Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያና ሱዳን ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

0 698

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያና ሱዳን ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ኢትዮጵያና ሱዳን ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

 የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ዛሬ ከፕሬዚዳንት ኦማር አል-በሽር ጋር ተወያይተዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ካርቱም የገቡ ሲሆን፥ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፕሮፌሰር ኢብራሂም ጋንዱር እና በሱዳን የኢፌዴሪ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙልጌታ ዘውዴ አቀባበል አድርጎውላቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ከአቀባበል ስነ ስርዓቱ በኋላ ዛሬ ዕኩለ ቀን ላይ ከፕሬዚዳንት ኦማር አል-በሽር ተወያይተዋል።

26804874_2102076876691974_1488869725156854348_n.jpg

በዚህም ዶክተር ወርቅነህ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተከታታይ ምክክር በማድረግ የሁለቱን አገራት ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር አለባቸው ብለዋል።

ሁለቱ አገሮች ያላቸውን ወዳጅነት ማጠናከር እንደሚገባቸውም ዶ/ር ወርቅነህ ገልፀዋል።

የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል-በሽር በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በማጠናከር የህዝበቸውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነታቸውን ማጎልበት እንደሚገባ ተናግረዋል።

26231284_2102094250023570_2893996080235632286_n.jpg

ፕሬዚዳንት አል-በሽር ኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ ጥቅሞች ስላላቸው ተባብሮ መስራት ይኖርባቸዋል ነው ያሉት።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ መገንባት ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአካባቢው ያሉ ሀገራት ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ሱዳን እንደምታምን ገልፀዋል።

በተያያዘ ዜና ዶክተር ወርቅነህ ከሱዳን አቻቸው ፕሮፌሰር ኢብራሂም ጋንዱር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ዶክተር ወርቅነህ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ከውይይቱ በኋላ ለሱዳን ሚዲያ፥ በአካበቢው የሚፈጠሩ ልዩነቶችን በመነጋጋር እና በውይይት እልባት ማግኘት ይገባቸዋል ብለዋል።

26733574_2102076940025301_8347707318485540257_n.jpg

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በአፍሪካ ቀንድ ዕድገት እና ብልፅግና፣ ሠላም እና መረገጋት እንዲመጣ ከሌሎች ሀገሮችም ጋር ተባብረው ይሰራሉ ነው ያሉት።

ፕሮፌሰር ጋንዱር በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ለሱዳን ስትራቴጂክ አጋር መሆኗን ተናግረዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy