NEWS

ሳዑዲ አረቢያ ከሙስና ጋር ተያይዞ እየፈፀመች ያለችው እስር የዘመቻዋ ጅማሬ ነው

By Admin

November 07, 2017

ሳዑዲ አረቢያ ከሙስና ጋር ተያይዞ በንጉሳውያን ቤተሰብ አባላት፣ ሚኒስትሮች እና ባለሀብቶች የጀመረችው እስር የፀረ ሙስና ዘመቻዋ ጅማሬ መሆኑን ገለፀች።

የአገሪቱ አቃቤ ህግ ሼክ ሳዑድ አል ሞጄብ በሰጡት መግለጫ ድርጊቱን “ሙስናን ከያለበት ለመንቀል የሂደቱ ወሳኝ ጅማሬ ነው” ሲሉ ገልፀዋል።

በልዑሉ የሚመራው 32 አባላት የያዘ አዲስ በተቋቋመው የፀረ-ሙስና ኮሚቴ፥ እስከ አሁን ባለው ሂደት 11 የንጉሳውያን ቤተሰብ አባላት፣ አራት ሚኒስቴሮችን እና በርካታ የቀድሞ የሚኒስትር አመራሮች እንዲሁም ባለሀብቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገልጿል።

አዲስ የተቋቋመው የፀረ-ሙስና ኮሚቴ ኃላፊነትም በሙስና ክስ ጉዳዮች ላይ የተደረጉት ምርመራዎች ሙስና የተፈፀመባቸው የተለያዩ ዘርፎች መለየታቸውን ጠቁመዋል።

አገሪቱ በተጨማሪም ከሙስና ጋር በተያያዘ ከአገር እንዳይወጡ እና የባንክ ሂሳባቸው እንዳይንቀሰቀስ የሚታገዱ ሰዎች ዝርዝርንም እያዘጋጀች መሆኑ ነው የተመለከተው።

ባንኮችም የተጠርጣሪዎች የባንክ ሂሳብ እንዳይንቀሳቀስ ማገድ ጀምረዋል።