Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በፈጣን እድገትና ድህነት ቅነሳ አርዓያ ሆናለች… የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም

0 577

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ በድህነት ቅነሳና እኩልነትን በማረጋገጥ አርዓያ መሆኗን የተባበሩት መንግሥታት ልማት ፕሮግራም ያካሄደው አዲስ ጥናት አመለከተ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገሮችን የገቢ አለመመጣጠን አዝማሚያዎች ይፋ አድርጓል፡፡

የልማት ፕሮግራሙ ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራትን የገቢ አለመመጣጠን አዝማሚያዎች አጥንቶ ለሀገራቱ የገቢ አለመመጣጠኑን መቀነስ የሚያግዙ  የፖሊሲ መመሪያዎችን ይሰጣል፡፡

ለገቢ አለመመጣጠን ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችን ለይቶ ሀገራቱ በፖሊሲዎቻቸው እንዲያካትቷቸው በማድረግ ለዘላቂ የልማት ግቦች ስኬትም  ይሰራል፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትሶዋና፣ ናሚብያ፣ ዛምቢያ፣ ማዕከላዊ አፍካ ሪፐብሊክ፣ ኮሞሮስና ሌሴቶ የገቢ አለመመጣጠን በስፋት የሚስተዋልባቸው ሀገራት መሆናቸውን ጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡

ቡርኪናፋሶ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ቡሩንዲና ጊኒ ደግሞ የገቢ መመጣጠን የሚስተዋልባቸወቅ ቀዳሚ ሀገራት ናቸው፡፡

ጥናቱ ይፋ እንዳደረገው ኢትዮጵያ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ፣ ድህነትን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስና እኩልነትን በማረጋገጥ  በአርዓያነት የምትጠቀስ ሀገር ሆናለች፡፡

የግብርና ምርትና ምርታማነት አነስተኛ ለሆነባቸው፣ የህዝብ ቁጥራቸው በማሻቀብ ላይ ለሚገኝባቸውና ተቋሞቻቸውን ተደራሽ ማድረግ ላልቻሉ ሀገራት ጠቃሚ የፖሊሲ ተሞክሮዎች እንዳሏትም ነው ጥናቱ ያመላከተው፡፡

ጥናቱ አዲስ አበባ ውስጥ ይፋ ሲደረግ የኢፌዴሪ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም ተከስተ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በመተግበር ላይ ያለው ሴፍቲኔት ፕሮግራም በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት አቻ የሌለው መሆኑን ጠቅሰው በድህነት ቅነሳውና  ገቢን በማመጣጠን እንቅስቃሴው የጎላ  አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡

በከተሞች ያለውን የገቢ አለመመጣጠን ለመቀነስ ይቻል ዘንድ ፕሮግራሙ አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች እየተተገበረ መሆንንም  አብራርተዋል፡፡

መንግሥታት ለህዝብ ቁጥር፣ ለማክሮ ኢኮኖሚ፣ ለሰብዓዊ ልማትና እድገት ትኩረት በመስጠት እኩልነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባቸውም ነው የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በጥናቱ የጠቆመው፡፡

ምንጭ፡- UNDP

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy