Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት መኃንዲስ መሆኗን አሜሪካ ገለጸች

0 584

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአፍሪካን የኢኮኖሚ፣ሰላምና መረጋጋት ችግሮችን ለመፍታት ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደምትሰራ አሜሪካ አስታወቀች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ዶናልድ ያማሞቶ የተመራውን ልዑካን ቡድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ዶናልድ ያማሞቶ በዚህ ወቅት እንዳሉት ከ75 በመቶ በላይ በወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ ያለውን የአፍሪካ ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመፍታት አሜሪካ ኢትዮጵያን ማዕከል አድርጋ መስራት ትፈልጋለች።

”ኢትዮጵያ የቀጠናውም ሆነ የአህጉሪቱ የኢኮኖሚ እድገት መሃንዲስ ናት” ያሉት ረዳት ሚኒስትሩ አገሪቱ ያካበተችውን ልምድ የሌሎች አገራት ችግሮችን ለመፍታት እንደሚጠቅም ገልጸዋል።

በዚህና ሌሎች አህጉራዊ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ጋር መስማማታቸውን የገለፁት ውይይቱን የተከታተሉት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዴሊቨሪ ዩኒት ሃላፊ አቶ ዛዲግ አብረሃ ናቸው።

አሜሪካና ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ እድገት፣ በሰብዓዊ መብትና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በመከላከያና ጸጥታ ጉዳዮች  በትብብር እንደሚሰሩ በመግለጽ የዛሬውም ውይይት በነዚህ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም አሜሪካ በነዚህ ጉዳዮች ላይ የምታደርገው ድጋፍ እንዲጠናከርና ትብብሩም ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ተስማምተዋል።

በቀጠናዊ የሰላም ጉዳዮች ላይ በተለይም በደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ ጉዳይ ዙሪያ  ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመምከር ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ድጋፍ በሚያደርጉበት አግባብ ላይ መምከራቸውን አቶ ዛድግ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያና አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1903 የተጀመረ ሲሆን ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነት ያላቸው አገሮች ናቸው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy