Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሰላምና የህብረተሰቡ የባለቤትነት መንፈስ

0 635

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሰላምና የህብረተሰቡ የባለቤትነት መንፈስ

ዳዊት ምትኩ

የሰላምን ለእኛ አገር ሰው መንገር ለቀባሪው የማርዳት ያህል ነው። የኢትዮጰያ ህዝብ ትናንትም ይሁን ዛሬ ስለ ሰላም በሚገባ የሚያውቅ ነው። ይሁንና እዚህና እዚያ የሚረጩት አሉባልታዎች የህብረተሰቡን ሰላም ሲያናጉት ይስተዋላል። ታዲያ ዛሬም የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ ረገድ ህብረተሰቡ የባለቤትነት ስሜት ይበልጥ ማዳበር አለበት።

በተለይም በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ያለውን ችግር ለመፍታትም ህብረተሰቡ ወሳኝ ሃይል መሆኑ አይካድም። በሁለም አካባቢዎች የፀጥታ ሃይልን ብቻ በማሰማራት ውጤት ማግኘት አይቻልም። ከዚህ ይልቅ ህብረተሰቡ የየአካባቢውን ሰላም በዋነኛነት መጠበቅ ይኖርበታል።

ዘላቂ መፍትሔ ሊሆን የሚችችለውም ይኸው ነው። ታዲያ ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ በሁሉም አካባቢዎች ተጠያቂነት መንገሱ እንደማይቀርና ችግሮችን በመፍጠርና በማወሳሰብ የተሳተፉ አካላት ሁሉ ተጠያቂ መሆናቸው እንደማይቀር ህብረተሰቡ መገንዘብ ያለበት ይመስለኛል።

ህዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታው የሚወሰነው ሀገራችን በምትከተለው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ መሆኑን ስለሚያውቅ ሁሌም ሰላም ወዳድ ኃይሎች ጋር የሚቆም ነው። የሰላምን ጠቀሜታ ስለሚገነዘብም ከምንግዜውም በላይ ሁሌም በየአካባቢው ለሰላሙ  ዘብ እንደቆመ ነው።

ህዝቡ በየቀየው ላለው የሰላም ሁኔታ ዋነኛ መሰረት ነው። በዚያ አካባቢ ለሚከሰት ማናቸው የፀረ-ሰላም ድርጊት መልሶ የሚጎዳው እርሱን በመሆኑ ለሰላሙ ይበልጥ መትጋት አለበት።

እንዲህ ዓይነቱ ሰላምን የሚያጎሉ፣ ልማትን የሚያፋጥኑና ንትርክን የሚያስቀሩ መንገዶችን መከተል ባይቻል ኖሮ፤ የመጀመሪያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን እውን ማድረግና ህዝቡም የተጀመረውን የፀረ ድህነት ዘመቻ አጠናክሮ ባልቀጠለ ነበር።

ከልማት ዕቅዱም በየደረጃው ተጠቃሚ ሆኖ ተፈላጊውን የዕድገት ራዕይ ሰንቆ ባልተጓዘም ነበር። አሁን እያለመ ላለውና ከመጀመሪያው ዕቅድ ጋር ተመጋጋቢ የሆነውን ሁለተኛውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድንም ባላለመ ነበር።

በዚህ ደረጃ ላይ ሆኖ የተጀመረውን ዕድገት ለማስቀጠልና በዚያውም ልክ ዴሞክራሲው ሀገር በቀል ፍላጎትን መሰረት ባደረገ መልኩ እንዲጎለብት የተደረገው ጥረት፤ እንዳለ ሆኖ ይህ ህዝብ በአንዳንድ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች ውስጥ ከመልካም አስተዳድር ጋር እንዲሁም ፅንፈኛ ኃይሎችና የሀገራችንን መለወጥ የማይሹ አንዳንድ ወገኖች አማካኝነት የተከሰተውን ሁከት ለመቋቋም ህዝቡ በባለቤትነት መንፈስ የከፈለው መስዕዋትነት በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ይህ የህዝቡ ስሜት የመነጨው ከምንም ተነስቶ አይደለም። የሰላምን ዋጋ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነው። ካለፉት ተግባሮቹ ስለተማረ ነው።

ከተግባር የበለጠ ትምህርት ቤት ባለመኖሩም፤ ይህ ህዝብ የሰላሙ ዘብ ሆኖ ቆሟል። ሁከቱን ለመቀልበስ በሀገራችን የተፈጠረውን አለመረጋጋት ተከትሎ የህዝቡን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥና ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል ሲባል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአስፈጻሚው አካል ታውጆ ተግባራዊ ሲሆንም ይህ ህዝብ የአንበሳውን ድርሻ ተጫውቷል። በዚህ የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ በሀገራችን ላይ ተደቅኖ የነበረው አደጋ እንዲቀለበስ ለማድረግ በተደረገው ርብርብ የህዝቡ ሚና ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።

ይህ ሰላም ወዳድ ህዝብ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሰላምን በማወክ ተግባር ላይ የተገኙ ወጣቶችን በመገሰፅ፣ ለሰላም እንዲሰሩና የሰላምን እሴት እንዲያውቁ ማድረግ የቻለ ነው። ይህ ህዝብ ላለፉት 26 ዓመታት ገደማ የተራመዳቸው የልማት አባጣና ጎርባጣ ውጣ ውረዶች ያስታውሳል።

ለውጦቹ በአሁኑ ወቅት የሚቀራቸው ተጨባጭ ለውጦች ቢኖሩም፤ ከትናንቱ በተሻለ ቁመና እንደሚገኙ ይገነዘባል። እርሱንም በተሻለ ማማ ላይ እንደሚያወጡት በልማቱ ውስጥ ተዋናይ የሆነው ማንኛውም ዜጋ በየደረጃው ተጠቃሚ እየሆነ መምጣቱን ራሱን በመግለፅ ጭምር ሊያስረዳ ይችላል።

ትክክለኛ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ካሉ፣ ህዝቡን ከዳር እስከ ዳር የሚያንቀሳቅስ ልማታዊ መንግስት ካለና በዚሁ መሪ አካል አስተባባሪነት ብሎም በህዝቡ የባለቤትነት መንፈስ የሚዘወር ሰላም እስካለ ድረስ፤ ሰርቶ መለወጥና ማደግ እንደሚቻል ጠንቅቆ የሚያውቅ ህዝብ ነው። በመሆኑም በአንዳንድ አካባቢዎች አልፎ አልፎ ስለሚከሰቱ የሰላም እጦቶች ይህ ህዝብ በቀዳሚነት ሊሰለፍ ይገባል። የባለቤትነት መንፈሱንም ይበልጥ የሚያጠናክርበት ወቅት ላይ መሆኑንም መገንዘብ አለበት።  

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy