Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ድርቅና የምርት ዕድገት

0 320

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ድርቅና የምርት ዕድገት

                                                       ደስታ ኃይሉ

በአገራችን በአሁኑ ወቅት ይሰበሰባል ተብሎ የሚጠበቀው ምርት ከፍተኛ ነው። ይህም ምርት ብክነትን በሚቀንስ መልኩ ተሰብስቦ ወደ ገበያ ሲወጣ በአንዳንድ የአገራችን ክፍሎች የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ያስችላል።

ከዚህ በተጨማሪም መንግስት በአርሶ አደሩ አነስተኛ ማሳ ላይ በሚከተለው የማስፋት ስትራቴጂ ምርትን የሚያሳድግ መሆኑን ማረጋገጥ የተቻለበትና በዘላቂነትም በየጊዜው የሚከሰተውን ድርቅ ትርፍ አምራች ከሆኑት አካባቢዎች ወዳልሆኑት በማዘዋወር በዘላቂነት የድርቅን ተጠቂነት በዘላቂነት ሊቀርፍ ይችላል።

ድርቅን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቅረፍ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ስትራቴጂው በኩል እየተደረገ ያለውን ጥረት መመልከት ይቻላል። ከአረንጓዴው ልማት ስትራቴጂ መሰረቶች ውስጥ የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን፣ የደን ልማት፣ ታዳሽ ሀይል አማራጭ መከተል እንዲሁም የትራንስፖርት፣ የኢንዱስትሪ የቤት ልማትን በተስማሚ ቴክኖሎጂ መተግበር የሚሉት ጉዳዩች በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው። የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ፣ ኢትዮጵያ ያቀደችውን የተለጠጠ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማሳካትና የሙቀት አማቂ ጋዞችን መቀነስ የሚያስችሉ አማራጮችና ዕድሎችን መለየት ዋናው አለማው ነበር፡፡ መንግስት በዘርፉ የተሻለ ልምድ ያላቸውን የልማት አጋር አካላትን ለመሳብ ጥረት እንደሚደረግም ስትራቴጂው ያመለክታል፡፡

ሀገራችን በተለመደው የኢኮኖሚ ዕድገት አማራጭ ብትጓዝ በ2002 ዓ.ም የነበራት 150 ሚልዮን ቶን የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት በ2022 ዓ.ም ከዕጥፍ በላይ በማደግ 400 ሚልዮን ቶን ይደርሳል፡፡

የልማቱ አማራጭ አብዛኛውን የአገሪቱን ጠቅላላ ምርት ነዳጅና ተመሳሳይ የሀይል ምንጮችን ከውጭ በማስገባት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ሀገሪቱን ለውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ይዳርጋታል፡፡ ከታዳሽ ሀይል በተለይም ከውሃ ሀይልን በማመንጨት በተነጻጻሪ ከሌሎች ሀገራት ቀድማ አረንጓዴ ልማትን መተግበር የጀመረችው ኢትዮጵያ፣ ሀገሪቱ ለአየር ንብረት ለውጥ ያላትን ተጋላጭነት በፍጥነት የአረንጓዴ ልማት ማስፈጽሚያ ስትራቴጂ ቀርጻለች፡፡

የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን፣ የደን ልማት፣ ታዳሽ ሀይል አማራጭ መከተል እንዲሁም የትራንስፖርት፣ የኢንዱስትሪ የቤት ልማትን በተስማሚ ቴክኖሎጂ መተግበር የአገሪቱ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂው መሰረቶች ናቸው፡፡ የስትራቴጂው መሰረቶች አተገባበር እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

የመጀመሪያው የስትራቴጂው መሰረት የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን ነው፡፡ ዘርፉ የአገሪቱ ኢኮኖሚ መሪ ዘርፍ መሆኑና የአብዛኛው የሀገሪቱ ዜጎች መተዳደሪያ መሆኑ ልዮ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል፡፡

የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ ከዚህ ቀደም በተለምዶ እንደሚደረገው የሚታረስ መሬትን ማስፋፋትና የቀንድ ከብቶችን ቁጥር ከማሳደግ ይልቅ የመሬትንና የቀንድ ከብቶችን ምርታማነት ማሳደግ የአረንጓዴ ልማት አቅጣጫ ነው፡፡

የተሻሻሉ የሰብልና የቀንድ ከብት ዝርያዎችን አርሶ አደሩ እንዲጠቀም ማድረግ የግብርና ዘርፍ ማሳደጊያ ሰልት ነው፡፡ የደን ጭፍጨፋን ለመቀነስ በተለይም በተራቆቱና በተጎዱ አከባቢዎች ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እንዲሁም ከፍተኛ የመስኖ ልማት ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋትም በስትራቴጂው የተያዘ ዕቅድ ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂው የተመሰረተው የደን ሃብት ልማት ላይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ፤ ደን 80 በመቶ ለሚሆኑ በተለይም በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል ለሚኖሩ ዜጎች የኃይል ምንጭ ነው፡፡

ከዚህ ንብ በማነብ፤ የጫካ ቡና እና ከጣውላ የሚገኘው ምርት የጠቅላላ ሀገራዊ ምርትን 4 በመቶ ድርሻ ይዛል፡፡ በተለይም የአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ ብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ እንዲሁም ለአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሆኑትን ሙቀት አማቂ ጋዞችን በማምከን ረገድ የደን ዘርፉ የማይተካ ሚና አለው፡፡

ለአገር ውስጥና ለአከባቢያዊ ፍጆታ የሚያስፈልገውን የኤሌክትሪክ ሀይል ፍጆታን፤ ከታዳሽ የሀይል ምንጮች ማስፋፋት የስትራቴጂው ሶስተኛ መሰረት ነው፡፡ ኤሌክትሪክ ለዘመናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ የሀይል ምንጭ ነው፡፡

ከከተሞችና እንዱስትሪዎች የሀይል ፍጆታ አንስቶ ለመስኖ የሚያስፈልገውን ውሃ ለመግፋት ይዉላል፡፡ በአማካይ ከ10 በመቶ በላይ የሚያድገው የሀገሪቱ አኮኖሚ በአመት ከ14 በመቶ በላይ የኤሌክትሪክ ሀይል ያስፈልጋል፡፡

እንደሚታወቀው ሀገራችን ከታዳሽ የሀይል ምንጮች ብቻ 60 ሺህ ሜጋ ዋት ማመንጨት የሚያስችል ዕምቅ አቅም አላት፡፡ ከዚህም ውስጥ የሀይድሮ ዘርፉ 45 ሺህ ሜጋዋት በመያዝ ፣የታዳሽ ሀይል ምንጭ 75 በመቶ ድርሻ ይዟል፡፡ ከጂኦተርማል፣ ከንፋስና ከፀሀይ የሚገኘው ቀሪውን 25 በመቶ ድርሻ ይይዛሉ፡፡

ኢትዮጵያ ያላትን ታዳሽ የሀይል አማራጭ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የተረፈውን ደግሞ ወደ ውጭ በመላክ 50 ሚልዮን ቶን ለአየር ንብረት ዋነኛ መንስዔ የሆኑት ሙቀት አማቂ ጋዞችን መቀነስ ትችላለች፡፡

ሌላው አማራጭ ታዳሽ ሀይል አማራጭ ነው፡፡ አማራጩ ነዳጅና ድንጋይ ከሰልን የመሰሉ የሀይል አማራጮች ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ቀላል አይደለም፡፡ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ዕቅድን አውጥቶ መዋዕለ-ንዋይ ማፍሰስን ይጠይቃል፡፡

ሀገራችን ያቀደችው የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ካላት ዕምቅ የታዳሽ ሀይል አማራጭ ጋር ተዳምሮ ሀገሪቱ አሁንና ወደ ፊት የሚያስፈልጋትን የሀይል አቅርቦት ችግር እንዳይገጥመው ዋስትና ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ መካከለኛ ገቢ ያላት ሀገር ለመፍጠር ያላትን ውጥን ላማሳካት፤ የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂው የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡

ሀገራችን የነደፈቻቸው የአረንጓዴ ልማት አማራጮች የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ለአየር ንብረት ለውጥ መንስዔ የሆኑትን የሙቀት አማቂ ጋዞችን መቀነስ ላይ ያተኮራል፡፡ በዚህም አረንጓዴ የዕድገት አማራጭ መከተሏ እስከ 2022 ዓ.ም ድረስ ታመነጭ የነበረውን 250 ሚልዮን ቶን ሙቀት አማቂ ጋዞች ወደ ህዋው እንዳይቀላቀል ትከላከላለች፡፡ ይህ ደግሞ በተጠቀሰው ጊዜ ከተለመደው ዕድገት አማራጭ አንጻር የሚመነጨውን ሙቀት አማቂ ጋዞች 64 በመቶ መቀነስ ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በተለመደው የዕድገት አማራጭ 1 ነጥብ 8 ቶን ይደርስ የነበረውን የነፍስ ወከፍ የማመንጨት መጠን የአረንጓዴ የዕድገት አማራጭን በመጠቀም ወደ 1 ነጥብ 1 ቶን ማድረስ ይቻላል፡፡ የአረንጓዴ ልማት የዕድገት አማራጭ አለም አቀፉን ሙቀት አማቂ ጋዞች ከማስወገድ በተጨማሪ ለአከባቢው ሀገራት ትርፍ የኤሌክትሪክ ሀይልን በርካሽ ዋጋ ማቅረብ አስችሏታል፡፡

ከአረንጓዴው ልማት በተጨማሪም ኢትዮጵያ የግብርና ምርቱ ድርቁን እንዲቋቋም እየሰራች ነው። አርሶ አደሩ ከራሱ ተርፎ ለገበያ በማምረት ተጠቃሚ የሚሆንበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ፣ ሀገሪቱም ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ ጎዳና እንዲፈጠር አድርጓል። ለዚህ ስኬት በመንግስት በኩል የተወሰዱት እርምጃዎች በቂ ማሳያዎች ናቸው ማለት ይቻላል።

እንደሚታወቀው ሁሉ ኢትዮጵያ ለእርሻ የሚውል ሰፊ መሬት አላት። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች በአርሶ አደሩ እጅ እንዳለ የሚታሰበው መሬት አነስተኛ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ካለችውም መሬት ቢሆን የሚያገኘው ምርት ዝቅተኛ ነው። አመራረቱም እጅግ ኋላ ቀር ሆኖ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት ግን ይህ ተቀይሮ አርሶ አደሩ ከተጠበቀው በላይ ምርት እያመረተ ነው።

ይህም በድርቅ ለተጎዱት አካባቢዎች ትርፍ አምራች አርሶ አደሮች እንዲሸፍኑ የሚያስችል ነው። ድርቅን በአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ የመቅረፍ ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ ምርትን በማሳደግም ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን መደገፍ ይቻላል። በአሁኑ ወቅት ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው ከፍተኛ ምርትም ይህን ሁኔታ በማካካስ ረገድ የራሱ ሚና አለው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy