Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ስራ ፈጣሪዎቹ መንደሮች

0 340

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ስራ ፈጣሪዎቹ መንደሮች

ዳዊት ምትኩ

ኢትዮጵያ በሁሉም የአገራችን ክፍሎች የገነባቻቸውና በመገንባት ላይ የምትገኘው የኢንዱስትሪ መንደሮች በተለይ ለየአካባቢው ወጣቶች ስራ ከመፍጠር አኳያ ሚናቸው የላቀ መሆኑን እያስመሰከረሩ ነው። አገራችን የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማስፋፋት እያከናወነች ያለችውን ተግባሮች በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጋር የሚያያዙ ናቸው።

እንደሚታወቀው ሁሉ ኢትዮጵያ ከአገር ውስጡ ባለሃብት በተጨማሪ የውጭ ባለሃብቶች በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚኖራቸው የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ተሳታፊነት እንዲሆኑ እያደረገች ነው። ይህም የዘርፉን ዕድገት ለማፋጠን ጉልህ ሚና አለው።

ይህን መሰረታዊ ዕውነታ በመመርኮዝም በዕቅድ ዘመኑ በሁሉም ዘርፎች ጥንቃቄ በተሞላው ሁኔታ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ብርቱ ጥረት ይደረጋል። በተለይም  ከፍተኛ አቅምና ፍላጎት እንዲሁም በአፈፃፀማቸው ጥሩ ስምና ዝና ያላቸውን የውጭ ኩባንያዎች በመመልመልና የማግባባት ስራ በማከናወን የዘርፉን ዕድገት እንዲያሳድጉት ማድረግ እንዲገባ ተጠቅሷል። ባለሃብቶቹን ኤክስፖርት ተኮር በሆኑ የማኑፋክቸሪንግ ውጤቶች ላይ በማሰማራት ሀገራችን ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

እርግጥ ሀገራችን የውጭ ባለሃብቶች ኤክስፖርት ተኮር በሆኑ ዘርፎች ውስጥ እንዲካተቱ ስታደርግ ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ምንም ዓይነት ቦታ ሳትሰጥ ነው ማለት አይደለም። የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችም መዋዕለ ንዋያቸውን በዘርፉ እንዲያፈሱ ይደረጋል።

በተለይም በማደግ ላይ የሚገኙት የሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ተመልምለው በቂ ድጋፍ እንደሚሰጣቸውና በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ገቢ ምርቶችን በሚተኩ ዘርፎች ጭምር እንዲሳተፉ እየተደረገ ነው።

አገራችን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የምታደርገውን ሽግግር በማሳለጥ ረገድ የኢንዱስትሪ መንደሮቹ ሚና ከፍተኛ ነው። መንግስትም በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች በራሱ ከፍተኛ ወጪ መንደሮቹን በመገንባት ላይ ይገኛል። የመንደሮቹ ልማት ለዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥሩ ናቸው።

መንግስት በያዘው ዕቅድ መሰረት በኢኮኖሚው ላይ የሚታይ መዋቅራዊ ለውጥን ለማስጀመር የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ በየዓመቱ ቢያንስ የ24 በመቶ ዓመታዊ አማካይ ዕድገት ማስመዝገብ ይኖርበታል። ይህ ማለት በ2012 ዓ.ም የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ በአጠቃላይ ኢኮኖሚው ያለውን ድርሻ ወደ ስምንት በመቶ ከፍ እንዲል ያደርገዋል።

ይህ ለውጥም የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ድርሻ በአሁኑ ወቅት ከሚገኝበት በአራት እጥፍ እንዲያድግ በማድረግ ወደ መጀመሪያው የመካከለኛ ጉዞ መንገድ ለመድረስ ለታለመው ዕቅድ እስከ 18 በመቶ የማድረስ ግብን ሊያሳካ ይችላል። ሀገራችን ለያዘችው የመካከለኛ ገቢ ራዕይን ለማሳካትም መደላድል ይፈጥራል። የዜጎች ስራ የማግኘት እድልና ተጠቃሚነት በዚያው ልክ ከፍ ይላል።

የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዕድገት ሊረጋገጥ የሚችለው ከኢንቨስትመንት መስፋፋት ጋር ተያይዞ እንጂ ለብቻው ተፈፃሚ እንዲሆን ብቻ አይደለም። የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ኢንቨስትመንትን ዕውን ከማድረግ አኳያ መቆራኘት ይኖርበታል።

ይህን ዕውን ለማድረግም በአሁኑ ወቅት ያሉትም ይሁኑ በቀጣይ ወደ ስራ የሚገቡት ኢንዱስትሪዎች፤ የቴክኖሎጂ አቅማቸውን፣ ምርታማነታቸውን፣ የጥራት አመራር አቅማቸውን ብሎም ተወዳዳሪነታቸውን በቀጣይነት መገንባት ይችሉ ዘንድ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረግላቸዋል።  

ከዚህ ጎን ለጎንም የሳይንስ፣ የቴክኖሎጅና የኢኖቬሽን አቅምን ለማሳደግ ከሀገሪቱ የዕድገት ፍላጐት ጋር የተጣጣመ የቴክኖሎጅ ሽግግር ለማድረግ በዕቅዱ ላይ ተቀምጧል። ይህን ለማከናወንም በተለይ ለሀገር ውስጥ ኩባንያዎችና ባለሃብቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።

ስለሆነም በዘርፉ እስካሁን ድረስ የተደራጁ የኢንዱስትሪ ልማት ደጋፊ ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች አቅማቸው ይበልጥ እንዲጎለብትና ጥራት ባለው የትምህርት ማሳለጫዎች እንዲደጉ ይደረጋል። ከውጭ መሰል ተቋማት ጋር የሚኖራቸው ቁርኝትና እንዲጠናከር አሰራራቸውም እንዲዘምን ለማድረግ ታስቧል።

በመሆኑም ተስማሚና የተሻሻሉ ቴክኖሎጅዎችን የማፈላለግ፣ የመምረጥ፣ የማለማመድና የመጠቀም ብሎም የማሻሻል ስራዎችን በማከናወን የዘርፉን ምርታማነትን ለማሳደግ ጥረት ይደረጋል።

በመሆኑም በተለይ ጥራትን፣ ምርታማነትን እንዲሁም ተወዳዳሪነትን ለማጐልበት ሀገራችን የመረጠችው የካይዘን የአመራር ፍልስፍና በሁሉም ዓይነት ኢንዱስትሪዎችና የኤክስፖርት ዘርፎች ገቢራዊ እንዲሆኑ ወሳኝ ስራዎች እየተከናወኑ ናቸው።

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ኢትዮጵያ ከህዝብ ቁጥሯ ጋር ተመጋጋቢ የሆነ የአንዱስትሪ መንደሮችን መገንባት ከቻለች ከምስራቅ አፍሪካ አልፋ የአፍሪካ የኢንዱስትሪ አቅም ማሳያ ልትሆን ትችላለች።

የአገራችን የህዝብ ቁጥር በአምስት በመቶ ገደማ እያደገ ይገኛል፤ በየአመቱ ለአንድ ሚሊዮን ህዝቦች የስራ ዕድል መፍጠር ያስፈልጋል። የህዝብ ቁጥር ተግዳሮት ብቻ አይደለም። ከፈጣን ኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ከተሳሰረ ዕድልም ጭምር ነው። እናም ይህን የህዝብ ቁጥር በትክክል ሊያሟሉ የሚችሉ የኢንዱስትሪ መንደሮችን መገንባት ያስፈልጋል። ይህም በዚያው ልክ ስራ በመፍጠር የስራ ፈላጊዎችን ቁጥር ይቀንሳል።  

እርግጥ ይህን ፍላጎት ሊሸፍኑ የሚችሉት የኢንዱስትሪ መንደሮች የሚገነቡት የአገር ውስጥም ይሁን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ነው። ፓርኮቹ አስፈላጊው የመሰረተ ልማት ተሟልቶላቸው የሚገነቡ በመሆናቸው ባለሃብቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያደርጓቸው ናቸው።

በመልማት ላይ የሚገኙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዓለም የደረሰበትን የግንባታ ሂደት ተከትለው የሚገነቡ በመሆናቸው ከአካባቢ ብክለት ነፃ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ  በምርት ወቅት ተረፈ ምርታቸውን እንደገና መጠቀም በሚያስችል ሁኔታ የተገነቡ በመሆናቸው የሃብት ብክነትን ማስወገድ ይችላሉ። ይህም መንደሮቹ በምርትም ይሁን በተረፈ ምርት ውጤታማ መሆን የሚያስችሉ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።

በአሁኑ ሰዓት በአዋሳና በመቀሌ ስራቸውን የጀመሩት የኢንዱስትሪ መንደሮች ለበርካታ ዜጎች የስራ እድልን የፈጠሩ ናቸው። መንግስት በአንድ የኢንዲስትሪ መንደር የውጭ ኢንቨስትመንት ይስባል፣ የአካባቢ ብክለትን ይቆጣጠራል፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ያስፋፋል፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ስራ ፈጠራን ያሳልጣል። የዚህ ሁሉ ተግባሮቹ መቋጫ የህብረተሰቡን ህይወት ትርጉም በላው ደረጃ መለወጥ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል እላለሁ።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy