Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዶክተር ወርቅነህ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጉብኝት እያደረጉ ነው

0 663

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

 የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ገብተዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ዱባይ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢፌዴሪ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር አቶ ተጀበ በርሄና ሌሎች ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በነገው እለትም ከአገሪቱ አቻቸው ሼክ አብዱላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን እንዲሁም ከሰራተኛና የሰው ሃብት ሚኒስትር ጋር የሁለቱን አገራት ግንኙንት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመስከረም ወር በተካሄደው 72ኛው የተመድ ጉባኤ ወቅት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የጎንዮሽ ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ግንኙነት ከተጀመረ የቆየ ቢሆንም ኢትዮጵያ ቆንስላዋን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2004 በዱባይ የከፈተች ሲሆን፥ ኤምባሲዋን ደግሞ በ2014 በአቡ ዳቢ ከፍታለች።

የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ደግሞ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2010 ነበር ኤምባሲዋን በኢትዮጵያ የከፈተችው።

የኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የንግድ ግንኙነት ከ10 ዓመት በፊት ከነበረበት 45 ነጥብ 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ዶላር ባሳለፍነው የፈረንጆች 2016 ዓመት ከ809 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላርመብለጡን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያስረዳል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy