Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ15 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

1 1,558

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚሆን የ15 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ህብረቱ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ የገንዘብ ድጋፉ በድርቅ ምክንያት ለአስከፊ የምግብ እጥረት ለተጋለጡ አካባቢዎች የሚውል ነው።

አሁን የተደረገው የገንዘብ ድጋፍም የአውሮፓ ህብረት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ለኢትዮጵያ ያደረገውን የገንዘብ ድጋፍ 91 ሚሊየን ዩሮ ያደርሰዋል።

የአውሮፓ ህብረት መግለጫ እንደሚያመለክተው፥ አዲሱን ድጋፍ ማድረግ ያስፈለገው በሀገር ውስጥ ካለው የድርቅ ችግር በተጨማሪ ከጎረቤት ሀገራት ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ነው።

የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ እርዳታ ኮሚሽነር ክርስቶስ ስታይሊያንድስ፥ ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ያለው የድርቅ አደጋ እና በየእለቱ እየጨመረ የመጣውን የስደተኞች ቁጥር ተከትሎ ከበርካታ አቅጣጫዎች ጫና እንዳለባት እያጋጥሟት ነው የገለፁት።

ህብረቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን እና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች የመርዳት ፍላጎት አለው ያሉት ኮሚሽነሩ፥ የገንዘብ ድጋፉም የተራድኦ ድርጅቶች ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ አካባቢዎች በአፋጣኝ ምግብ እንዲያቀርቡ እና በምግብ እጥረት ምክንያት ለጤና ችግር የተጋለጡ ሰዎች አስፈላጊውን ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ ይረዳል ብለዋል።

የገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪም በድርቁ ምንክያት በሀገር ውስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ መጠለያ እና እንክብካቤ እንዲያገኙ እንዲሁም በድርቅ ምክንያት እንስሳት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል እንደሚውል ተነግሯል።

የዝናብ መጠን መቀነሱን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተለያዩ አከባቢዎች የምግብ እጥረት ተከስቶ መቆየቱ ይታወሳል።

ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ በቁጥሩ ሁለተኛ የሆነ ስድተኞች ቁጥርን በማስተናገድ ላይ ስትሆን፥ አሁን ላይ በአገሪቱ የሚገኙ የስደተኞች ቁጥር ከ880 ሺህ ይበልጣል።

እንደዚህ አይነቶቹ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ጫናዎች ተደማምረው በሀገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ የምግብ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ ላይ ይግኛሉ።

ህብረቱ በአውሮፓ ህብረት የልማት ፈንድ በኩል እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር ከ2014 እስከ 2020 የሚቆይ ለልማት ስራዎች የሚውል የ745 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

  1. milkyas tefera says

    good

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy