Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

400 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘው የታክስ ኦዲተር ክስ ተመሰረተበት

0 759

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

400 ሽህ ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘዉ የታክስ ኦዲተር ክስ ተመሰረተበት።

ክሱ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ነዉ የቀረበው።

ተከሳሹ አቶ ገመቹ አያኖ የሚባል ሲሆን፥ በኢትዮጵያ ገቢዎች እና ጉሙሩክ ባለስልጣን የአዲስ አበባ መካከለኛ ግብር ከፋይ ቁጥር ሁለት የታክስ ኦዲተር ባለሙያ ነው።

 

የጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ፥ ተከሳሹ የ2004 እና 2005 ዓ.ም ግብርን ኦዲት በማድረግ ከግብር ከፋዩ አቶ አበበ ሙልጌታ ጋር በመደወል ውዝፍ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ግብር እንዳለባቸውና ግብሩን ካልከፈሉ እስከ 10 ሚሊየን ብር የሚደርስ ገቢ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መናገሩን ያመለክታል።1 ሚሊየን ብር ለእሱ ከሰጡት ግን ውዝፍ ግብራቸውን 1 ሚሊየን ብር እንደሚያደርግላቸው መግለጹም በክሱ ተዘርዝሯል።

በዚህም መሰረት በአዲስ አበባ ብስራተ ገብርኤል እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም ምሽት 12 ሰዓት ከ35 ዲቃ ላይ ከግለሰቡ ተሽከርካሪ 400 ሺህ ብር በፌስታል ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዞ በቁጥጥር ስር መዋሉም በክሱ ተብራርቷል።

ተከሳሹ አቶ ገመቹ አያኖ ላይም በጉቦ መቀበል ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል።

አቃቤ ህግም ለወንጀሉ መፈፀም ያስረዳልኛል ያለውን የስው ምስክር ዝርዝር እና የሰነድ ማስረጃዎችንም ከክሱ ጋር አያይዞ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

ተከሳሹም ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱ የተነበበለት ሲሆን፥ በክሱ ላይ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመስማት ለህዳር 7 ቀን 2010 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰተጥቷል።

ተከሳሹ አቶ ገመቹ አያኖ ወደ አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲወርድም ፍርድ ቤቱ አዟል።

 

 

በታሪክ አዱኛ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy