Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የህዝባዊ አጋርነት መገለጫ

0 366

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የህዝባዊ አጋርነት መገለጫ

                                                  ታዬ ከበደ

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ማብራሪያ ከሰጠ ወዲህ በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ የሚገኙ አገልግሎቶች አሰጣጥ እየተሻሻሉ ናቸው። ይህም ኢህአዴግና መንግስት እንደ ወትሮው ለዝቅተኛው የህዝብ ክፍል ያላቸውን አጋርነት ያሳዩበት ነው።

ከማብራሪያው ወዲህ በየዘርፎቹ የሚገኙ አገልግሎቶች ተደራሽነታቸው መጨመሩን (ስኳር፣ ዘይትና የመሳሰሉት መሰረታዊ ሸቀጦች እንዲቀርቡ መደረጋቸው) እንዲሁም የዋጋ ግሸበትን ለመቀነስ ጥረት እየተደረገ ነው። ይህም ኢህአዴግና መንግስት እንደ ወትሮው ለህዝቡ ያላቸው አጋርነት መገለጫ ነው ማለት ይቻላል።

በተለይም የህዝቡን ኑሮ እየተፈታተነ የሚገኘው የዋጋ ንረት እዚህ ላይ መነሳት ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል። መንግስት በጥቂት ጊዜ ውስጥ የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት እየወሰዳቸው ያሉት ርምጃዎች የሚያበረታቱ ናቸው።

እንደሚታወቀው ሁሉ በተለይም የብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያውን ተከትሎ ሊፈጠሩ የሚችሉ ስጋቶችን ለመከላከል መንግስት ተገቢውን ጥረት እያደረገ ነው። መንግስት ምንም ዓይነት የነዳጅና የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እየሰራ ነው።

በአሁኑ ወቅት ከመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎችና ሸቀጦች ስርጭት አኳያም መንግስት ስንዴን፣ ዘይትንና ስኳርን ጨምሮ እና የዋጋ ንረት እና እጥረት እንዳይከሰት የዋጋ ቁጥጥር ማድረግ ጀምሯል። በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ ምንም ዓይነት የታሪፍ ጭማሪ እንዳይደረግ ጥረት እየተደረገ ነው።

አገሪቱ ለድርቅ ያልተጋለጠችበትና ከፍተኛ የመኸር ሰብል ምርት በሚገኝበት ጊዜ እንዲደረግ መወሰኑ በገበያው ያለውን የምርት መጠን እንዳይጓደል እና የእህል ዋጋ ንረት እንዳይኖር የሚያደርግ ነው።

ከውጭ የመጡ ምርቶችን በመጋዘን አከማችተው ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ነው። እርምጃ የመውሰድ ስራውም ተጠናክሮ ይቀጥላል። ገበያውን ለማረጋጋት የጅምላ መሸጫ ሱቆች መሰረታዊ ሸቀጦችን በበቂ ሁኔታ እንዲያቀርብ ይደረጋል።

ይህ ሁሉ የመንግስት ጥረት ህዝቡ በዋጋ ንረት እንዳይጎዳ ለማድረግ የታሰበ መሆኑ ግልጽ ነው። እርግጥ ለዜጎቹ ሃላፊነት የሚሰማው መንግስት የሚያደርገው ይህንኑ ነው። መንግስት ለህዝቡ የገባውን ቃል መቼም አጥፎ ስለማያውቅ ይህንንም በማድረግ ሃላፊነቱን እንደሚወጣ በተለያዩ ጊዜያት የፈፀማቸው ተግባራት ህያው ምስክር ናቸው።

በተለያዩ ወቅቶች መንግስት የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት ተከታታይ የሆኑ ልማታዊ እርምጃዎችን በመውሰድ የህዝቡን ጥያቄ መልሷል። የዋጋ ግሽበቱ ባለ ሁለት አሃዝ በነበረበት በዚያ ወቅት፤ ህብረተሰቡ እንዳይጎዳ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ እንዲሁም መሰረታዊ የሆኑ የፍጆታ ዕቃዎችን ራሱ በማስገባትና በሸማቾች ማህበራት አማካኝነት አከፋፍሏል።

እንዲሁም ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገዛበትን እንደ “አለ በጅምላ” ዓይነት የአቅርቦት ቦታዎችን በመክፈት የህዝቡን ጥያቄዎች የመለሰና በመመለስ ላይ የሚገኝ መንግስት ነው። ይህም የኢፌዴሪ መንግስትን ህዝባዊነትና ሁሌም ቢሆን ለህዝቡ የገባውን ቃል የማያጥፍ መሆኑን የሚያመላክት ነው።

እርግጥ ቀደም ሲል የጠቀስኳቸው ምሳሌዎች እጅግ ከሚበዛው የመንግስት ተግባራት ውስጥ እፍኝ ያህሉን ነው። ምንም እንኳን እነዚህ መንግስታዊ ህዝባዊነት ምሳሌዎች ቢሆኑም፤ ዋናውንና መንግስት ለህዝቡ የሀገባውን ቃል የማያጥፍና ሁሌም ተግባሮቹን የሚያከናውነው ህዝቡን መሰረት ባደረገ አኳኋን መሆኑን ማሳያዎች ናቸው።

ታዲያ ይህን የመንግስት የገንዘብ ምንዛሬ ለውጥ በተገቢው ሁኔታ መረዳት ይገባል። በአሁኑ ወቅት ምጣኔ ሃብታችን በፍጥነት እያደገ ነው። አሁን ባለንበት ሁኔታ በኤክስፖርትና በኢምፖርት መካከል ክፍተት መኖሩ ግልፅ ነው። ጉድለቱ እየሰፋ መጥቶ የተጠቀሰው ደረጃ ላይ መድረሱ ግን ያሳስባል፡፡

በእነዚህ ዓመታት የታየው ደካማ የኤክስፖርት አፈፃፀም አስተማማኝ የውጪ ምንዛሪ ግኝት በማረጋገጥ ለፈጣን ዕድገታችን አስፈላጊ የሆኑ መሣሪያዎችና ዕቃዎች ከውጪ በማስገባት ዕድገታችን ለማስቀጠል አና ከውጪ ብድርና ዕርዳታ ጥገኝነት ለመላቀቅ ትልቅ ማነቆ ቢሆንም ችግሩ በህዝቡ ላይ ሳንካ እንዳይፈጥር መንግስት ከምን ጊዜውም በላይ እየሰራ ነው፡፡

በሌላ በኩልም መንግስት የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደ አማራጭ ወስዶ የሰራ  ነው። ዛሬ ምርትና ምርታማነት በማደጉ ሳቢያ የአርሶ አደሩ ህይወት በአያሌው እየተለወጠ ነው። እንዲያውም በአንዳንድ አካባቢ የሚገኙት አርሶ አደሮች ትርፍ አምራች እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።

ይህ ትርፍ አምራችነታቸውም ከተጠቃሚነታቸው ባሻገር ሌሎች አካባቢዎች በተፈጥሮአዊው የድርቅ አደጋ በሚጠቁበት ወቅት የሚፈጠረውን ክፍተት እየሞሉ ነው። ምርትና ምርታማነት በማደጉ ሳቢያ ከፍተኛ ምርት እንደሚገኝ ይታሰባል።

ተባዮችን በባህላዊ መንገድ መከላከል ከአቅም በላይ በሚሆንበት ወቅትም ፀረ- ተባይ ኬሚካሎችን በመርጨትና በመከላከል በአሁኑ ወቅት በጥሩ ሁኔታ ማሳ ላይ የሚገኘውን ምርት ወደ ጎተራው እስኪገባ ድረስ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ርብርብ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በተለይ የሚገኘው ምርት በተምች ወረርሽኝ እንዳይጠቃ ብርቱ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል።

ይህን ጥረት የሁሉም አካል መሆን አለበት። ለመንግስት ወይም ለአርሶ አደሩ ብቻ የሚተው አይደለም። ሁሉም በኃላፊነት ንፈስ ሊንቀሳቀስ ይገባል። ይህ ሲሆንም ምርቱ የሚጠበቀውን ያሀል ይሆንና በምንዛሬ ለውጥ ሳቢያ ለሚፈጠረው የዋጋ ንረት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል።

በግብርናም ምርታማነቱ መሻሻል ያሳየ ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ ባለመድረሱ ለኤክስፖርት የምናቀርባቸው የግብርና ውጤቶች በመጠን፣ በጥራትና በዓይነት ውሱን ናቸው ማለት ይቻላል። ታዲያ እነዚህን ሁኔታዎች ለመቀየር መንግስት ጥረት እያደረገ ነው። ለዚህ ደግሞ ተገቢው ትኩረት ተደርጎ የተገኘውን የግብርና ምርት በአግባቡ ሰብስቦ ጥቅም ላይ ለማዋል እየተረባረበ ነው።

በአሁኑ ወቅት የተገኘው የግብርና ምርት እድገት ምርቱን በአግባቡ ለመሰብሰብ መንግስት ጥረት እያደረገ ነው። እየወሰዳቸው ካሉ የዋጋ ማረጋጋት ስራዎች በተጨማሪ ምርቱ የነበረውን ክፍተት በመሸፈን የአገር ውስጥ ገበያን እንዲረጋጋ እየሰራ ነው። ይህም ህዝቡ እንዳይጎዳና በሀገር ውስጥ ምርቶች እንዲጠቀም የሚያደርግ ነው። እናም በእኔ እምነት እነዚህ ጉዳዩች የመንግስት ህዝባዊ አጋርነት መገለጫ ይመስሉኛል። ተጠናክረው መቀጠልም አለባቸው።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy