Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጠንካራው ትግል

0 265

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ጠንካራው ትግል

ዳዊት ምትኩ

በአሁኑ ሰዓት በፖለቲካ  አመራሩ ውስጥ ኪራይ ሰብሳቢነትን፣ ሙስናን እንዲሁም ሌሎች ፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄዶችን ለመግታት ጠንካራ ትግል መካሄድ ጀምሯል። በተለያዩ የድርጅቱ ፓርቲዎች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በየደረጃው እየተካሄዱ ያሉት የመተጋገል መድረኮች የዚህ ጉልህ ማስረጃ ነው።

ታዲያ በዚህ ጠንካራ ትግል መንግስትና ገዥው ፓርቲ በጀመሩት የጥልቅ ተሃድሶ ሂደት ተግባሮች የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ ከፍተኛ ስለነበር ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸው ይታወቃል። የአገራችን ማነቆ ይሆናል ተብሎ የሚታሰበው ሙስናንና ኪራይ ሰብሳቢነትን በመታገል ረገድም የተወሰነ ርቀት መኬድ ተችሏል። እነዚህን ለውጦች አቅቦ በመያዝ በህዝቡ ግንባር ቀደም ተዋናይነት ሂደቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ ይመስለኛል።  

እንደሚታወቀው ሁሉ የዛሬ 16 ዓመት ገደማ በተካሄደው ኪራይ ሰብሳቢነትን፣ ጥገኝነትንና የመንግስት ስልጣንን ለራስ ጥቅም የማዋል ተግባርን የመታገል ተሃድሶ ውስጥ በዋነኛነት መንግስትና ገዥው ፓርቲ ጉዳዩን ቢያቀጣጥሉትም ህዝቡ የማይተካ ሚና እንደነበረው እናስታውሳለን።

ይህ ተሃድሶ ሀገራችንን አሁን ላለችበት የዕድገት ጎዳና ያበቃት መሆኑ አይካድም። በወቅቱ በአንድ በኩል ስልጣንን የኢኮኖሚያዊ ሃብትና የብልፅግና መሳሪያ በማድረግ ፀረ-ዴክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት በሚሹ ወገኖች፤ በሌላ በኩል ደግሞ ስልጣን የሃብት ምንጭ እንዳይሆን፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ እንዲያብብና እንዲዳብር ብሎም የጥገኝነት አስተሳሰብ የበላይነት እንዳያገኝ በሚተጉ ኃይሎች መካከል ከፍተኛ ግምገማና የመድረክ ትግል መካሄዱን እናስታውሳለን።

ታዲያ በወቅቱ ተፈጥረው በነበሩት በእነዚህ ሁለት ፅንፍ አመለካከቶች ዙሪያ በተካሄዱ ግምገማዊ የሃሳብ ፍጭት፤ ስልጣን የጥቂቶች የሃብት ማካበቻ እንዳይሆን እንዲሁም ዴሞክራሲና ዴክራሲያዊ አንድነት እንዲጎለብት ብሎም የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ በህብረተሰቡ ውስጥ የበላይነት እንዳያገኝ የታገለው ወገን ነጥሮ በመውጣት ተሃድሶው ግቡን መትቷል፤ ውጤትም አምጥቷል።

እንደ እውነቱ ከሆነ በወቅቱ እንዲህ ዓይነቱ የተሃድሶ ርምጃ ባይካሄድ ኖሮ ሀገራችን የምትመራባቸው የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲሁም ስልቶች ባልተነደፉ ነበር። ያኔ አቆጥቁጦ የነበረው ፀረ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብም በወቅቱ ከነበረው ሁኔታ ጋር አብሮ ባልከሰመ ነበር። እናም ተሃድሶ ሲባል እንዲያው ለይስሙላ አሊያም ለታይታ ሲባል ብቻ የሚከናወን ሳይሆን ይህን መሰሉን ለውጦች እውን የሚያደርግ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ይመስለኛል።

መንግስት ትናንትም ይሁን ዛሬ ያከናወናቸውና የሚያከናውናቸው ተሃድሶዎች ተጨባጭ ውጤቶችን ያመጡ ናቸው። መንግስት በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው የተሃድሶ ሂደት የመንግስት መዋቅሮችን የህዝቡን እርካታ በሚፈጥሩ መንገድ እያከናወነ ነው። ሙሰኞችን ለህግ በማቅረብ በፈፀሙት ጥፋት ልክ እንዲቀጡ በማድረግ ሂደት ውስጥ ህዝቡ እያከናወነ ያለው ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

ይህ ሁኔታም ከዚህ ቀደም በነበሩ የተሃድሶ መንገዶች የተከናወኑ ተግባራትን የሚያጠናክርና ይበልጥ የሚያሰርፅ ነው። መንግስት ለያዘው ቁርጠኛና ውጤት ሊያመጣ የሚችለው ጠንካራ የጥልቅ ተሃድሶ ሁሉም የበኩሉን ጠጠር ቢወረውር የሚፈለገው ለውጥ ሊመጣ ይችላልሚና መወጣት ሲችል ነው።

ርግጥ በየትኛውም ዴክራሲያዊ ሀገር ውስጥ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር ነባራዊ ክስተት ነው። ምንም እንኳን በሀገራችንም መንግሥትና ህዝብ በመገንባት ላይ የሚገኙት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ገና ለጋ ቢሆንም፤ እንደ ጀማሪ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ከዚህ ነባራዊ ክስተት የፀዳንና ጉድለቶች የሉብንም ብሎ ለመናገር አይቻልም።

ለነገሩ የኢፌዴሪ መንግስትና እርሱን የሚመራው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከህዝቡ ጋር በመሆን በየጊዜው በሚወስዷቸው በርካታ ርምጃዎች የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰቦች በመጠኑም ቢሆን እየቀረፉ ቢሆኑም፤ የሚፈለገው የአስተሳሰብ ለውጥ ተገኝቷል ማለት አይቻልም። እንዲያውም አስተሳሰቦቹ እየገነገኑ ጫፍ ላይ እየወጡ ይመስላሉ።

በአሁኑ ሰዓት በአመዛኙ ኪራይ ሰብሳቢነትንና ሙስናን የሚፀየፍና እንደ ነውር የሚያይ የመንግስት ስራ አስፈፃሚን ብሎም ህዝብን በተሟላ ሁኔታ መፍጠር አልተቻለም። አስተሳሰቡ በሚገባ ሁኔታ በተግባር ተቀርፏል ማለት አይቻልም። ምንም ዓይነት መሰረታዊ ለውጥ አልመጣም ባይቻልም፤ አጥጋቢ ነው ብሎ በትክክል መናገር የሚቻል ይመስለኝም።

በሰጪም ይሁን በተቀባይ መካከል ያለው አስተሳሰብ አንድና ተመሳሳይ ነው ማለት ይቻላል። ይህ የሆነውም ካለፉት ስርዓቶች ይዘናቸው የመጣናቸው ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ቅሪት አስተሳሰቦች ብሎም ልማቱ የፈጠራቸው አንዳንድ ሁኔታዎች አስተዋፅኦ በማድረጋቸው  መሆኑ አያጠያይቅም።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ሁሉም ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ የመንግስት ስራ ፈፃሚዎችና ከሙስና ጋር ግንኙነት ባለቸው ግለሰቦች ላይ የተወሰዱት የአስተዳደራዊና ህጋዊ ርምጃዎች መንግስት በፀረ-ሙሰና ትግሉ ላይ ምን ያህል ቁርጠኛ አቋም እንዳለው የሚያሳዩ ናቸው።

ይህ የመንግስት ቁርጠኛ አቋም መንግስት ዛሬም እንደ ትናንቱ ቃሉን የማያጥፍና ሁሌም የሚያካሂደው የፀረ ሙስና ትግል በውጤት የሚታጀብና ለዚህም ህዝቡ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ያደረገው መሆኑን ያሳየ ተግባር ነው። መንግስት ትናንትም ይሁን ዛሬ ያከናወናቸውና የሚያከናውናቸው የፀረ-ሙስና ዘመቻዎች ግባቸውን የሚመቱት ህዝቡን ያሳተፉ በመሆናቸው ነው።

መንግስት በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው የፀረ ሙስና ትግል የመንግስት መዋቅሮችን የህዝቡን እርካታ በሚፈጥሩ መንገድ እያከናወነ ነው፤ ምንም እንኳን የሚቀሩ ጉዳዩች ቢኖሩም። ይህ ሁኔታም ከዚህ ቀደም በነበሩ የተሃድሶ መንገዶች የተከናወኑ ተግባራትን የሚያጠናክርና ይበልጥ የሚያሰርፅ ነው።

መንግስት በቁርጠኝነት የያዘው ይህ የፀረ ሙስና ትግል በህዝቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎ መረጋገጥ መቻል አለበት። ኪራይ ሰብሳቢዎችንና መዝባሪ ሙሰኞችን ህዝቡ በሚገባ ያውቃቸዋል። ትናንት ምን እንደነበሩና ዛሬ የት እንደደረሱ ከህዝብ የሚሰወር አይደለም። ህዝቡ የከፈለው ግብር እነማን ኪስ ውስጥ ያለአግባብ እንደገባ ያውቃል።

ህዝቡ በኪራይ ሰብሳቢነትና በሙስና ላይ የሚሳተፉ ወገኖችን ሁሉንም አብጠርጥሮ ያውቃቸዋል። እነማን ከማን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው፣ የትስስር ሰንሰለታቸው እስከየት ድረስ እንደሆነ፣ በምን ዓይነት ቁርኝት እንደሚጠቃቀሙ ከህዝቡ የተሰወረ አይደለም።

እርግጥ ኪራይ ሰብሳቢዎችና ሙሰኞቹ ከሌላ ፕላኔት የመጡ ሳይሆኑ ከህዝቡ ውስጥ የተገኙ በመሆናቸው ህዝቡ የአውራ ጣቱን ያህል በሚገባ ያውቃቸዋል። በመሆኑም የፀረ ሙስና ትግሉ ግለቱን ጨምሮ ትናንት ከነበረበት ወደ ተሻለ ከፍታ እንዲሸጋገር የህዝቡን ሚና ማረጋገጥ ይገባል። ይህን ጠንካራ ትግል ይበልጥ ማጠናከር ያስፈልጋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy