Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በኢትዮጵያ የሽብር ድርጊት ለመፈፀም ከኤርትራ ስልጠና ወስደው የገቡ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

0 340

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኢትዮጵያ የሽብር ድርጊት ለመፈፀም ከኤርትራ ስልጠና ወስደው የገቡ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በኤርትራ ሀረና ተብሎ በሚጠራ ስፋራ ግንቦት 7 የተባለውን የሽብር ድርጅት በመቀላቀልና ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ በኢትዮጵያ የሽብር ድርጊት ሲፈጽሙ የተያዙት አምስት ግለሰቦች ከ14 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ።

ተከሳሾቹ ዮሃንስ መንግስቴ፣ ጸጋዬ ዘለቀ፣ ጋሻው ሙንዬ፣ ማንአስቦት ብርሀኑ እና አስማረ ግለጥ የተባሉ ናቸው።

ግለሰቦቹ ራሱን ግንቦት 7 ብሎ በሚጠራው የሽብር ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ በኤርትራ ስልጠና በመውሰድና የጦር መሳሪያዎችን፣ ጥይቶችንና ቦምቦችን በመያዝ ለሽብር ተልእኮ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን አቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ክስ ያስረዳል።

የከሳሽ አቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ግለሰቦቹ በሰሜን ጎንደር ዞን አርማጭሆ ወረዳ ዘመነወርቅና መተማ ወረዳ ላይ በአርሶ አደሮች ላይ ተኩስ ከፍተዋል።

በዚህም 1 ሰው ህይወቱ ሲያልፍ ሁለት ግለሰቦችን አቁስለው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስረዳል።

በዚህም መሰረት ከሳሽ አቃቤ ህግ በግለሰቦቹ ላይ በሽብር ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋኝል።

የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛው የወንጀል ችሎትም ክሱ ለተከሳሾቹ እንዲደርሳቸው ካደረገ በኋላ ተነቦላቸው እንዲረዱት ተደርጓል።

ተከሳሾቹ በሰጡት የእምነት ክህደት ቃልም የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምንም ጥፋተኛም አይደለንም በማለት ክደው ተከራክረዋል።

ይሁን እንጂ ግለሰቦቹ የከሳሽ አቃቤ ህግን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች መከላከል ባለመቻላቸው ጥፋተኛ ተብለዋል።

በዚህም መሰረት 2ኛ ተከሳሽ ጸጋዬ ዘለቀ ለፍርድ ቤቱ ሁለት የቅጣት ማቅለያ በማቅረቡ በ14ት ዓመት ፅኑ እስራት ሲቀጣ ሌሎቹ አራቱ ተከሳሾች በ15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

በሰለሞን ጥበበስላሴ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy