Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የግንባታዎቹ ፋይዳ

0 337

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የግንባታዎቹ ፋይዳ

ዳዊት ምትኩ

በአገራችን እየተከናወኑ ያሉትን የኤርፖርት ግንባታዎች የፈጣን ዕድገታችን አመላካቾች ናቸው። ግንባታዎቹ በአቪየሺን ኢንዱስትሪ ውስጥ ተወስኖ የቆየውን የአየር ትራንስፖርት በማሳለጥ እንዲሁም ለአገራችን ምጣኔ ሃብት የሚኖራቸውን ሚና ቀላል አይደለም። በየአካባቢው በመገንባት ላይ የሚገኙት ኤርፖርቶች ኢኮኖሚውን ከማቀላጠፍ አኳያ በተለይም ህብረተሰቡ ኤርፖርቶቹ በአቅራቢያው መገንባታቸው ምክንያት ሊያገኝ ከሚችለው ጥቅም አኳያ ፋይዳቸው ከፍተኛ ነው።

እንደሚታወቀው ሁሉ የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ለብቻው ሳይሆን ከተቀናጀ የትራንስፖርት አሰራር ጋር የተያያዘ ነው። ባለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት ለትራንስፖርት ልማት በተሰጠው ትኩረት በመንገድ፣ በአቬሽንና አየር ትራንስፖርት፣ በባህር ትራንስፖርትና ማሪታይም አገልግሎት፣ በቅርቡ ደግሞ በባቡር ትራንስፖርት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተካሂዷል፡፡ በዚህም የአገራችን የትራንስፖርት ዘርፍ ጉልህ ዕድገት አስመዝግቧል፡፡

በቀጣዩ የዕቅድ ዘመን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፉ ከዚህም በላይ መሠረታዊ ለውጥ እንዲያሳይ ለማድረግ ታቅዷል፡፡ ዘርፉ ከሚጠይቀው ከፍተኛ ሁለንተናዊ አቅም አንጻር ግልፅ በሆነ ራዕይና የተቀናጀ የትራንስፖርት ስትራቴጂ ወይም ማስተር ፕላን መምራት ይኖርበታል፡፡

ስለሆነም በቅድሚያ የእስካሁኑ አፈፃፀማችን፣ የቀጣዩ ጊዜ የልማት ራዕያችንን እና የዓለም ምርጥ ልምድን መሠረት በማድረግ ወቅታዊ የሆነ የተቀናጀ አገራዊ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ስትራቴጂ/ማስተር ፕላን ተቀርፆ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ ስትራቴጂው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ፕሮግራሞችን የሚመራና የሚያቀናጅ ሲሆን በየዘርፉ የሚከናወነው ልማትም ይህንን የተቀናጀ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ማስተር ፕላን መሠረት ያደረገ ይሆናል፡፡

የባህር ትራንስፖርትና ሉጀስቲክስ አገልግሎት አገሪቱ ለነደፈችው የማኑፋክቸሪንግ ኢንነዱስትሪ ትራንስፎርሜሽንና የኤክስፖርት ልማት መስፋፋት ከሚጫወተው ቁልፍ ሚና አኳያ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ሲሆን የባህር ትራንስፖርት ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት ተልእኮ እውን ለማድረግ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የሚከናወኑ የሺፒንግ፣ ሎጂስቲክስና ድጋፍ ሰጪ ዋና ዋና ተግባራትን በተቀናጀ ሁኔታ ለአገልግሎት ሰጪና ለተገልጋይ አካላት የተሟለና ወጥነት ያለው ወቅታዊና ተደራሽ የሆነ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፡፡

ከፍ ብሎ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን መሠረት በማድረግ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ተፈፃሚ የሚደረጉ ግቦች ተጥለዋል፡፡ እነዚህም በዓለም አቀፍ የሎጅስቲክስ የአፈፃፀምመለኪያ ከ2 ነጥብ 59 ወደ 3 ነጥብ 07 ከፍ ማድረግ ወይም በዓለም የሀገሪቱን ደረጃ ከ104ኛ ወደ 57ኛ ማሻሻል፣ የገቢ እና ወጪ ዕቃዎችን የትራንዚት ጊዜበ 50 በመቶ መቀነስ፣ የገቢ እቃዎች የባህር ወደብ ላይ አማካይ የቆይታ ጊዜን አሁን ካለበት 40 ቀናትወደ 3 ቀናት ዝቅ ማድረግ በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት የሚጓጓዘውን የሀገሪቱ የጀኔራል ካርጐ ሽፋንን በዕቅዱ መነሻ ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 90 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነው።

ከሀገሪቱ በኮንቴይነር ሊጓጓዝ የሚችል የወጪ ጭነት በሀገር ውስጥ በኮንቴይነር አሽጐ መላክን ከ7 በመቶ ወደ 100 በመቶ ማድረስ፣ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ደህንነትንና ሴፍቲን በ50 በመቶ በማሳደግ የካርቦን ልቀትን 10 በመቶ መቀነስ፣ አንድ የጭነት ተሽከርካሪ ዓመታዊ የኪሎ ሜትር ሽፋን በ2007 ከደርሰበት 99 ሺህ 900 በ2012 ዓ.ም ወደ 121 ሺህ ከፍ እንዲል ለማድረግ እየተሰራ ነው።

የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ለማግኘት አማካይ የመጠበቂያ ጊዜን ከ30 ወደ 15 ደቂቃ ዝቅ ማድረግ፣ አንድ የአገር አቋራጭ አውቶቡስ ዓመታዊ የኪሜ ሽፋን ከ100,000 ወደ 105,000 ከፍ እንዲል ማድረግ፣በአገር አቀፍ ደረጃ በዓመት የተጓጓዙ ተሳፋሪዎች ብዛት በ2007 ከነበረበት 322 ሚሊዮን በ2012 ወደ 370 ሚሊዮን ከፍ እንዲል ማድረግ፣ በትራፊክ አደጋ ምክንያት በየ10 ሺህ ተሸከርካሪ የሚደርሰውን የሞት አደጋ በዕቅዱ መነሻ ዓመት ከነበረበት 58 በመቶ በ2012 ወደ 27 ዝቅ እንዲል ለማድረግ ስራዎች ተጀምረው አጥጋቢ ውጤት እያስገኙ ነው፡፡

እናም የአገራችን አቪየሽን ኢንዱስትሪ ከተቀናጀ የሎጀስቲክስ አሰጣጥ ስርዓት ተለይቶ የሚታይ እንዳልሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በተለይም ዘርፉ በየአካባቢው የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ እያካሄደ መሆኑ የሚያስገኘው ጥቅም ከፍተኛ ነው።

እንደሚታወቀው ሁሉ የኢትዮጵያ የአቪየሽን ባለስልጣን የሚያሰገነባቸው ግንባታዎች የመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ በርካታ መንግስታዊ አገልግሎቶችን የሚያካትት በመሆኑ እያንዳንዱ የሚመራበት ፖሊሲዎና ስትራቴጂዎች ያሏቨው ናቸው፡፡ ፖሊሲውና ስትራቴጂው የመንግስትን አጠቃላይ የልማት ፕሮግራም ውጤታማ ለማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ዓብይት የትኩረት አቅጣጫዎችም ተሰጥተውታል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ በየጊዜው የተዘጋጁትን የመንገድ ልማት ፕሮግራሞችን ለማስረፅ፤ በግንባታውም ይበልጥ ትኩረት ለገጠር ለመጋቢና ማህበረሰባዊ መንገዶች በመስጠት የገጠር ከተማ ትስስርን የማጠናከር፣ አግባብ ያላቸው ስልጠናዎች የመስጠት፣ የተሻሻሉ የመንገድ ዲዛይኖችን የመተግበር እንዲሁም ግልጽና ወቅታዊ የትራፊክ ደንቦችን ስራ ላይ የማዋሉና ተፈጻሚ የማድረግ ተግባራት ይገኙባቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የመንገድ ደህንነትን የማስጠበቅ፣ በትራንስፖርት ዘርፍ የግሉን ክፍል ኢኮኖሚ ይበልጥ ተሳታፊ የማድረግ እንዲሁም በህዝብ ቁጥር ማደግ፣ በከተሞች መስፋፋትና ከተማና ገጠርን ለማገናኘት ጊዜው የሚጠይቀው የህዝብ ትራንስፖርትን የማስፋትና ውጤታማ የማድረግ ብሎም የግብርና እና የፋብሪካ ምርቶችን ገበያ እንቅስቃሴ ቀልጣፋ እንዲሆን ማስቻል የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡ በዚህ ረገድ የአቪየሽን መዳረሻዎች እንዲሰፉ መደረጉ ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡

የአቪየሽን ግንባታው ፕሮግራሞች ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ የመንግስት ትኩረት ካገኙና ውጤታማ ከሆኑ የልማት ተግባራት መካከል ናቸው፡፡ በተለይም በበርካታ አካባቢዎች ግንባታቸው እየተካሄደ በመሆኑ ለአካባቢው ነዋሪ ጠቀሜታ ይፈጥራሉ፡፡ በየአካባቢውም ግንባታዎቹን ተከትሎ ከተማዎች መስፋፋታቸው አይቀርም፡፡ ይህም ከዚህ ቀደም ሰው የማይኖርባቸው አካባቢዎች የስራ ዕድልን ፈጥረው ሰዎች ዘላቂ ኑሯቸውን እንዲመሰርቱ ያደርጋል።

የዜጎች ተጠቃሚነት በዘመናዊ መንገድ እንዲተሳሰርም ያደርጋል። የመረጃ ልውውጡም ቀላል አይሆንም። ዛሬ ደረጃቸውን የጠበቁ የአየር ማረፊያዎች እየተገነቡ ነው። ግንባታዎቹ ዘመናዊ ገጽታን የተላበሱ የዘመናዊነት መገለጫ ናቸው፡፡ በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተገነቡት የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎች ዘመናዊ ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ለየከተማቹ ውበትና ድምቀት ናቸው፡፡

እነዚህ የአውሮፕላን ማረፊያዎች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እና የዲፕሎማሲ መልህቅ ለሆነችው አገራችን ቱሪዝምም የሚኖራቸው አስተዋጽኦ በቀላሉ የሚገመት አይሆንም፡፡ ለስራ ጉዳይ ወደ አገራችን ብቅ የሚሉ አፍሪካዊያንነና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አካላት እግረ መንገዳቸውን አገራችንን ለመጎብኘት ሲያስቡ ግንባታዎቹ ማለፊያ መዳረሻዎች ይሆናሉ፡፡ እናም የግንባታዎቹ ፋይዳ ዘርፈ ብዙ በመሆኑ ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል እላለሁ፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy