Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በእንቦጭ አረም የፈጠራው ስራ !!

0 401

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በእንቦጭ አረም የፈጠራው ስራ !!

ዋኘው መዝገቡ  

የእንቦጭ አረምን ከጣና ሀይቅ ላይ ለማጥፋት ሕዝባዊ ርብርብ እየተደረገ ነው። ይህ ርብርብ ክልል ሳይወስነው  ሁሉንም ዜጎች ያነሳሳ ነው። ዜጎች ከተለያዩ ማእዘናት ያንቀሳቀሰና ያሳተፈ በመሆኑ የዜጎችን ሕዝባዊ አንድነት የበለጠ ማጉላት አስችሏል። እምቦጭ አረሙን ለማረምና ለማጥፋት በባህላዊ መንገድ በእጅ ከመልቀም በተጨማሪ በፈጠራና ምርምር ስራ ለማገዝ እየተሰራ ነው። የጎንደርና የባር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ ረገድ ተጨባጭ ፈጠራ አበርክተዋል።

በእንቦጭ አረም  የተጋረጠብን አደጋ ለግዜው በጣና ሀይቅ ላይ ቢታይም ችግሩ በሌሎች ሐይቆቻችንም ላይ ሊከሰት እንደሚችል ምሁራን እየገለጹ ነው። የህዳሴውም ግድብ ከለዚህ ችግር ተጋላጭ መሆኑ ከወዲሁ እየተነገረ ነው። አረሙን በማስወገድ በሕልውናችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ መክላት ኃላፊነቱ የኢትዮጵያውያን ብቻ ነው። ግዜ የሚሰጠውም ጉዳይ እንዳልሆነም መታወቅ አለበት።

በዚህ ረገድ ቀደም ሲል እንደተገለጸው እምቦጭ አረሙን ነቅሎና አጭዶ ለማስወገድ የሚችል ሀገር በቀል መሳሪያ በጎንደር ዩኒቨርስቲና በባሕርዳርም ተሰርቶአል። በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተሰራው  ማሽን በጣና ኃይቅ ላይ እንዲሰማራ ተደርጎ ስራውን እየሰራ ይገኛል። መጀመሪያ ላይ ማሽኑ ግዙፍ ስለሆነ ለማጓጓዝም የሚከብድ የነበረ ሲሆን በስፍራው ላይ ተጭኖ እንዲደርስ ተደርጎ ስራውን ጀምሮአል።

ይሄ በሀገር ልጆች የተሰራ የፈጠራና የምርምር ስራ እንደ ዜጋ እንደ ሀገር በእጅጉ የሚያኮራን ነው። በቀጣይ የሚኖረው ሂደት ማሽኑ ከመጀመሪያው ልምድና ተሞክሮ በመነሳት የበለጠ እየተሻሻለ ስራዎችን በፍጥነትና በቅልጥፍና የሚሰራበት መንገድ እየታየ ሊሻሻል ይችላል። ይሄ በስራው ሂደት ውስጥ የሚፈተሸ ነው። ማንኛውም የፈጠራ ውጤት በሂደት በሚደረግበት ፍተሻ እየተሻሻለ እንደሚሄድ ይታወቃል። ። በዚህ መልኩ ቀጣይ የመለወጥ የማዘመን ስራዎቹ ይቀጥላሉ ማለት ነው። የእምቦጭ አረምን ለማጥፋትና ለማስወገድ የራሳችን ዜጎች ሰርተው ወደስራ ያስገቡት ማሽን ለሀገራዊ ችግር ሀገራዊ መፍትሔ የበለጠና የተሻለ አማራጭ መሆኑን ያሳየ ነው።

ሌሎች ችግሮቻችንን የሚፈቱ የራሳችን ምሁራን የፈጠራ ስራ የሆኑ ማሽኖችም በተለያየ ዘርፍ ተሰርተው የምናይበት ግዜ ሩቅ አይሆንም። ምርምሩና የፈጠራ ስራው ለሀገር መድሕንና ትንሳኤ ሆኖ ሀገራችን በሳይንስና ምርምሩም መስክ ከፍተኛ ድሎችን በወጣቶችዋ እንደምታስመዘግብ እምነታችን የገዘፈ ነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy