Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኦሮሞና አማራ ህዝቦች የትስስር መድረክ ተሳታፊዎች ወደ ባህር ዳር እያቀኑ ነው

0 492

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኦሮሞና አማራ ህዝቦች ትስስር መድረክ ተሳታፊዎች ወደ ባህር ዳር ከተማ በማቅናት ላይ ናቸው።

የኦሮሞና አማራ ህዝቦች ትስስር መድረክ ኮንፈረንስ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል።

የሁለቱ ክልሎች የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊዎች አቶ ንጉሱ ጥላሁን እና አቶ አዲሱ አረጋ የምክክር መድረኩን ዓላማና ያለውን ፋይዳ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም የምክክር መድረኩ “አብሮነታችን ለሰላማችን፤ ሰላማችን ለአብሮነታችን!” በሚል መሪ መልዕክት እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

nigusu_addissu.jpg

በኮንፍረንሉ ላይ ለመካፈልም ከ20 የኦሮሚያ ዞኖችና ከ18 ከተሞች የተወጣጡ ከ250 በላይ የሚሆኑ የኦሮሞ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ምሁራን እና አርቲስቶች ዛሬ ማለዳ ወደ ባህር ዳር ከተማ ጉዞ መጀመራቸውን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።

በኮንፍረንሱ የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች አንድነት፣ ለሀገራችን ሰላምና ሉዓላዊነት ስለከፈሉት የጋራ መስዋዕትነትና ስለፈፀሙት አኩሪ ገድሎች ተነስተው ውይይት እንደሚደረግባቸውም ገልፀዋል።

እንዲሁም የሁለቱን ህዝቦች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኦኮኖሚያዊ መስተጋብር የሚያሳዩ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ እቅጣጫዎችን የሚያመላክቱ የውይይት መነሻ ፅሁፎች በምሁራን ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸውም አቶ አዲሱ አብራርተዋል።

ኮንፍረንሱን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ እና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋችዉ በጋራ ይመሩታል ተብሎ ይጠበቃል።

one_love_2.jpg

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በበኩላቸው፥ የአማራ ህዝብ በኮንስረፍሱ ላይ ለመካፈል ከኦሮሚያ ክልል የሚመጡ እንግዶችን የአባይ ድልድይ ላይ ለመቀበል ዝግጁ ሆኖ በመጠባበቅ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።

በፍኖተ ሰላም፣ በእንጀባራ እና በባህር ዳር ከተሞችም ለእንግዶቹ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አቶ አዲሱ፥ የክልሉ መንግስት ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ጋር የህዝቦችን ወንድማማችነት እና አንድነት ሊያጠናክሩ የሚችሉ ቀጣይነት ያላችው ኮንፈረንሶች እንደሚያዘጋጅ አስታውቀዋል።

በዚህም የሀገሪቱ ህዝቦች ትስስር፣ ሰላም እና አንድነት ብሎም ለዘመናት የቆየውን የህዝቦችን መስተጋብር በማጠናከር ረገድ የበኩሉን በጎ አስተዋፅኦ ማበርከት የሚያስችሉ ስራዎችን አቅዶ በመስራት ላይ ይገኛልም ነው ያሉት።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy