ሱዳን ከኤርትራ ጋር በስተምስራቅ በኩል የሚያዋስናትን ድንበርን መዝጋቷ ተገለፀ ።
በሱዳን የከሰላ ግዛት አስተዳደር ከአውሮፓውያኑ ጥር 5 2018 ጀምሮ ከኤርትራ ጋር የሚያገናኘው ድንበር መዘጋቱን የሚገልፅ አዋጅ ማውጣቱ ተነግሯል።
ድንበሩ ለምን እንደተዘጋ ማብራሪያ ባይሰጥም፥ ውሳኔው የተወሰነው ፕሬዚዳንት ኦማር አልባሽ በአውሮፓውያኑ ታህሳስ 30 በከሰላ እና በሰሜን ኮርዶፋን ግዛቶች ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ መሆኑን ተገልጿል።
የሀገሪቱ ባለስልጣናት ውሳኔው መንግስት በሁለቱ ግዛቶች ውስጥ ያሉ ህገወጥ ታጣቂዎችን ለመያዝ እያካሄደ ያለው ዘመቻ አካል ነው ብለዋል።
ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ወታደሮች፣ በርካታ ወታደራዊ ተሽከርካሪዊች እና ታንኮች የሀገሪቱ ከተሞች በማቋረጥ ከኤርትራ ጋር ወደምትገናኝበት ድንበር መሻገራቸው የተለያዩ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ኤርትራውያን በሀገሪቱ ያለውን ስርዓት በመሸሽ፥ በየዓመቱ ከሰላላ ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን በመሄድ ከዚያም በሜዲትራኒያን ባህር አድርገው ወደ አውሮፓ አደገኛ ጉዞ እንደሚያደርጉ ይታወቃል።
ምንጭ፥ AFP