Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

“መብራት ለሁሉም”— በከፍታው ዘመን

0 612

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

“መብራት ለሁሉም”— በከፍታው ዘመን

ዳዊት ምትኩ

አገራችን “መብራት ለሁሉም” የሚል የልማት ፕሮግራም መንገፏ ይታወቃል። ፕሮግራሙ የአገራችንን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሽግግር በማምጣት ረገድ ወሳኝ ከመሆኑም ባሻገር፤ በ2017 መላው ኢትዮጵያውያንን የመብራት ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የተያዘው ዕቅድ የከፍታ ዘመናችን ማሳያ ነው።

የፕሮግራሙ ፋይዳ የዜጎችን ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ከማረጋገጥ፣ የአገራችንን ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ ከማሸጋገር፣ የዜጎችን የስራ ዕድል እና የስራ ፈጠራ ከማበረታታት እንዲሁም የዜጎችን ጤንነት ከማሻሻልና የተፈጥሮ ሃብታችንን ከውድመት ከማዳን…ወዘተ አኳያ የሚኖረውን ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።

የ“መብራት ለሁሉም” ፕሮግራም ሁሉንም የኢትዮጵያ ገጠቶች በኤሌክትሪክ ብርሃን ለማንቆጥቆጥ ዓላማ ያለው ነው። ይህ ዓላማ አገሪቱ በሁሉም የገጠር አካባቢዎች መብራትን ለማዳረስ ከወጠነችው ከሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የሚቀዳ ነው።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የውሃ ማማ መሆኗ በተደጋጋሚ ተነግሯል፡፡ ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት ኢትዮጵያ የተለያዩ የሃይል አማራጮችን ብትጠቀም በአጠቃላይ ስልሳ ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም አላት፡፡ የውሃ ሃብቷን በመጠቀም ደግሞ አርባ አምስት ሺህ ሜጋ ዋት ማመንጨት ትችላለች፡፡

ኢትዮጵያ ከውሃ ብቻ 45 ሺ ሜጋ ዋት፣ ከነፋስ 10 ሺ ሜጋ ዋት እንዲሁም ከጂአተርማል አምስት ሺ ሜጋ ዋት ሊለማ የሚችል ሀብት አላት፡፡ ይህንን ሀብት አሟጥጦ ለመጠቀም ግን ከምንም በላይ ቆራጥና ብልህነት የታየበት አመራር ግድ ይላል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የራስንም ሀብት ለማልማት ዛሬ የዓለም አቀፍ ልዩ ልዩ ተቋማት ጫና ቀላል የሚባል አይደለምና፡፡ መንግሥት ይህንን ጫናና ተጽዕኖ ተቋቁሞ የኃይል ማመንጫዎችን በስፋት እያሰራ ይገኛል፡፡ የተከዜ ኃይል ማመንጫና ሁለገቡ ጣና በለስም ተጽዕኖን የመቋቋም ብቃት ማሳያዎች ናቸው፡፡

ከዚህ ውስጥ የአባይ ወንዝን በመገደብ ብቻ ሃያ ስምንት ሺህ ሜጋ ዋት ማመንጨት እንደምትችል ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ይህ ሃቅ በአሃዝ ሲሰላም የዓባይ ወንዝ የኤሌክትሪክ ሃይል በማመንጫት ረገድ ሌሎች ወንዞቻችን ከሚያመነጩት ስድሳ ሁለት ከመቶ ይሸፍናል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው— መንግስት የአባይ ወንዝን ቁልፍ የልማታችን አካል በማድረግ ከህዝቡ ጋር በመተሳሳር ለፍፃሜው ያልተቋረጠ ርብርብ በማድረግ ላይ የሚገኘው፡፡

አገራችን ምንም እንኳን ግብርና መር የኢኮኖሚ ፖሊሲ የምትከተልና ውጤታማ መሆኗ የሚታወቅ ቢሆንም ቅሉ፤ ወደ ኢንዱስትሪው መር ኢኮኖሚ መሸጋገሯ የማይቀር ጉዳይ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የኤሌትሪክ ሃይልን የሚጠይቅ ነው፡፡

እናም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየተስተዋለ ከሚታየው ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍሰት ጋር ተያይዞ ለቀጣይነቱ የህዳሴው ግድብ የኤሌትሪክ ሃይል ማመንጫ የሚሰጠው ምላሽ ምን ያህል ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ለመገመት የሚያዳግት አይመስለኝም፡፡

ስለሆነም ወቅታዊውን ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍሰት ከማስቀጠል ባሻገር፤ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለምናደርገው ጉዞ መፋጠን አስተዋጽኦው የላቀ ነው—ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ። ለዚህም ነው ግድቡ ለሀገራዊው የህዳሴ ጉዞ ስኬት ዕድገትን የማስቀጠልና ያለማስቀጠል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ እንደ ሀገር የመቀጠልና ያለመቀጠል የህልውና ጉዳይ መሆኑ ተደጋግሞ የሚገለፀው፡፡

ያም ሆኖ በአገራችን የኤሌክትሪክ ሃይልን ለገጠሩ ጭምር ለማዳረስ በአሁኑ ሰዓት “መብራት ለሁሉም” የሚል ዕቅድ ነድፋለች። ኢትዮጵያ በርካታ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት መዋዕለ ንዋይ አላት። የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች እና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ አውታሮች ግንባታን ፕሮጀክቶችን ገቢራዊ እያደረገች ነው።

የጎደለው ነገር ቢኖር የአገልግሎት አቅርቦት የምንለው የመጨረሻው ግንኙነት ነው፤ የተጠቃሚዎችን እና የመሳሰሉትን የማገናኘቱ ሥራ። በከፍተኛነቱ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም እና ወደ 60 በመቶ የሚሆኑትን ከተሞች እና መንደሮች የሚሸፍን የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ በአገሪቱ ይገኛል። ችግሩ ትክክለኛ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ምጣኔው አነስተኛ መሆኑ ነው። ታዲያ ይህን ችግር ለመቅረፍ መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ነው።

 

በአሁኑ ሰዓት ለውጦች ቢኖሩም የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚያገኙት ኢትዮጵያውያን ቁጥር የሚፈለገውን ያህል ነው ለማለት የሚቻል አይመስለኝም። በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት የኤሌክትሪክ ኃይል ፈላጊ ዜጎቹን ከአገልግሎቱ ለማገናኘት ያቀደ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ለሰባት አመታት ተግባራዊ የሚሆነው እቅድ የዓለም ባንክ ለአገሪቱ በሰጠው ብድር የሚሰራ ሲሆን “መብራት ለሁሉም” የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል። እቅዱን ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ ውኃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ነው።

“መብራት ለሁሉም” በኢትዮጵያ ብሔራዊ የኤሌክትሪክፍኬሽን አቅርቦት ፕሮግራም ነው። የዚህ ፕሮግራም አላማ ሁሉም የአገሪቱ ክልሎች በቂ፣ አስተማማኝ አቅምን ያገናዘበ ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት አቅርቦት እንዲኖረው ለማድረግ ተብሎ የተነደፈ ፕሮግራም ነው።

ፕሮግራሙ በመላ አገሪቱ የሚገኙትን ሁሉንም ዜጎች ከብሔራዊ የኤሌክትሪክ ቋት እና ከብሔራዊ የኤሌክትሪክ ቋት ውጪ ያሉትን የሕብረተሰብ ክፍሎች ሁሉንም ተጠቃሚ ያደርጋል።

የዓለም ባንክ ባለሙያው እንደሚሉት በኃይል ማመንጫ መሰረተ-ልማቶች ላይ ብቻ አተኩሮ የቆየው የኢትዮጵያ መንግሥት አዲሱ እቅድ የትኩረት ለውጥ ያደረገበት ነው። በተለይም በኤሌክትሪክ ቋት እና በደንበኞች መካከል ያለውን ክፍተት ማጥበብ ቀዳሚው የፕሮግራሙ ትኩረት ነው። ለእቅዱ ስኬታማነት በአምስት ዓመታት ውስጥ ወደ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል።

መረጃዎች እንደሚያስረዱት በመጀመሪያው አምስት አመት ወደ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ይገመታል። በአሁኑ ወቅት በየአመቱ ከብሔራዊው የኤሌክትሪክ ቋት ጋር ግንኙነት የሚፈጠርላቸው ሰዎች 52 ሺህ ናቸው። ይህን ቁጥር በሚቀጥሉት አምስት አመታት እስከ አንድ ሚሊዮን ድረስ ማሳደግ ይጠይቃል።

ለአምስት ዓመቱ ከሚያስፈልገው አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዩን ብር ውስጥ የዓለም ባንክ 375 ሚሊዮን ዶላር ለማቅረብ ተስማምቷል። የቀረው ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ከተጠቃሚዎች የግንኙነት ክፍያ የሚፈፀም ነው። ይህ እቅድ በስራ ላይ ውሎ የሚያስፈልገው የፋይናንስ ግብዓት ከተገኘ መብራትን ለሁሉም ለማዳረስ የሚከብድ አይደለም።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy