Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የጉብኝቱ አንድምታ

0 282

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የጉብኝቱ አንድምታ

                                                    ደስታ ኃይሉ

ሰሞኑን የዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ክርስቲን ላጋርድ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው ነበር። ይህ ጉብኝት ትርጉም ያለው ነው። ጉብኝቱ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ስራ ላይ መሆናቸውን፣ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትን እየሳቡ መሆናቸውን፣ እዚህ አገር ውስጥ በርካታ የስራ ዕድል እየተፈጠረ እንደሆነና የአገራችን ኢኮኖሚ ማገር የሆነው የግብርና ስራችን ስኬት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ምክንያት የተደረገ ነው ማለት ይቻላል። የእነዚህ ስኬቶች ባለቤት የሆነው የአገራችን ህዝብ ስራ ላይ የሚገኝ ባተሌ በመሆኑ ለነውጥና ለሁከት ምንም ዓይነት ጊዜ የሌለው መሆኑንም የሚገልጽ ይመስለኛል።

የዋና ዳይሬክተሯ ጉብኝት መነሻው ስኬቶቻችን ናቸው። እንደሚታወቀው ሁሉ ግብርና እስካሁን ድረስ የሀገራችን ኢኮኖሚ ምሶሶ ነው። በግብርናው መሪነት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በተከታተለ ባለ ሁለት አሃዝ ፍጥነት የሚያድግ እንዲሁም የአብዛኛውን የአገሪቱን ነዋሪ ህዝብ ህይወት ትርጉም ባለው ደረጃ መለወጥ የቻለ ነው። ይህ ዕድገቱም ኢንዱስትሪው የመሪነት ሚናውን እስከሚረከብ ድረስ የሚቀጥል ነው።

ግብርናው በሀገሪቱ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ እምቅ ሃብት ነው። ይህ ሃብት ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል እየፈጠረ ሲሆን፤ ገና ምንም ያልተነካ እምቅ በመሆኑም ውጤት ሊያመጣ የሚችል ነው። ሀገሪቱን ለመለወጥ ወሳኙ ሃብት ተደርጎ የመወሰዱ ተገቢነት የሚያጠያይቅ አይደለም።

በሁለተኛው የልማት ዕቅድ የግብርና ዘርፍ በየዓመቱ ቢያንስ በአማካይ የስምንት በመቶ ዕድገት እንዲያስመዘግብ ተደርጎ ውጤት ተገኝቶበታል። ምርጥ ተሞክሮ ያላቸውን አርሶ አደሮች ውጤት ወደ ሌሎች አርሶ አደሮች በማስፋፋት የዋና ዋና ሰብሎችን ምርት በእጥፍ ለማሳደግ እየተሰራ ነው። ከሁለት ዓመት በላይ የሚሆነው የዕቅዱ አፈፃፀም እንደሚያሳየው ከወዲሁ እመርታዎች እየተገኙ ነው።

መንግሥት ለዘመናዊ ግብርና ያልተደፈረውን የአገሪቱን አርሶ አደር የአስተራረስ ዘይቤ የመለወጥን አስፈላጊነት ተገንዝቦ በቀየሰው መስመር የሚታይ ተጨባጭ ለውጥ እየተገኘ ነው። አርሶ አደሩ በድርቅ በቀላሉ መጠቃት ምክንያቱም ደግሞ የዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ አለመኖር እንደሆነ ተረጋግጧል።

በአሁኑ ወቅት አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ኑሮው እንዲሻሻል ተገቢ ትኩረት አግኝቷል። ለዚህም በቂ ማሳያዎችንም ማቅረብ ይቻላል። መንግሥት የዘመናት ቁጭቱን አገራዊ መሠረት ባላቸው አቅጣጫዎች የመፍታት ትግሉን እያካሄደ ነው። አርሶ አደሩ ከራሱ ተርፎ ለገበያ በማምረት ተጠቃሚ የሚሆንበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ፣ ሀገሪቱም ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ ጎዳና ላይ መሆኗን አረጋግጧል።

በአርሶ አደሩ እጅ እንዳለ የሚታሰበው መሬት አነስተኛ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ካለችው መሬት የሚያገኘው ምርት ዝቅተኛ ነው። ይህን መንግሥት በሚገባ በመገንዘቡ ዘርፈ ብዙ የማሻሻል ጥረቶች አድርጓል። በውጤቱም አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮችን ይዞ ለውጥ  ማምጣት አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ መስበር ችሏል።

አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ትኩረት ከመስጠት ይልቅ ለሰፋፊ እርሻዎች ትኩረት መስጠትና ለውጥ ማምጣትን የሚሰብኩ ወገኖች እንዳሉ ግልጽ ነው። እነዚህ ወገኖች የሚሰብኩት በግብርናው ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ትኩረት የመስጠትን አስፈላጊነት የሚሰብክ ነበር። ይህ ደግሞ ሀገራዊና ህዝባዊ ጥቅም የሚመጣበትን ምስጢር ካለመረዳት ወይም ለመረዳት ካለመፈለግ የመጣ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።

መንግሥት አነስተኛ ይዞታ ላላቸው አርሶ አደሮች ምን ያህል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ ገልጿል። ይህን የመንግሥትን ፖሊሲ ትክክለኛነት ለማረጋገጥም ተችሏል። የሚታይና አሳማኝ ውጤት ማምጣትም እንደተቻለም ከአርሶ አደሩ በላይ ምስክር የሚያሻው አይመስለኝም።

ምንም እንኳን ለውጡን የማይፈልጉ ኃይሎች ስህተት ፈላጊ ሆነው ቢቀጥሉም፤ በግብርናው ዘርፍ ባመጣነው ለውጥ ብዙዎች በመስማማት ላይ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግ፣ ለምርቱ ገበያ በማመቻቸትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ትስስር በመፍጠር ምርትና ምርታማነትን አሳድጋ ተጠቃሚ በመሆን ላይ ትገኛለች።

አርሶ አደሩ የለውጥ መስመሩን ተረድቶ በእምነት ወደ ሥራው በመግባቱ በዓመት ሁለቴና ከዚያም በላይ ለማምረት ችሏል። እንዲሁም በከርሰ ምድርና በገጸ -ምድር ያለውን የውኃ ሃብት የመጠቀም ሰፊ ተግባር አከናውኗል።

በውኃ ማሰባሰብና ማቆር፣ የጉድጓድ ውኃን በመጠቀም የወንዝ ውኃን ጠልፎ ጥቅም ላይ በማዋል ብዙ ርቀት ተጉዟል። በመሆኑም አርሶ አደሩ ከራሱ ፍጆታ አልፎ ለከተማው ነዋሪዎች ከፍተኛ ፍላጎት የሆኑትን ምርቶች ማቅረብ ችሏል። ከነዚህ ውስጥ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ናቸው።

ከዝናብ ጥገኝነት በተላቀቁ አመራረት የተገኙትን ምርቶች መጠቀምም እየተቻለ ነው። የመስኖ ልማት ሥራው በበጋ የበቆሎ እሸት ተመጋቢዎች እንዲሆን አስችሎናል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ ሥራው ከሁለት እጥፍ በላይ አድጓል።

ለአርሶ አደሩም በዚያው ልክ ገበያው ተመቻችቷል። አርሶ አደሩ በራሱ ባቋቋማቸው የአርሶ አደሮች የህብረት ሥራ አማካይነት ምርቱን ለገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል። በዚህም ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ ነው።

የግብርናው ዘርፍም በአስተማማኝ ሁኔታ ገበያው ሳያሳስበው ምርትና ምርታማነቱን በማሳደግ ላይ ብቻ አተኩሮ ለልማት ለውጥ ሽግግሩ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥርበት ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ይቻላል። አርሶ አደሩን በማህበር የማደራጀት ሥራ በተናጠል ሊፈቱ ያልቻሉ ችግሮች በጋራ እንዲፈታ አስችሎታል።

መንግሥት ያቋቋመው የምርት ገበያም በተለይ ቡና፣ ሰሊጥ፣ በቆሎና ቦሎቄ በዘመናዊ ግብይት ውስጥ እንዲያልፉ በማድረግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት አረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ አርሶ አደሩ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የማድረግ ጥረት ለምርታማነቱ የላቀ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው።

መንግሥት ባስቀመጣቸው የግብርናው ዘርፍ የልማት ፕሮግራሞች፣ ስትራቴጂዎችና መርሀ ግብሮች በመጠቀም ውጤታማ የሆኑ አርሶ አደሮችን በማበረታታትና በመሸለም በርካታ ውጤታማ አርሶ አደሮችን ለማፍራት ተችሏል። እነዚህ አርሶ አደሮች ለሌሎች ፋና ወጊ በመሆን የዘርፉን ስኬቶች እያጎለበቷቸው ይገኛሉ። ይህም የኢንዱስትሪው ዘርፍ በግብዓት እጥረት እንዳይሰተጓጎል የራሱን ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው።

እንደሚታወቀው ሁሉ የአገራችን ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከነበረት ኋላ ቀር ሁኔታ እየተቀየረ ነው። በተለይም መንግስት በየአካባቢው የገነባቸውና የሚገነባቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዘርፉን እያነቃቁት ይገኛሉ።

የፓርኮቹ ልማት ማንኛውም ሀገር በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካ መስኮች ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ተጠቃሚ ያደርጋል። ልማቱ እንደ ጨርቃጨርቅ በመሳሰሉ ቀላል የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በርካታ የስራ ዕድል የሚፈጠር እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትንም በስፋት መሳብ የሚችል ነው።

ይህም የህዝቦችን ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ፤ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ረገድም የራሱን ሚና ይጫወታል። ከዚህ ጎን ለጎንም የቀላል ማኑፋክቸሪንግ ልማቱን ያፋጥናል፤ ከተሞችን ወደ ላቀ የዕድገት ደረጃ የማሸጋገር ብሎም አዳዲስ ከተሞች እንዲፈጠሩና በዚያኑ ልክም የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ የራሱን አዎንታዊ ሚና ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።

በአገራችን ተፈፃሚ እየሆኑ ያሉት እነዚህ ሁሉ ስኬቶች ምንጫቸው ህዝቡ ነው። የህዝቡ ሰላምና መረጋጋት የፈጠራቸው ናቸው። ይህ ህዝብ በስራ ላይ ሆኖ ዕድገቱን እያሰለጠ መሆኑን የሚያስገነዝቡ ናቸው።

ለሁከትና ለብጥብጥ ጊዜ የሌለው በመሆኑም ከላይ የጠቀስኳቸውን ስኬቶች ተጎናፅፏል። እናም የዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ክርስቲን ላጋርድ አገራችንን ለጉብኝት መምረጣቸው ከእነዚህ ስኬቶች ጀርባ ያላቸው አድናቆት መሆኑ ከማንም ሊሰወር የሚችል ሃቅ አይመስለኝም።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy