Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ የውጭ ጉዲፈቻን በአዋጅ ከለከለች

0 412

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የውጭ ጉዲፈቻን የሚከለክለው አዋጅ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል።

በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ 213/1992 አንቀፅ 193 እና 194 ላይ የውጭ ጉዲፈቻ እንደ አማራጭ መቀመጡ በህፃናት ላይ ለሚፈፀሙ የተለያዩ ወንጀሎች በር ከፍቷል ተብሏል።

ከምክር ቤቱ አባላት ለህፃናት ምቹ እና በቂ ማሳደጊያዎች ሳይዘጋጁ የውጭ ጉዲፈቻን መዝጋቱ ተገቢ አለመሆኑ ተነስቷል።

በአንፃሩ በውጭ ጉዲፈቻ ስም በህፃናቱ ላይ ከሚፈፀም ህገወጥ ዝውውር እና የመብት ጥሰት ጋር ሲወዳደር የውጭ ጉዲፈቻን ማቆሙ የተሻለ ነው የሚል ሀሳብ የሰነዘሩም የምክር ቤት አባላት አሉ።

በምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ቋሚ ኮሜቴ ሰብሳቢ አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት በበኩላቸው፥ በኢትዮጵያ የሚሰሩ በርካታ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ህብረተሰቡ ህፃናቱን በአገር ውስጥ ጉዲፈቻ ተቀብሎ የማሳደግ ተነሳሽነት እያሳየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በመሆኑም የውጭ ጉዲፈቻን ማስቀረቱ በህፃናት ላይ የሚደርሰውን የማንነትና የስነ ልቦና ቀውስ ለማስቀረት ያግዛል ነው ያሉት ሰብሳቢው።

አዋጁ የህፃናት ጉዳይ ፖሊሲውን በተሟላ ሁኔታ ለማስፈፀምና ህፃናት በሀገራቸው ባህል፣ ወግና ልማድ ታንፀው እንዲያድጉ ለማድረግም ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው መደበኛ ስብሰባ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅን እና የፌዴራል የፍትህ፣ የህግ ምርምር እና ስልጠና ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ አዋጅንም አፅድቋል።

በፋሲካው ታደሰ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy