Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ ሐኪሞች ቡድን በሶማሊያ ህዝብ ዘንድ ጥልቅ የአጋርነት ስሜት ፈጥሯል

0 478

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

 የኢትዮጵያ ሐኪሞች ቡድን ተግባር በሶማሊያ ህዝብ ዘንድ ጥልቅ የአጋርነትና የወዳጅነት ስሜት መፍጠሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተናገሩ።

ዜጎች በተሰማሩበት የሙያ መስክ ለአገር ገጽታ ግንባታ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሶማሊያ በደረሰው የሽብር ጥቃት ለተጎዱ ወገኖች በስፍራው ተገኝተው የህክምና አገልግሎት ለሰጡ የኢትዮጵያ ሃኪሞች የልዑካን ቡድን አባላት ዛሬ ምስጋናና እውቅና ስጥቷል።

በቅርቡ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የደረሰው ጥቃት ከ360 በላይ ሰዎችን ህይወት ሲያጠፋ በርካቶችን ለአካል ጉዳት መዳረጉ ይታወሳል።

በአደጋው በደረሰው ጉዳት ድጋፍ ለማድረግ ቀድመው አጋርነታቸውን ካሳዩ አገራት መካከል ኢትዮጵያ ተጠቃሽ ስትሆን የሃዘን መግለጫ ከመላክ ባለፈ ሰባት ቶን መድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ለግሳለች።

ዛሬ ምስጋናና ዕውቅና የተሰጠው አራት አባላትን የያዘ የህክምና ባለሙያዎች ቡድንም ወደ ስፍራው ልካለች።

ሚኒስተሩ ዶክተር ወርቅነህ ለቡድኑ በተዘጋጀው የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም ላይ እንዳሉት ልዑኩ ወደ ስፍራው በማቅናቱ የበርካቶችን ህይወት አትርፏል ከአካል ጉዳተኝነትም ታድጓል።

ይህም ወንድማማች በሆኑት በኢትዮጵያና ሶማሊያ ህዝቦች ዘንድ ጥልቅ የአጋርነትና ወዳጅነት ስሜት መፍጠሩን ገልጸዋል።

ከዚህ አንጻር ቡድኑ የተሰጠው ሃላፊነትና የተወጣው ተግባር ምስጋናና እውቅና የሚያሰጠው እንደሆነ ነው የተናገሩት።

ቡድኑ ያከናወነው ተግባር ለሌሎች ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል የጠቀሱት ሚኒስትሩ ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት የሙያ መስክ ለአገሩ አምባሳደር ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የህክምና ቡድኑ ልዑክ መሪ ዶክተር አስቻለው ጌታቸው በበኩላቸው ስራቸው የተሳካ እንደነበር ገልጸዋል።

የተሰጣቸውን ኃላፊነቱ መወጣታቸው ትልቅ የህሊና እርካታ እንደሰጣቸውና ተልእኮውም ልምድ ያገኙበት መሆኑን አክለዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy