Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ጉልህ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በመፍታት ከፍተኛ ለውጥ ያመጣ ነው….ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም

0 688

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት በአገሪቷ ውስጥ የነበሩ ጉልህ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በመፍታት ከፍተኛ ለውጥ ያመጣ ተራማጅ ህገ መንግሥት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡

ህገ መንግሥቱ የዓለም አቀፉ በተለይም ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያስቀመጣቸውን መርሆዎች ጭምር ሙሉ በሙሉ አካቶ የያዘ ዘመናዊ ከሚባሉ ህገ መንግሥቶች ተርታ የሚመደብ ትልቅ የቃል ኪዳን ሰነድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የገቡትን ቃል ኪዳን ለመፈፀም የሚያስችሉ በህገ መንግሥት ውስጥ የተለያዩ ምዕራፎች የተደነገጉ መሠረታዊ ጉዳዮች መኖራቸውንም እንዲሁ ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ኢትዮጵያዊ አንድነታቸውን አጠናክረው ለመሄድ የተጠናከረ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚከተሉት የጉዞ መስመር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

አንዱ ቤተኛ ሌላው ባዕድ የማይሆንበት፤ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቤተኛ የሆኑበት የራሳቸው የጋራ ፕሮጀክት ያላቸው መሆኑን ያረጋግጣል ብለዋል።

አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ላለፉት 25 ዓመታት እና ከዚያም ወዲህ የተሰሩ ሥራዎች ህያው ምስክሮች መሆናቸውን ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ የተናገሩት፡፡

ይህ የቃል ኪዳን ሰነድ በትክክለኛ አቅጣጫ እየሄደ እንዳለ የሚያስመሰክሩ ሥራዎችን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች አከናውነዋልም ብለዋል፡፡

በየአካባቢያቸው በልማት ሥራ ላይ በሰፊው በመሳተፍ ኢትዮጵያ ለባለፉት 15 ዓመታት ፈጣን እድገት እንድታስመዘግብ አድርገዋልም ነው ያሉት፡፡

በአጠቃላይ የፖለቲካ ማህበረሰቡንም ሆነ የኢኮኖሚ ማህበረሰቡን በመገንባትና የኢትዮጵያ ህዳሴ በሚል የተያዘውን ፕሮጀክት ለማሳካት ረጅም ርቀት ሄደናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy