Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አማራጭ የሌለው መፍትሔ

0 421

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አማራጭ የሌለው መፍትሔ

ዳዊት ምትኩ

ከአገራችን ተጨባጭ የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ሁኔታዎች አኳያ ከፌዴራሊዝም ውጭ ሌላ አማራጭ ሥርዓት የለም። ያለፉት ስርዓቶች ህዝቡን በሃይልና በአፈና በመያዛቸው ሳቢያ የነበረውን ምስቅልቅል ሁኔታ ሁላችንም የምንገነዘበው ነው።

እነዚያ ስርዓቶችን በህዝቦች ይሁንታ ላይ የተመሰረተ ስርዓትን ሳይሆን፤ ገዥዎች በራሳቸው ፈቃድ እንዳሻቸው የሚያደርጓት፣ አንዳንዶም “ስዩመ እግዚሐብሔር” እያሉ የህዝቦችን መብት በመለኮታዊ ሃይል ሽፋን እየገሰሱ እንደነበር ይታወቃል። ደርግ ደግሞ ስልጣኑን ለማስጠጠበቅ የመላው የሀገራችንን ህዝቦች የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ፍላጎቶችን ስሙን እየቀያየረ ሲደፍቅ ነበር። እነዚህ ሁሉ ችግሮች በህዝቦች የጋራ መራር ትግል ዳግም ላይመለሱ ዶሴያቸው ተዘግቷል።

እናም አዲሲቷ ኢትዮጵያ በአስተማማኝነት ማሰፈን ከምትፈልገው ሰላም፣ አውን ለማድረግ ከምትሻው የልማት ዕቅድና እንዲገነባ ከምትፈልገው የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አኳያ ፌዴራሊዝም አማራጭ የሌለው መፍትሔ ሊሆን ችሏል። ሥርዓቱ የሚከተላቸው እነዚህ የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ መንገዶች የአገራችንን ህዳሴ የሚያሳካና የህዝቦችን ጥያቄዎች እየመለሰ በመሆኑም ተኪ የማይገኝለት እንዲሆን አድርጎታል።

ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር፣ የሚፈልጉትን ኃይማኖት የመከተል፣ በቋንቋቸው የመናገር እና የመጻፍ፣ ባህላቸውን እና እሴቶቻቸውን በነጻነት የመግለፅ መብቶቻቸን እንዲጎናፀፉ አድርጓቸዋል። እርግጥም የኢትዮጵያ ህዝቦች የዘመናት ትግል መንስዔም እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ በመሆኑ ይህ ውጤት ከተገኘ 26 ዓመታት እየሆነ ነው።

የአገራችን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ህገ- መንግሥቱን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በገዛ ፈቃዳቸው ተስማምተው እና ተማምነው እንዲያፀድቁት የተጫውተው ሚና የላቀ መሆኑ በተግባር ታይቷል።

እርግጥ የኢትዮጵያ ባህል፣ ቋንቋ እና ታሪክ ማለት የኢትዮጵያ ህዝቦች ባህሎች፣ ቋንቋዎች እና ታሪኮች ተደምረው የሚፈጥሩት ውህደት ነው። ይህ የሀገራችን ነባራዊ ክስተትን በልዩነት ውስጥ ባለ አንድነት ሊያስተናግድ የሚችለው በፌዴራሊዝም ሥርዓት ውስጥ ነው። ለኢትዮጵያ ብቸኛው አማራጭ ፌዴራላዊ ሥርዓትን መከተል መሆኑን የሥርዓቱ ባለቤቶች የሆኑት የሀገራችብን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በፅናት አምነውበት እንዲተገበር የፈለጉትም ለዚሁ ነው።

ፌዴራሊዝም ለግጭቶች ቦታ የለውም። ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር፣ የሚፈልጉትን ኃይማኖት የመከተል፣ በቋንቋቸው የመናገር እና የመጻፍ፣ ባህላቸውን እና እሴቶቻቸውን በነጻነት የመግለፅ መብቶቻቸን እንዲጎናፀፉ አድርጓቸዋል። እርግጥም የኢትዮጵያ ህዝቦች የዘመናት ትግል መንስዔም እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ በመሆኑ ይህ ውጤት ከተገኘ 26 ዓመታት እየሆነ ነው።

የአገራችን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ህገ- መንግሥቱን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በገዛ ፈቃዳቸው ተስማምተው እና ተማምነው እንዲያፀድቁት የተጫውተው ሚና የላቀ መሆኑ በተግባር ታይቷል። እርግጥ የኢትዮጵያ ባህል፣ ቋንቋ እና ታሪክ ማለት የኢትዮጵያ ህዝቦች ባህሎች፣ ቋንቋዎች እና ታሪኮች ተደምረው የሚፈጥሩት ውህደት ነው። ይህ የሀገራችን ነባራዊ ክስተትን በልዩነት ውስጥ ባለ አንድነት ሊያስተናግድ የሚችለው በፌዴራሊዝም ሥርዓት ውስጥ ነው። ለዚህም ይመስለኛል— ለኢትዮጵያ ብቸኛው አማራጭ ፌዴራላዊ ሥርዓትን መከተል መሆኑን የሥርዓቱ ባለቤቶች የሆኑት የሀገራችብን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በፅናት አምነውበት እንዲተገበር የወሰኑት።

ያም ሆኖ

 

ቀደም ሲል የነበሩት አምባገነናዊና ፊውዳላዊ ሥርዓቶች በህዝቦች መካከል የፈጠሩት የተዛባ ግንኙነቶች እንዲሁም የተፈጥሮ ሃብት እጥረቶች በአንዳንድ አካባቢዎች ለሚታዮ ግጭቶች መንስኤ እየሆኑ መምጣታቸው አይካድም። እንዲሁም የመልካም አስተዳደር እጦትና የኪራይ ሰብሳቢዎች ሴራ የግጭት መንስኤዎች እየሆኑ ነው።

በየትኛውም ማኅበረሰብ ውስጥ ግጭት መቼም ቢሆን ሊጠፋ የማይችል ነባራዊ ሁኔታ ነው። እንኳንስ የህዝቦች ንቃተ ህሊና እየተገነባ እና ይበል የሚያሰኝ ደረጃ ላይ እየደረሰ ባለበት በእኛ ሀገር ውስጥ ቀርቶ፤ በሥልጣኔ በገፉ ሌሎች ሀገሮች ውስጥም ቢሆን ግጭት መኖሩ ነባራዊ ክሰተት ነው። በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ የሚመላለሰው የሰው ልጅ ቀርቶ ህይወት የሌላቸው ግዑዛን ነገሮችም በተፈጥሮ እንቅስቃሴ ሳቢያ ሊጋጩ ይችላሉ።  

እርግጥ ከሰው ልጅ ግጭቶች አኳያ በዓለማችን ላይ የተፈጥሮ ሀብት እጥረት መኖሩ እንደ መንስዔ የሚታይ ነው። አገራችንም ከዚህ የተፈጥሮ ዕውነታ ልትርቅ አትችልም። በመሆኑም ግጭት ትናንትም ይሁን ዛሬ እንዲሁም ነገ መኖሩ ያለና የሚኖር ጉዳይ ነው።

ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ግን ካለፉት ጊዜያት ጋር ፈፅሞ በማይገናኝ መልኩ ለዚህ ነባራዊ ችግር ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ ሁኔታውን በመለወጥ ላይ ይገኛል። የአገሪቱ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ያላቸውን የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ እንዲጠቀሙና ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመተሳሰብ የጋራ ሀብታቸው እንዲሆን ማድረግ ችሏል። በአሁኑ ሰዓት ሥርዓቱ አንድነትን በሚያጠናክሩና በሚያፀኑ መሰረቶች ላይ በመመርኮዝ እየሰራ ነው።

ፌዴራላዊ ሥርዓቱ ያለፉ የተዛቡ ግንኙነቶችን ለማረም በሚያደርገው የእኩልነትና የፍትህ ተግባራት በርካታ ውጤቶች ተገኝተዋል። የተዛቡ የህዝቦች ግንኙነቶችን በማስተካከል በሚደረጉ የፍትህና የእኩልነት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያለፉትን ስርዓቶች በመናፈቅ አሊያም በዚያኛው ዓይነት ፀረ-ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ሀገራችን እንድትመራ የሚፈልጉ አካላት ግን ይህን ሁኔታ ሊገዳደሩት ይሞክራሉ—ምንም እንኳን ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ለዚህ የሚሆን መፈናፈኛ ባይሰጣቸውም።

በህገ መንግስቱ ላይ እንደሰፈረው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገታችን እንዲፋጠን ለማድረግ በነፃ ፍላጎታቸው በህግ የበላይነትና በራሳቸው ፈቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ የመገንባት ዓላማ አላቸው።

መጪው የጋራ ዕድላቸው መመስረት ያለበት ከታሪካቸው የወረሱትን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅማቸውን በማሳደግ ላይ መሆን እንዳለበት የተቀበሉ መሆናቸውን በተደጋጋፊነት በፍትሐዊና ፈጣን ልማት ለማሳደግ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት አስፈላጊ ነው ብለውም ያምናሉ። ምንም እንኳን ያለፉት ስርዓቶች በህዝቦች መካከል የተዛቡ ግንኙነቶችን ፈጥረው ቢያልፉም፣ ዛሬ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ በእኩልነትና በፍትህ ዴሞክራሲያዊ መንገዶች እነዚህ ችግሮች እየተቀረፉ ነው።

ሥርዓቱ በሂደት ራሱን በራሱ እያረመ ለዛሬው የህዝቦች መፈቃቀድና አንድነት መጠናከር ጉልህ ሚና መጫወቱና ፍትህንና እኩልነትን ከማጠናከር አኳያም ረጅም ርቀት ተጉዟል። እርግጥ ሥርዓቱ ራሱን እያረመና እንደ ማንኛውም ጀማሪ የፌዴራል ስርዓት ያሉበትን ችግሮች እየነቀሰ እንዲሁም ካለፉት ክስተቶች እየተማረ በአገሪቱ ህዝቦች በመታገዝ በአስተማማኝ መንገድ ላይ ነው። ለዚህም ነው ሥርዓቱ ተኪ የለውም የሚባለው።

እናም ይህን ተኪ አልባ ሥርዓት አክብሮ ማስከበር ይገባል። ብልሹ አሰራርና ኪራይ ሰብሳቢነት ሊወገዱ ይገባል። እነዚህ የህብረተሰቡን አመኔታ ብሎም ሥርዓቱን የሚገዘግዙ አስተሳሰቦች ካልተቀረፉ የህዝቦችን መሰረታዊ ህይወት በዘላቂነት ለመለወጥ የተያዘውን ግብ ለማሳካት እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ።

ሥርዓቱ ቀደም ሲል በአገራችን ህዝቦች ላይ ተንሰራፍቶ የነበረውን የጭቆና ቀንበር ላይመለስ የጣለ ነው። የነፃነት መብቶችን ለመላው የአገሪቱ ዜጎች ሰጥቷል። ሁሉም ዜጋ እንደ አቅሙ ንብረት በማፍራት ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጓል። ሥርዓቱ ህዝቦች የሚፈልጉትን ሁሉ እንዲሆኑ ያስቻለ ነው። ይህ የህዝቦች በሁሉም መስኮች ተጠቃሚነት ከአቅም በላይ ባልሆኑ ሰንካላ ምክንያቶች እንደማይደናቀፍ የሚታወቅ ቢሆንም ህብረተሰቡም ለዚህ ምትክ አልባ ሥርዓት የበኩሉን ማድረግ ይኖርበታል።    

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy