Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አሸባሪነትን መከላከል የሁሌም ተግባራችን ይሁን!

0 304

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አሸባሪነትን መከላከል የሁሌም ተግባራችን ይሁን!

                                                        ደስታ ኃይሉ

የአይኤስ አባል በመሆን አገራችን ውስጥ የተለያዩ ጥቃቶችን ሊያደርሱ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለው በፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰጥቷቸዋል። ይህም አገራችን አሸባሪዎችን እንደማትታገስ የሚያሳይ ውሳኔ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ የአሸባሪዎች ሴል በመሆን መንቀሳቀስ እንደማይቻልም ያረጋገጠ ክስተት ነው።

ያም ሆኖ ከአሸባሪዎቹ ተግባር አንድ እወነታን መረዳት ይቻላል። ይኸውም የአሸባሪነት ተግባር ዛሬም ቸል ሊባል የማይገባው ድርጊት መሆኑን የሚያመላክት ነው። የአሸባሪነት ተግባር ዘር፣ ሃይማኖር፣ ቀለም፣ የትምህረት ደረጃና የኑሮ ሁኔታን…ወዘተ. የማይለይ ዘግናኝ ድርጊት ነው።

የሽብርተኝነት አደጋ የትም ሀገር ውስጥ እንዳለው ሁሉ፤ እኛም ሀገር ውስጥ ሊኖር አይችልም ብሎ መደምደም አይቻልም። ፍርድ ቤት ቀርበው ውሳኔ የተሰጣቸው የአይኤስ ጀዌዎች ማሳያዎች ይመስሉኛል። እንዲሁም በተለያዩ ወቅቶች ፍርድ ቤት የሚቀርቡና የእነ ኦነግን፣ ግንቦት ሰባትንና ኦብነግን የመሳሰሉ አሸባሪዎችንና ፀረ-ሰላም ሃይሎችን ዓላማ አንግበው በሰላም ወዳዶቹ ህዝባችንና በፀጥታ ሃይሎች ትብብር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በዋቢነት ማንሳት ይቻላል። እናም ጉዳዩን ከቀጠናውና ከሀገራችን አኳያ መመልከቱ ለአንባቢያን ግንዛቤ የሚሰጥ ነው።

እርግጥ ሽብርተኝነት በልማትና በሰላም ላይ የሚያንዣብብ አደጋ በንፁሃን ዜጎች ህይወት ጥፋት ላይ የሚያነጣጥር የፈሪ ዱላ ነው፡፡ ታዲያ የጅምላ ጥፋትን የሚያስከትለው ይህ የጥፋት መንገድ ምንም እንኳን የትኛውንም ሀገር ለችግር የመዳረግ ብቃት ያለው ቢሆንም፤ ችግሩ የሚከፋው ከድህነትና ከኋላቀርነት ለመላቀቅ ደፋ ቀና እያሉ በሚገኙ ሀገሮች ላይ መሆኑ የሚያሳስብ አድርጎታል። እንደሚታወቀው የአፍሪካ ቀንድ ለዚህ ችግር የተጋለጠና የሽብር ጥቃት ስለባ ከሆነ አመታት ተቆጥረዋል።

በእርግጥ ችግሩን ከቀጠናው አገራት ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት በሁለት ክፍሎ ማየት ጠቃሚነት የጎላ ነው። በምስራቅ አፍሪካ በአንድ በኩል የሽብር ጥቃት ሰለባ የሆኑ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አሻበሪነትን በማስፋፋት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው ሀገሮችን እናገኛለን፡፡

ከዚህ አኳያም ከድህነትና ኋላቀርነት የመውጣት ዓላማን አንግበው ለስኬታማነቱ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ለሚገኙት የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት፣ በተለይም ለፈጣን ልማት ቀጣይነት በመረባረብ ላይ የምትገኘው ሀገራችን ሽብርተኝነት በተለያዩ ጊዜያት ተፈታትኗታል። ሊያንበረክካት ግን አልቻለም፡፡ ይህ ውጤት የተገኘው ደግሞ ለተግባሩ መስፋፋት ምቹ ሁኔታ የማይፈጥሩት ህዝባችንና መንግስት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት መሆኑ እሙን ነው።

በአገራችን ላይ የተደቀነውን ሽብርተኝነት በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። የመጀመሪያው በኤርትራ መንግስት የሚደገፉ፣ የሽብር ተግባሩን ለማሳካት የሚሰማሩ ብሎም የተላላኪነት ሚናቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙ አሸባሪዎችና ፀረ-ሠላም ኃይሎች ናቸው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የምስራቅ አፍሪካው የአል ቃዒዳ ክንፍ የሆነው አል ሸባብ እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአይአኤስ ሴል በመሆን የትንቀሳቀሱ ሃይሎችን (በፍርድ ቤ ውሳኔ ያገኙ) መመልከት ይቻላል።

አሸባሪዎችንና ፀረ ሰላም ሃይሎችን የማደራጀት፣ የማሰልጠን፣ የማስታጠቅና የማሰማራት አባዜ የተጠናወተው የኤርትራ መንግስት፤ በተለይም ራሳቸውን ኦነግ፣ ግንቦት ሰባትና ኦብነግ እያሉ የሚጠሩ አሸባሪ ቡድኖችን ወደ ሀገራችን አሰርጎ በማስገባት የሠላም፣ የልማትና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደቶችን ለማደናቀፍ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፤ ዛሬም ድረስ ከድርጊቱ አልተቆጠበም።

በሀገራችን ላይ ከተቃጡት የሽብር ጥቃቶች መካከል፣ በመዲናችን አዲስ አበባ በትግራይ ሆቴል፣ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላየ የደረሰውን የሽብር ድርጊት የፈጸመው የአስመራው መንግስት ተላላኪው ኦነግን እናገኛለን፡፡ አሸባሪው ኦነግ በፈሪ ዱላው የንጹሃን ዜጎችን ህይወት የመቅጠፍ እኩይ ተግባር በዚህ ብቻ ሳይወሰን፤ በባቡር ትራንስፖርት፣ የተለያዩ መሰረተ ልማት ተቋማትን በማውደም ጭምር ድብቅ አጀንዳውን ለማስፈጸም፣ በዜጎች ላይ ፍርሃትና ውዠንብር ለማንገስ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፤ ስኬቱ ያልተሳካና የማይሳካ ቢሆንበትም።

ሽብርተኛው ኦነግ የታጠቀ ኃይሉን አሰርጎ በማስገባት ሀገራችን ከድህትና ከኋላቀርነት ለመላቀቅ የምታደርገውን ትግል ለማኮላሸት የተለያየ ጥረት ቢያደርግም፤ በተለያዩ ጊዜያት ከፍተኛ ወድመት የሚያስከትሉ ጥቃቶች ለመሰንዘር ያካሄዳቸው ሙከራዎቹ ግን ለፍሬ ሳይበቁ ተጨናግፈዋል፡፡ ይህ ደግሞ በሽብር ተግባር ላይ ተሰማርተው ዓላማቸውን ሳያሳኩ በሠላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ጥረት ለፍርድ ከቀረቡ የአሸባሪው ቡድን አባላት አማካኝነት የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡

ራሱን “አርበኞች ግንቦት ሰባት” እያለ የሚጠራው የሽብር ቡድን ዕጣ ፈንታም ከዚህ የተለየ አይደለም። ታዲያ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ልማትና ሠላም የቆመ ሃይል በማስመሰል በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የሚደሰኩረው አሸባሪው ግንቦት ሰባት፤ ተለዕኮውን ለመቀበል ጥቂት እንኳን አላቅማማም። ይህም ባንዳነቱን ያረጋገጠ ክስተት ሆኖ አልፏል። ያመጣው አንዳችም ለውጥ ግን የለም።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልማትን ለማደናቀፍ የተላላኪነቱን ሚና ከተረከቡት መካከል አሸባሪው ኦብነግ ይጠቀሳል። ኦብነግ ከሻዕቢያና ከሌሎች የሀገራችንን ልማት ከማይሹ ሀገሮች ተልዕኮን እየተቀበለ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልማትን የማደናቀፍ ስራን አንግቦ የአፍራሽነት ሚናውን ሲወጣ ቆይቷል። ግን በክለሉ ህዝብና በፀጥታ ሃይሎች ትብብር ፍላጎቱ ከንቱ ሆኖ ቀርቷል።

በተለይም ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ለፖለቲካ መጠቀሚያነት፣ ለስልጣን መቆናጠጫነት ተግባር ከመረጡ ሃይሎች ባሻገር፤ ዓላማቸውን ለማሳካት የተለያዩ ፀረ ህገ መንግስታዊ ስልቶችን ለመጠቀም ሞክረው ያልተሳካላቸውና በተስፋ መቁረጥ የሚወራጩት አሸባሪ ቡድኖችም እየተስተዋሉ ነው።

በቅርቡ በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰጣቸው የአይኤስ አባላትና የምስራቅ አፍሪካው የአልቃዒዳ ክንፍ የሆነው አል-ሸባብ በአዚህ ረገድ ተጠቃሽ ናቸው። ታዲያ እነዚህን የሽብር ቡድኖች መላው የአገራችን ህዝቦች ሊኮንኗቸው ይገባል። በተለይ የአይኤስ አባላት እዚህ አገር ውስጥ የሽብርተኝነት ተግባር ለመፈፀም መሞከራቸው አሸባሪነትን መከላከል የሁሌም ተግባር መሆን እንዳለበት የሚያመላክት እውነታ ይመስለኛል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy