Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ለኢኮኖሚ ዕድገቱ ቀጣይነት የግል ዘርፉን ማበረታታት ያስፈልጋል-ክርስቲን ላጋርድ

0 498

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የያዘቻቸውን የልማት ግቦች ውጤታማ ለማድረግ የግሉን ዘርፍ ማበረታታት እንደሚገባት የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ. ኤም. ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስቲን ላጋርድ ገለጹ።

ተቋሙ ለኢትዮጵያ የወጪ ንግድ መዛባት መፍትሄ የሚሆን የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግም ቃል ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙትን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስቲን ላጋርድን ተቀብለው በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል።

ተቋሙ በየዓመቱ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዕድገት የሚገመግም ቡድን በመላክ የሚከታተል ሲሆን፤ ማኔጂንግ ዳይሬክተሯም አገሪቷ  ተከታታይ ዓመታት የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመስገቧን ተከትሎ ለይፋዊ ጉብኝት መምጣታቸው ተነግሯል።

ማኔጂንግ ዳይሬክተሯ ኢትዮጵያ በተለይም በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ትግበራ ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ባለ ሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቧን አድንቀዋል፡፡

በነዚህ ዓመታት በከፍተኛ መጠን ድህነትን መቀነስና ዘላቂ ልማት ማምጣት መቻሏንም አንስተዋል።

አገሪቷ የግሉ ዘርፍ በተለያዩ መስኮች እንዲሰማራ በማበረታታት ለወጣቶች በቂ የስራ ዕድል መፍጠር ላይ ትኩረት ሰጥታ መስራትና የኢኮኖሚ ዕድገቱን ቀጣይነት ማረጋጋጥ  እንዳለባትም አስገንዝበዋል።

 ኢትዮጵያ ባለፉት 70 ዓመታት በተቋሙ አማካኝነት ልዩ የብድርና የቴክኒክ እርዳታ እንዲሁም የውጭ ዕዳ ጫና ቅነሳና ስረዛ ድጋፍ ስታገኝ መቆየቷንም አስታውሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በወጪ ንግዱ ላይ ችግር እያጋጠማት መሆኑን ጠቅሰው፤ የወጪ ንግዱ በሚፈለገው ደረጃ እንዲያድግና ሚዛኑን እንዲጠበቅ ለጀመረቻቸው ስራዎች ተቋሙ ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ተናግረዋል።

በተለይ የታክስ አስተዳደርና አሰባሰብ ስርዓት ላይ ያለውን ክፍተት የሚሞላ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ መስማማታቸውን ነው የሚገልጹት።

እ.አ.አ በ2011 ተቋሙን መምራት የጀመሩት ክርስቲን ላጋርድ በ2016 በድጋሚ ለተጨማሪ አምስት ዓመት ተመርጠው በማኔጂንግ ዳይሬክተርነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy