Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አፍሪካን ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ በጋራ መስራት ይገባል- ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

0 922

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአፍሪካን አህጉራዊ ኢኮኖሚያዊ መዋቅር በማጠናከር ተመራጭ የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ መዳረሻ ለማድረግ በጋራ መረባረብ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ፡፡

የአፍሪካና የአለም ኢንቨስትመንት ፎረም ለሶስት ቀናት በግብጽ ሻርም ኤል ሼክ ከተማ ተካሄዷል፡፡

በመድረኩ “በአፍሪካ ቻይና አጋርነት” አስመልክቶ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ የተጋበዙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፤ አፍሪካን ተመራጭ የኢንቨስትመንትና ቢዝነስ መዳረሻ ለማድረግ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ሁለንተናዊ ልማት ውስጥ የቻይና አጋርነት ጉልህ መሆኑን ያወሱት አቶ ደመቀ፥ አህጉሪቱ ካላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት እና ሰፊ የሰው ጉልበት አኳያ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ ብዙ መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ከቻይና ጋር በተፈጠረው ውጤታማ ትብብር የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ በአብነት ያነሱት አቶ ደመቀ፤ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ለማሸጋገር በመሰረተ ልማት ግንባታ፤ በትራንስፖርት፤ በሃይል ልማትና በማምረቻ ኢንዱስትሪ የቻይና ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ደመቀ በሃገሪቱ የተጀመሩ የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ ዕድሎችን የማስፋፋት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ ደመቀ ገለጻ፥ “የቻይና አፍሪካ አጋርነት በጋራ ጥቅም መርህ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ አህጉሪቱ ያሉባትን ችግሮች በመፍታት፤ ተመራጭ የኢንቨስትመንት እና ቢዝነስ መዳረሻ ለማድረግ የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል”።

በተለይ ቻይና የነደፈችው አለም አቀፍ አዲስ የትብብር ፍኖተ ካርታ ለሰው ልጅ የተመቸ ዓለም ለመፍጠር በተነደፈው ራዕይ አፍሪካ የዚህ ተጠቃሚ እንድትሆን የበለጠ መስራት እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡

በመድረኩ የተጋበዙ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በበኩላቸው ኢትዮጵያ የጀመረችው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ እና የኢንቨስትመንት ማሻሻያዎች በርካታ የውጭ ባለሃብቶችን መሳቧ ለአፍሪካ ሃገራት በምሳሌነት የሚወሰድ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy