት ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል እየፈጠረ ሲሆን፤ ገና ምንም ያልተነካ እምቅ በመሆኑም ውጤት ሊያመጣ የሚችል ነው። ሀገሪቱን ለመለወጥ ወሳኙ ሃብት ተደርጎ መወሰዱም እንዲሁ።

ቀደም ሲል እንደገለፅኩት ምርትና ምርታማነት በማደጉ ሳቢያ የአርሶ አደሩ ህይወት በአያሌው ተለውጧል። እንዲያውም በአንዳንድ አካባቢ የሚገኙት አርሶ አደሮች ትርፍ አምራች እንዲሆኑ አስችሏቸዋል። ይህ ትርፍ አምራችነታቸውም ከተጠቃሚነታቸውባሻገር ሌሎች አካባቢዎች በተፈጥሮአዊው የድርቅ አደጋ በሚጠቁበት ወቅት የሚፈጠረውን ክፍተት እየሞሉ ነው። ምርትና ምርታማነት በማደጉ ሳቢያ ከፍተኛ ምርት እንደሚገኝ ይታሰባል።

በቅርቡ የእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ በ2009 የምርት ዘመን ከ345 ሚሊዩን ኩንታል በላይ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል። በአብዛኛዎቹ የመኸር አብቃይ አከባቢዎች የተስተካከለ የዝናብ ስርጭት በመኖሩ በአሁኑ ወቅት ጥሩ የምርት ሁኔታ በእርሻ ማሳ ላይ መኖሩን ሚኒስቴሩ መግለፁ ይታወሳል። አርሶ አደሩም በእሸትና በቡቃያ ደርጃ ያሉ ምርቶችን በአግባቡ የመጠበቅ፣ በየጊዜው ማሳውን የመፈተሽ ሰብሉ በአረም እንዳይጠቃ ክትትል ማድረጉ ተመልክቷል።

ተባዮችን በባህላዊ መንገድ መከላከል ከአቅም በላይ በሚሆንበት ወቅትም ፀረ- ተባይ ኬሚካሎችን በመርጨትና በመከላከል በአሁኑ ወቅት በጥሩ ሁኔታ ማሳ ላይ የሚገኘውን ምርት ወደ ጎተራው እስኪገባ ድረስ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ርብርብ እያደረጉ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ የሰብል ምርቱን ለማሳደግ አዳዲስና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ለማስተዋወቅ ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። እንዲሁም የአርሶ እደሩን ጉልበት የሚያግዙ የሚደግፉና ጉልበቱን ውጤታማ የሚያደርጉ መጠነኛና አነስተኛ የሜካናይዜሽን ስራዎች እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገባ ጥረት እየተደረገ ነው።

ታዲያ ከዚህ የሚኒስቴሩ ማብራሪያ መረዳት የሚቻለው ነገር ቢኖር፤ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ መንግስታዊ ጥረት ላይ የተወሰኑ ተግዳሮቶች መኖራቸውን ነው። እርግጥ የግብርና ምርት የጥራት ችግርና ብክነት አሁንም ያልተሻገርናቸው ችግሮች ናቸው። ያም ሆኖ ችግሮቹን መቅረፍ ያስፈልጋል። ያም ሆኖ የመስኖ አሰራሮችን በመከተል ምርቱን ከፍ ማድረግ ይገባል።

የዋና ዋና ሰብሎችን ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ ዋናው ጉዳይ የአብዛኛውን አርሶ አደር የምርታማነት መጠን ምርጥ አርሶ አደሮች የደረሱበት ደረጃ ማድረስ መሠረታዊ ግባችን ሊሆን የሚገባ መሆኑ ነው። ይኸም በዋና ዋና የምግብ ሰብሎች፣ የፋብሪካ ግብኣቶች እንዲሁም የኤክስፖርት ሰብሎች ጭምር መከናወን ያለበት ግብ ተደርጐ ተወስዷል።

ይህ መሠረታዊ ግብ እንደተጠበቀ ሆኖ በተከታታይ የሞዴል አርሶ አደሮች ምርታማነት ደረጃ ላይ የደረሱ በርከት ያሉ አርሶ አደሮች ያሉ በመሆኑ የግብርና ምርምር ተቋማትን አቅም በማጐልበትና በማበረታታት እነዚህ አርሶ አደሮች ወደ ግብርና ምርምር ተቋማት የምርታማነት ደረጃ እንዲቀራረቡ ተጨማሪ ፓኬጆች ተዘጋጅተው ርብርብ እየተደረገባቸው ነው።  

የአርሶአደሩን የሰብል ልማት የማስፋትና ምርታማነቱንና ጥራትን ከፍ በማድረግ በገበያ ተወዳዳሪ ከመሆን በተጨማሪ የአትክልትና ፍራፍሬ የማልማት አቅሙን የማሳደግና በዘርፉ እመርታ ለማምጣት እየተሰራ ነው። አርሶአደሩ በራሱ፣ ከተማሩ ወጣት አነስተኛ የግብርና ኢንቨስተሮች ወይም ከአገር ውስጥና ከውጭ ባለሃብቶች ጋር በመቀናጀት ምርታማነትንና የምርት ጥራትን እንዲያረጋግጥ እየተሰራ ነው። ይህ ቅንጅት የሚጠቅመን አነስተኛ ማሳ ላይ የሚያመርቱ አርሶአደሮችን በአካባቢ ስፔሻላይዜሽን እንዲሳተፋ የሚያደርግ እንዲሁም የገበያ፣ የመሠረተ ልማትና ሎጅስቲክስ አቅርቦት ማነቆ እንዳይሆን የሚያግዝ ሆኗል።

 

የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራ በቂ እርጥበት ባለበት ሁኔታ እንዲካሄድ ለማድረግ የጀመርነውን የተፈጥሮ ሃብትና የተፋሰስ ልማት ስራ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ እንዲሸጋገሩ እየተደረገ ነው። የውሃ አጠቃቀማችንን በማሻሻልና የመስኖ ሥራ እንደ የአግሮ ኢኮሎጅው ሁኔታ በማካሄድ ምርታማነቱን በማረጋገጥና የግብርና ልማት ዘላቂነትን በማረጋገጥ መስራት ይገባል።

ይህ ስራ የደን ልማት ተግባሮችን በማጐልበት ለአካባቢ ተፅዕኖ የማይበገር የግብርና ልማት ወይም ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለማካሄድ የሚያስችል ነው። በአርሶአደር አቅም የሚሠራው የመስኖ ልማት በማጠናከር በትራንስፎርሜሽንና ዘላቂ ልማት ዕቅድ ዘመን ከ4 ሚልዮን ሄክታር በላይ መሬት እንዲለማ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው። በተጓዳኝ በክልልና በፌዴራል መንግሥት ደረጃ የሚሠሩ አነስተኛና መካከለኛ የመስኖ ልማትና ግድብ መጠናከር ይኖርባቸዋል። በተግራይ ክልል ራያ አካባቢ የተገኘው ለውጥ በዚህ መነሻነት በተከናወነ የመስኖ ስራ በመሆኑ ሌሎች ክልሎችም በተሞክሮነት ሊወስዱት የሚገባ ይመስለኛል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy