Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የፈተናዎችን ቋጠሮ የሚፈታ ድርጅት

1 1,308

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የፈተናዎችን ቋጠሮ የሚፈታ ድርጅት

                                                   ዘአማን በላይ

እንደ መግቢያ

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፣ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ብአዴን)፣ የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) እና የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ጥምረት የፈጠረው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እንደ ተማሪ ተፈታኝ እንዲሁም እንደ ታጋይ ደግሞ የድል ባለቤት ሊባል የሚችል ነው። ድርጅቱ ከሀገራችን ህዝቦች ጋር በመሆን አምባገነኑን የደርግ ስርዓት ለመጣል ርብርብ ለማድረግ ከወሰነበት ጊዜ አንስቶ በመንግስትነት ሀገሪቱን መምራት እስከ ጀመረበት ጊዜ ድረስ በርካታ ፈተናዎችና መሰናክሎች አጋጥመውታል። እነዚህ ፈተናዎችና መሰናክሎች ድርጅቱን የተፈታተኑት ጊዜ ቀላል አይደሉም። አንዳንዶቹ ከድርጅቱ አልፎ ሀገርን አስጊ በሆነ ደረጃ የችግር ቋፍ ላይ ሊያደርሷት የሚችሉ ነበሩ።

ዳሩ ግን “ብዙሃን ይመውዑ” (ብዙሃን ያቸንፋሉ) እንዲል መፅሐፉ፤ ድርጅቱ ማልዶ ለትግል ከተነሳበት ወቅት ጀምሮ ከአብዛኛው ህዝብ ጋር ሲወድቅና ሲነሳ የመጣ በመሆኑና አባላቱም ከታች እስከ ላይ ድረስ በነበራቸው ፅኑ የመተጋገል መንፈስ እየተመራ አያሌ ውጣ ውረዶችን በብቃት መሻገር ችሏል። ዛሬ ላይ ደግሞ ፊት ለፊቱ የተደቀኑበትን ፈተናዎች ቋጠሮ ለመፍታት ግምገማ ተቀምጧል። እስካሁን የደረሰበትን የግምገማ ሂደትን ለህዝብ ይፋ በማድረግ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ደረጃ የአስተሳሰብ አንድነት መፈጠሩን አብስሮናል። “ይበል!” የሚያሰኝ ነው።

ሆኖም በአሁኑ ወቅት እዚህም ሆነ እዚያ የሚነሱት ጥያቄዎች ቀልብ የሚስቡ ሆነዋል። አንዳንድ ወገኖች፤ “ኢህአዴግ የትናንት ፈተናዎችን የመፍታት ተሞክሮዎቹን በዚህኛው አዲስ የፈተና ችግር ማጥሪያ ግምገማ ይጠቀምባቸው ይሆን ወይስ እንደተለመደው ‘በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ስራዎች መከናወናቸውን ገምግመናል’ በማለት ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ባመጣውና ቀዳሚውን የመተጋገል መንፈስ ገሸሽ ባደረገው አዲሱ ባህሪው ይቀጥላል?” የሚል ጥያቄ ያነሳሉ። ሌሎች ደግሞ፤ “ነብር ተፈጥሯዊ ዥንጉርጉርነቱን እንደማይተወው ሁሉ፤ ኢህአዴግም በነበረው የትናንቱ ባህሪያዊ መንገድ ቀጥሎ የፈተናዎችን አንጓ እየለየ እንደ ወትሮው የተግዳሮቶቹን ቋጠሮ ይፈታ ይሆን?” ሲሉ ስጋት አዘል ጥያቄ ሲያቀርቡ ይስተዋላል።

ርግጥ ጊዜው ሰዎችን ብዙ የሚያናግር ነው። ጉዳዩ የሀገርን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ የማረጋገጥና የተጀመረውን የጋራ ተጠቃሚነት እንዲቀጥል መሻት ስለሆነ፤ ‘ሰዎች ለምን ጥያቄ አቀረቡ?’ ማለት አይቻልም። አይገባምም። እንኳንስ ማናቸውንም ዓይነት ጥያቄዎች በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንዲቀርቡ የተሟላ ህገ መንግስታዊ መብትን የተጎናጸፈው የሀገሬ ህዝብ ቀርቶ፤ የተሸራረፈና ጭርሱንም መብት የሌለው የጎረቤት ሀገራት ህዝብም የሚሰማውን ነገር እየፈራና እየቸረም ቢሆን ማንፀባረቁ የሚቀር አይመስለኝም—መጠየቅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነውና።

ታዲያ “ማንኛውም ጥያቄ የራሱ መልስ አለው” እንደሚባለው፤ የድርጅቱን የፈተናዎችን ቋጠሮ የመፍታት አቅም ለመቃኘት ሶስት የእውነታ ሰበዞችን መምዘዝ ብቻ በቂ ይመስለኛል—በደርግ ውድቀት መባቻ (1983 ዓ.ም)፣ በቀዳማዊው የተሃድሶ ወቅት (1994 ዓ.ም) እና በሀገራችን የጎዳና ላይ ነውጥ በተነሳበት በ1997 ዓ.ም የተከተላቸውን ፈተናዎችን በብልሃትና በሰከነ መንገድ የመፍታት ተሞክሮዎችን። ድርጅቱ በእነዚህ ሶስት የተለያዩ ወቅቶች የፈታቸው የፈተና ቋጠሮዎች እንደ ተሞክሮ በእርሾነት ሊያገለግሉ የሚችሉ ይመስሉኛል። እናም ተረኩን የኋሊዮሽ ድርሳን ጉዞ እያንሰላሰልናቸው፣ ኢህአዴግ በአሁኑ ወቅት ያጋጠሙት የተከማቹና ደም እያፋሰሱ ያሉ ፈተናዎችን እንደምን ሊወጣ እንደሚችል በመመልከት ልናሳርገው እንችላለን። ቀዳሚው የድሉ መባቻ ወቅት ነው።…

የድሉ መባቻ

ከዛሬ 26 ዓመት በፊት። ወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት ያየለበት ነበር። አገር ጫታ የሆነበትም ጭምር። 1983 ዓ.ም። ያኔ ከ17 የማያንሱ የታጠቁ የብሔር ቡድኖች ነፍጥ አንግበዋል። ቡድኖቹ የተለያዩ ዘውግ ያላቸው ናቸው። የተወሰኑት ጠባቦችና ትምክህተኞች ሲሆኑ፤ ሌሎቹ ደግሞ የፅንፈኝነትና የአክራሪነት ፊታውራሪዎች ነበሩ። ሁሉም በየፊናው ይሻኮታል። የጎሪጥ ይተያያል።

በወቅቱ ደርግን ገርስሶ ስልጣን የያዘው ኢህአዴግ እነዚህ ቡድኖች ለሀገራችን የጋራ መፍትሔ እንዲሹ ባቀረበላቸው ጥሪ መሰረት የሽግግር መንግስቱን ለመቀላለቀል ከያሉበት ቦታ ወደ ሀገራቸው ተመሙ። አንዳንዶቹ ሱፋቸውን ግጥም አድርገው፣ ከረባታቸውን ‘ተከራብተው’ እና ፅድት ያሉ ሳምሶናዊታቸውን አንጠልጥለው እያፏጩ በቦሌ በኩል ገቡ። ትዕይንትም ሆነ። ርግጥ ለኢህአዴግ የእነዚህን የማይጣጣም ፍላጎት ያላቸውን ቡድኖች ማቻቻል በራሱ ትልቅ ተግዳሮት ነበር። የቡድኖቹን የተበታተነ ፍላጎት የተመለከቱ አንዳንድ ተንታኝ ተብዬዎችና የውጭ ሚዲያዎች እንዲሁም የሀገር ውስጥ የከሰረ ተሸናፊ ፖለቲካ አራማጆች ‘ኢትዮጵያ መበታተኗ ነው’ እያሉ ያሟርቱ ጀመር። ደረታቸውን እየደቁም “ወይኔ ኢትዮጵያ!” በማለት የአዞ እንባቸውን እንዳፈሰሱ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ። ኢህአዴግ ግን “ወይኔአቸውን” አልሰማም። ከፊቱ የተደቀነውን ፈተና በድል አድራጊነት ለመወጣት የራሱን መንገድ ተከተለ። እናም በመጀመሪያዎቹ የስልጣን ዓመታት በአራቱም የሀገሪቱ ማዕዘናት የሰላምና ማረጋጋት ስራዎችን ወደ ማከናወኑ ፊቱን አዞረ—ቀዳሚው ስራ ይኸው ነበርና።

በውድ የህዝብ ልጆች አኩሪ መስዕዋትነት የተገኘውን ድል ለመንጠቅ የሚሯሯጡ ፀረ ሰላም፣ ፀረ ልማትና ፀረ ዴሞክራሲ ኃይሎችን የማፅዳት ተግባሮችን ከወነ። ማንኛውም የትግል መድረክ አልጋ በአልጋ እንዳይሆን ያልተጻፈው የመተጋገል ሂደት የግድ ያዛልና ሂደቱ ሳንካ ገጠመው። አበው “በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል” እንዲሉ፤ ኢህአዴግና ሌሎች ታጣቂ ኃይሎች ለሀገራዊ ሰላም እየተሯሯጡ ባሉበት በዚያ ቀውጢ ወቅት፤ ራሱን “ኦነግ” እያለ ይጠራ የነበረው የጠባቦች ቡድን ይህንን የተቀደሰ ዓላማ ሊቀበል አልፈቀደም። የጦረኝነት አቅጣጫን ምርጫው አደረገ። ሰላማዊውን የሽግግር መንግስቱን መድረክ ረግጦ አፈነገጠ።

ግና ጦርነት ምጣኔ ሃብቷን እንደ ካሮት ቁልቁል እንድታድግ ያደረጋት ኢትዮጵያ ዳግም ወደዚያ ህይወትና ንብረት አውዳሚ ዘግናኝ ትዕይንት እንድትገባ ኢህአዴግ አልፈለገም። በ“ኦነግ” የጥፋት መንገድም ሊጓዝ አላሻውም። እናም ከፍተኛ ትዕግስት በተሞላበት ሁኔታ “ኦነግ”ን ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጣ ለመነ፤ አስለመነ። “ቢተኩሱባችሁም እንዳትተኩሱ” እያለ ሰራዊቱን ጭምር ለመስዕዋትነት ዳርጎ የሰላም እጁን ዘረጋ። ግና ሰሚ አላገኘም። ጠባቡ ቡድን በእንምቢተኝነቱ ፀና። እንዲያውም “ኦነግ” ለሰላም ሲታሰብ በየአካባቢው ሰው መግደልንና ንብረት ማውደምን ስራዬ ብሎ ተያያዘው። በዚህም የቡድኑ ፍላጎት ለሰላም የተዘረጉ እጆችን በጦረኝነት ማጠፍ መሆኑ ታወቀ።

ሁሉም የሰላም አማራጮች ተሟጥጠው አበቁ። 10 ሺህ የሚገመተውን የ“ኦነግ” ሰራዊት በመረጠው የጦርነት ቋንቋ ማናገር ግድ ሆነ። ኢህአዴግ የህዝቡን ሰላምና መረጋጋት የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት እንዲሁም “ኦነግ” በወቅቱ ያራምድ የነበረው ዜጎችን የመግደል ተግባሩ ህዝቡ መቆም እንዳለበት መጠየቁ በመረጠው ቋንቋው ለማናገር ገፊ ምክንያቶች ሆነው ቀረቡ። እናም በስተመጨረሻ የጠባቡ ቡድን የእብሪት ፊኛ ፈንድቶ ችግሩ በቁጥጥር ስር ሊውል ቻለ። የወቅታዊ ፈተናው ቋጠሮም እንዲህ ተፈታ።…

ከዚህ በኋላም ኢህአዴግ ከህዝቡ ጋር በመሆን ያከናወናቸው የሰላምና መረጋጋት ርምጃዎች ወሳኝ ምዕራፍን ከፈቱ። የሀገሪቱን ለሰላምና መረጋጋት ዕውን በማድረግ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ያቀዷቸውና በሽግግር መንግስቱ የተቀመጡት ዓላማዎች ዕውን እንዲሆኑ አስቻሉ። የሀገሪቱ ህዝቦች ወደውና ፈቅደው አንድ የጋራ ፖለቲካዊና ማጣኔ ሃብታዊ ማህበረሰብ ለመመስረት የሚያስችለውን የተመቻቸ ሰላማዊ ምህዳርንም ፈጠሩ። ርምጃዎቹም በህዝቦች ፈቃድና ይሁንታ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢፌዴሪ) እንዲመሰረት አስተማማኝ መሰረት ጣሉ። በደርግ ውድቀት መባቻ ላይ “ኢትዮጵያ መበታተኗ ነው” በማለት ሲያሟርቱ የነበሩ ወገኖች ጥንቆላ መሳይ ሟርትም መና ቀረ። ውሃ በላው። ድርጅቱም የፈተናዎችን ቋጠሮ ውል እየተረተረ  በሰላም መስመሩ ወደፊት መረሸ።…

ታዲያ የኢህአዴግን መንገድ የተመለከተ ማንኛውም ሰው “ድርጅቱ ለፈተና የተፈጠረ ነው” ብሎ ቢያስብ ብዙም የሚገርም አይመስለኝም። በሰላም መንገድ ለ10 ዓመታት ያህል የተጓዘው ኢህአዴግ፤ በ11ኛ ዓመቱ አዲስ ፈተና ፊቱ ላይ በጋሬጣነት ተደቅኖ ጠበቀው። ይህ አዲስ ፈተናም ወደ ቀዳማዊው ተሃድሶ እንዲያመራ አደረገው። ያኔም እንዲህ ሆነ።…

ቀዳማዊው ተሃድሶ

ይህ ወቅት ህወሓት ለሁለት የተከፈለበትና ኢህአዴግም እንደ ድርጅት የውስጠ-ድርጅት ትግሉ የጠነከረበት ጊዜ ነበር፤ የዛሬ 16 ዓመት ገደማ፤ 1994 ዓ.ም። ክፍፍሉ ሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችንም ጭምር የነካካ በመሆኑ ድርጅቱ ሁለንተናዊ አቋሙን በጥንቃቄ እንዲፈትሽ ያደረገ ነበር። ግና እንዴት?…ነገሩ ወዲህ ነው።….

ወቅቱ ኤርትራ መንግስት የእብሪት ወረራ የተከፈተው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ፍፁም ድል አድራጊነት የተጠናቀቀበት ማግስት ነው። እናም በህወሓት/ኢህአዴግ ውስጥ ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች ብቅ…ብቅ ማለት ጀመሩ። አመራሩም “የውስጥ ችግሮቻችንን ፈትሸን እንፍታ” የሚል የጋራ ድምዳሜ ላይ ይደርሳል። ውይይቱንም ሁሉም በየድርጅቱ እንዲያደርግና በስተመጨረሻም በኢህአዴግ ደረጃ ለመቀጠል ስምምነት ተደረገ። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ በወቅቱ በጠባብነት፣ በኪራይ ሰብሳቢነትና በትምክህት ጎራ የተሰለፈ ቡድንን ያቀፈ አካል በአንድ ወገን ብቅ አለ። በሌላ በኩል ደግሞ ድርጅቱንና ሀገሪቱን ከመበተን የሚያድን የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመርን ያነገቡ ኃይሎች ተሰለፉ። ልዩነቶች በገሃድ መታየት ጀመሩ። የውስጠ-ድርጅት ትግሉም እንደ ቋያ እሳት ተጋጋመ።

በወቅቱ “አንጃው” ተብሎ የተሰየመው የጥገኝነት አቀንቃኝ ቡድን በማዕከላዊ ኮሚቴ 13 ለ15 በሆነ ድምፅ ሲሸነፍ ዴሞክራሲዊ መንገድን በመርገጥ አሻፈረኝ ብሎ ውይይቱን አቋርጦ ወጣ። ይህን ቡድን ተሰብሳቢው “በሰማዕታት አጥንትና ስጋ ይዘናችኋል እባካችሁ ተቀመጡና ተወያዩ” ቢላቸው ‘እምቢኝ፣ አሻፈረኝ’ በማለት ውይይቱን ረግጦ ወጣ። ቡድኑ የድርጅቱን ህገ ደንብ በግላጭ ጣሰ። በድርጅቱ አሰራር መሰረት ውይይቱ “አንጃውን” አግዶ ባሉት አባላት እንዲቀጥል ተደረገ።

የድርጅቱ ድርሳናት እንደሚያትቱት፤ የ“አንጃው” አንዳንድ አባላት በወቅቱ በኦሕዴድና በደሕዴን ውስጥ የነበራቸውን ተሰሚነት በመጠቀም በሁለቱ ድርጅቶች ውስጥ ያልተገባ አካሄድን ለመከተል ሞከሩ። አባላቱ ደቡብና ኦሮሚያ በእኛ ስር ስለሆኑ ምን ያመጣሉ ሲሉም ታበዩ። ዳሩ ግን አብዛኛው ተወያይ የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመሩን በመደገፉ ምክንያት ይህ የ“አንጃው” ቀቢፀ-ተስፋ እንደ ጉም በንኖ ጠፋ። ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመሩ የበላይነትን በመያዙም ድርጅቱም ከብተና፣ ሀገራችንም የህዳሴዋን ጉዞ የምታሳልጥበት መንገድ ተያያዘችው። ዴሞክራሲውም ስር እንዲሰድ ብርቱ ጥረት ተደረገ። የድርጅቱ የወቅቱ ፈተና ቋጠሮም በዚህ መልኩ ተፈታ።…

ኢህአዴግና ፈተና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ይመስላሉ። በእያንዳንዱ የትግል መድረክ ፈተና ሊጠፋ አልቻለም። ገና ከመነሻው ዴሞክራሲ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚያምነው ኢህአዴግ ፊት ለፊቱ የሚጠብቀውን ሀገራዊ ምርጫ “እንከን አልባ” ለማድረግ ወገቡን ሸብ አድርጎ ተነሳ— ለምርጫ 97። ግና “ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከንቢያው ቂጢጥ” እንደሚባለው የምርጫው ዋዜማ በተቃዋሚዎች ኢ-ዴሞክራሲ አስተሳሰብና የጎዳና ላይ ነውጥ ታጠነ። ልጓም የሌላቸው የቀለም አብዮት ስብከቶች ቦታቸውን ያዙ።…

የጎዳናው ላይ ነውጥ

ምርጫ 97 የሀገራችን የተቃውሞ ጎራ የነበረበትን ቁመና የሚያሳይ ይመስለኛል። ጎራው ኢህአዴግ “እንከን አልባ”ና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ለማድረግ ቆርጦ የተነሳውን የምርጫ ሂደት ከጅምሩ እንከን በእንከን አደረገው። ጎራው በተዛባና በተሳሳተ መንገድ ሂደቱን ተጠቀመበት።

በወቅቱ ተቃዋሚዎች የህዝቡን ቅሬታዎችና ብሶቶች የማራገብ፣ ልክ እንደ አሁኑ ወቅት “ኢህአዴግ አብቅቶለታል” የሚል ቀቢፀ-ተስፋዊ ስብከት እንዲሁም ፍፁም ዘረኛ በሆነ አስተሳሰብ “ወደ መጡበት እንመልሳቸዋለን…ምንትስ” የሚሉ ኢ-ዴሞክራሲያዊ ምልከታዎችን እስከማራመድ ደረሱ። ባልተገባ ሁኔታም ምቹውን የምርጫ ምህዳር ዘመቱበት። ውሃ ቸለሱበት። የትምክህትና የጥበት ሃይሎች በአንድነት ተቀናጅተውም የዘመቻው አካል ሆኑ። በዓለም ላይ የሚገኙ አክራሪ ኒዮ-ሊበራሎችና ኪራይ ሰብሳቢ ሃይሎች ከያሉበት ዋሻ በፉጨት ተጠራርተው የዚሁ ዘግናኝ ቅስቀሳ አካል ሆኑ። የቀለም አብዮት ዘመቻም በውጭና በውስጥ ሃይሎች የጋራ ጊዜያዊ ግንባር አማካኝነት ተከፈተ።

“እንደ ወገብ ምንትስ ከኢትዮጵያ ትከሻ ላይ አይወርድም” የሚባለው የኤርትራ መንግስትም አጋጣሚውን ለመጠቀም ቋመጠ። በግንባር ተዋግቶ ያጣውን ድል በከተማ ውስጥ የጎዳና ላይ ነውጥ የሚያገኝ መስሎት የተለመደውን ጉም መዝገን ጀመረ። በስተመጨረሻም እነዚሁ ኃይሎች በፈጠሩት ሁኔታ ተቃዋሚዎች በጎዳና ላይ ነውጥ መንግስትን ከስልጣን ለማስወገድና ህገ መንግስቱን ቦጫጭቀው ለመጣል በቀለም አብዩተኞች እየታገዙ ተንቀሳቀሱ።

አገሪቱን በመምራት ላይ ያለው ኢህአዴግ ግን ይህን በሀገርና በህዝብ ላይ የተጋረጠን ወቅታዊ ፈተና ቋጠሮ እንደለመደው በሰላማዊ መንገድና በህጉ መሰረት ለመፍታት ጥረት አደረገ። ይህም በጎዳና ላይ ነውጥ ሳቢያ በህዝቡ ህይወትና ንብረት ላይ ለመዝመት የተጀመረው የተቃውሞ ጎራው ጥረት መና እንዲቀር አድርጓል። በኢህአዴግ የሚመራው መንግስት የህዝቡን ሰላማዊ ህይወት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት አካል በመሆኑ በወቅቱ መወሰድ ያለበትን ርምጃ ሳይወድ በግድ እንዲወስድ ተገደደ። የህግ የበላይነትም እንዲከበር ተደረገ።  

በወቅቱ በአንድ ወገን ሰላምን የማስከበር ስራ እየተከናወነ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተቃዋሚዎች ባሸነፉበት አዲስ አበባ ያገኙትን ወንበር እንዲወስዱና በመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ላይ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ እንዲለመኑ ተደረገ። ይህ የሆነበት ምክንያትም እነርሱን የመረጠውን ህዝብ በማክበርና ኢህአዴግ ለህዝብ ካለው አክብሮት የመነጨ ነው። እነርሱ ግን “እምቢኝ፣ አሻፈረኝ” አሉ። በሚያስገርም ሁኔታ የመረጣቸው ህዝብ ፓርላማ ግቡ ብሏቸው የሰጣቸውን ድምፅም መልሰው ለውይይት አቀረቡት። በስተመጨረሻም አንዳንዶቹ “ፓርላማ አንገባም” በማለት የመረጣቸውን ህዝብ ድምፅ አሽቀንጥረው ጣሉት።…መንግስትም የህዝቡን ድምፅ አክብረው ፓርላማ ከገቡት ተቃዋሚዎች ጋር አብሮ መስራቱን ቀጠለ። የነበረው የፈተና ቋጠሮም በዚህ መልኩ ተቋጨ።…

ከላይ የጠቀስኳቸው ጥቂት ነጥቦች ድርጅቱ ፈተናዎችን በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚፈታ ማሳያዎች ናቸው። በሂደት ከችግሮች ተምሮ ችግሮቹን እያረቀና የሚያጋጥሙትንም ተግዳሮቶች ከህዝብ ጋር በመሆን የማስተካከል አቅሙን የሚያረጋግጡም ናቸው። በዚህም ድርጅቱ ከፈተናዎች ባሻገር የዳበረ ተሞክሮ ባለቤት እንደሆነም አረጋጋጭ ናቸው። ኢህአዴግ ግን አሁንም ፊት ለፊቱ ላይ ፈተናዎች ተደቅነውበታል። ለመሆኑ ፈተናዎቹ ምንድን ናቸው?…

ወቅታዊው ፈተና

ለወቅታዊው ፈተና ዋቢ የማደርገው ኢህአዴግ በቅርቡ እያካሄደ ስላለው ግምገማ የሰጠውን መግለጫ ነው። ድርጅቱ በቆየው ባህል መሰረት አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያካሂደው የትግል ሂደት የሚያጋጥሙትን ጉድለቶች ሰፊ ጊዜ ሰጥቶ በጥልቀት እየገመገመ ነው። ግምገማውን መሰረት በማድረግም ራሱን በራሱ ያርማል፤ እንደሚያርምም ገልጷል።

ኢሕአዴግ የህብረተሰቡን ለውጥ የሚመራ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን፤ አስተማማኝ የለውጥ መሪ የሚሆነውም ራሱንም እየለወጠ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ያምናል። በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በመታየት ላይ የሚገኙት በዋነኛነት ከልማት፣ ከመልካም አስተዳደርና ከሰላም ጋር የተያያዙ ችግሮች የማያዳግምና መሠረታዊ የሆነ መፍትሔ እንደሚሰጥም ገልጷል። እስካሁን በተደረጉት ግምገማዎችም የችግሮቹን ዓይነተኛ ባህሪዎችና ዋነኛ መንስዔዎች አስመልክቶ ዝርዝር ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ በአመራሩ ዘንድ ከመቼውም ጊዜ በላቀ አኳኋን የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር መቻሉን ገልጷል። የአስተሳሰብ አንድነት ለተግባር አንድነት መሰረት በመሆኑም ድርጅቱ ኃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት እንደወትሮው በላቀ ደረጃ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት አገሪቱ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በፈጠረው ተስፋና የተከመሩ ፖለቲካዊ ችግሮች ፊቱ ላይ በደቀኑት ሥጋት መካከል አጣብቂኝ ውስጥ የገባችበት ሁኔታ እንዳለ በትክክል ተገንዝቧል። የተጀመረውን ፈጣን ዕድገትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እስካሁን የመጣበትን ርቀት ለማሳካትም ሆነ ወደፊትም ለማስቀጠል በኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ካሁን በፊት የነበረው አኩሪ በመተጋገል ላይ የተመሠረተ አንድነት በቦታው ላይ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አብራርቷል።

ኢህአዴግ ያደረገው የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ በርካታ አበረታች ውጤቶች የተገኙበት ቢሆንም፣ በሚፈለገው ደረጃ ጥልቀት ያልነበረው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተመልሶ ወደ አዘቅት መመለስ መጀመሩን በትክክል አስቀምጧል። በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በዋነኛነት የድርጅቱ አመራር ያሳየው ድክመት የፈጠራቸው መሆናቸውን በሚገባ ይገነዘባል። አገሪቱ በአሁኑ ወቅት ለምትገኝበት አስጊ ሁኔታ ድክመቱ ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም እንዲሁ።

ይህ በተወሰነ መልኩ ያነሳሁት የኢህአዴግ መግለጫ ያሉትን ችግሮች ያመነና ለመፍትሔውም እንደሚተጋ የሚያሳይ ነው። ራሱን በመፈተሽ በግምገማው ማጠቃለያ ላይ ተግባራዊ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ርግጥ ቀደም ሲል ከገለፅኳቸው ሶስት የፈተና አፈታቶቹ በመነሳት ድርጅቱ አሁን በአገሪቱ የተፈጠሩትን ችግሮች እልባት ሊሰጣቸው እንደሚችል መጠራጠር አይገባም። ድርጅቱ የሚለውን እንድንሰማው ያለፉት ተግባሮቹ ግድ ይሉናል።

ኢህአዴግ የጠመጣባቸው መንገዶች ትዕግስትን የተላበሰ፣ በአርቆ አሳቢነት የሚመራና ማናቸውንም ችግሮች ህዝብን ይዞ መፍታት የሚያስችል ተክለ-ቁመና ያለው በመሆኑ ፈተናዎቹን ማለፉ አጠያያቂ አይሆንም። እናም በመግቢያዬ አካባቢ አንዳንድ ሰዎች ያነሷቸው ጥያቄዎች በመግለጫው አግባብ ምላሽ ያገኙ ይመስለኛል። ምክንያቱም ድርጅቱ የትናንት የመተጋገል መንፈሱን እንደማይተው፣ ውስጣዊ የአመራር ችግሩን በጥልቀት ፈትሾ እንደሚፈታና የተፈጠረውን ሀገራዊ ችግር በቁርጠኝነት እንደሚፈታ በማስታወቁ ነው። ርግጥ በኢህአዴግ ቤት ውስጥ “አለባብሰው ቢያርሱ…” የሚለው ይትብሃል አይሰራም። ችግሮቹን በግምገማው በደንብ ፈትፍቶ በማየት ዛሬም የፈተናዎችን ቋጠሮ ፈትቶ የሚያሳየን ጊዜ ሩቅ የሚሆን አይመስለኝም።

  1. Tess says

    This article is well articulated and shows the challenges that EPRDF passed in the past 26 years curiously. I thank the writer who give detail information about the issue. Hopefully, the ruling party will solve the current crises.

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy