Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ ህዳሴ ብለን ለጀመርነው የጋራ ፕሮጀክት ስኬታማ ተግባራትን በማከናወን ረጅም ርቀት ተጉዘናል- ጠ/ሚ ኃይለማርያም

0 329

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ ህዳሴ ብለን ለጀመርነው የጋራ ፕሮጀክት ስኬታማ ተግባራትን በማከናወን ረጅም ርቀት ተጉዘናል- ጠ/ሚ ኃይለማርያም

“የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የኢትዮጵያ ህዳሴ ብለን ለጀመርነው የጋራ ፕሮጀክት ስኬታማ ተግባራትን በማከናወን ረጅም ርቀት ተጉዘናል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ 12ኛውን የብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች በዓልን በማስመልከት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና ህብረ ብሄር መጽሄት ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል።

“በሕገ መንግሥታችን የደመቀ ሕብረ ብሔርነታችን ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ሀሳብ 12ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ህዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም በአፋር ክልል ይከበራል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም፥ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የቃል ኪዳን ሰነዳቸው በሆነው ህገ መንግስት ላይ አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት የገቡት ቃል አፈጻጸም ሲታይ ስኬታማ ተግባራት መከናወኑን ገልጸዋል።

በፖለቲካም ሆነ በኢኮኖሚው ዘርፎች የተመዘገቡት ለውጦችና የተገኙት ውጤቶች ለአገሪቷ ህዳሴ የተሄደው ረጅም ርቀት ስኬታማ መሆኑን እንደሚያመላክትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በአንድ በኩል “በጣም የሚያማልል ስኬት ተመዝግቧል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሌላ በኩል ደግሞ ያልተፈቱ ተግዳሮቶች መኖራቸውን ነው የተናገሩት።

ከድህነት ለመውጣትና ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ለመፍጠር በሚደረገው ርብርብ የተገኘውን ሃብት ለመቀራመት የሚፈልግ ሃይል መኖሩ ለህዳሴ ጉዞው መሰረታዊ ተግዳሮት መሆኑን አመልክተው፤ ህዝቡ ከእነዚህ ሃይሎች ጋር እየታገለ መምጣቱንና አሁንም በትግል ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

ሌላው የህዳሴ ጉዞው ተግዳሮት ፀረ ዴሞክራሲ ተግባራት ለመታገል የህዝቡን ተሳትፎ የማጎልበት ችግር መኖሩን ጠቁመው፤ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች በተለያየ ወቅት ያጋጠሟቸውን ዴሞክራሲያዊ ችግሮች እየፈቱ መምጣታቸውን ይህንንም አጠናክሮ ማሰቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን የበለጸገች አገር ለመገንባት በርካታ ተግባራት ከፊታቸው እንደሚጠብቃቸው ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች እየፈቱ የአገሪቷን ህዳሴ እንደሚያረጋግጡ ነው የገለጹት።

በሌላ በኩል በጥልቅ ተሃድሶ የአንድ ዓመት ሂደት በተከናወኑ ተግባራት ለውጥ መታየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ተናግረዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፥ የፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ፣ ብልሹ አሰራርና ሙስና እየታየ በመምጣቱ ጥልቅ ተሀድሶ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ተካሂዷል።

ፀረ ዲሞክራሲ አካሄዶችን ለመግታት በፖለቲካ አመራሩ ውስጥ ያለውን ችግር መፍታት የሚያስችል ጠንካራ ትግል መካሄድ መጀመሩን አረጋግጠዋል።

በጥልቅ ተሃድሶ ሂደት የህዝቡ ተሳትፎ የነቃ እንዲሆን የሚያስችሉ እንቅሰቃሴዎች በመካሄዳቸው ተጨማሪ ለውጦች ተገኝተዋል፡፡

በሙስና ትግሉም የተወሰነ ርቀት መኬዱንና የአሰራር ሥርዓት ለማሻሻል የተጀመሩ ተግባራት የበለጠ ጥልቀት እንዲኖራቸው ለማድረግ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

ትግሉ ውጤታማ እየሆነ በሚሄድበት ጊዜ በህብረተሰብ ደረጃ ያለው እንደሚጠናከር ጠቁመው፤ በዚህ ሂደት ውስጥ ዓመቱን ሙሉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉበት መሆኑን ገልጸዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy