Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ይቅርታ ለአገራዊ መግባባት

0 273

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ይቅርታ ለአገራዊ መግባባት

ኢብሳ ነመራ

በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያካሄደውን ግምገማ ተከትሎ አራቱ የግንባሩ አባል ድርጅቶች _ የህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን ሊቃነ መናብርት በሰጡት መግለጫ፣ በፈፀሙት ወንጀል ምክንያት በፍርድ ቤት ቅጣት የተወሰነባቸው ወይም ደግሞ በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች የተሻለ ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በይቅርታ ህግና ህገመንግሥቱ በሚፈቅደው መልኩ ተገቢው ማጣራት በማካሄድ እንዲፈቱ ማድረግ ያስፈልጋል የሚል እምነት መያዙን አሳውቀው ነበር።

በወንጀል ተከሰው ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጦ የተፈረደባቸውና ገና በክስ ሂደት ላይ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ እንዲለቀቁ ሃሳቡን ያቀረበው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ነው። ይሁን እንጂ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ ወንጀለኞችን በይቅርታ የመፍታትና የወንጀል ክሶችን የማቋረጥ ወሳኔ አላሳለፈም። ከዚህ ይልቅ ሃሳቡን ጉዳዩ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ነው ያቀረበው። ይህ የሆነው ወንጀለኞችን በይቅርታ የመፍታትና ክስ የማቋረጥ ጉዳይ የፖለቲካ ወሳኔ ጉዳይ ባለመሆኑ፣ ኢህአዴግ እንደድርጅት ይህን የማደረግ ስልጣን ስለሌለውና ጉዳዩ የመንግስትና የህግ ጉዳይ በመሆኑ ነው። ልብ በሉ ይህን ሃሳብ እነደ ፖለቲካ አቋም ማመንጨት ግን ይችላል።

ይህን ጉዳይ በርካታ የመገናኛ ብዙሃንና አስተያየት ሰጪዎች መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን ሊፈታ ነው በሚል መንፈስ ሲያቀርቡት ተደምጧል። መንግስት የፖለቲካ እስረኞች መኖራቸውን አመነ የሚል ቃና ያለው አስተያየት የሰጡም አሉ። በመሰረቱ የኢህዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይህን ሃሳብ ያቀረበው በሃገሪቱ የፖለቲካ እስረኞች አሉ በሚል መነሻ አይደለም።

በቅድሚያ አንድ ግለሰብ የፖለቲካ ወይም የህሊና እስረኛ ሊባል የሚችለው በያዘው፣ በገለጸወና በሚያራምደው አመለካካት ምክንያት፣ በአመለካካተ በመደራጀቱ ምክንያት ወይም ፍላጎቱንና ተቃውሞውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመግለጽ በመውጣቱና በመሳሰሉት ሰለማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በመሳተፉ ብቻ ሲታሰር ነው።

የሃገራችንን ሁኔታ ስንመለከት በቅድሚያ ከላይ የተገለጹት ፖለቲካዊ ወይም ዴሞክራሲያዊ መብቶችና ነጻነቶች በህገመንግስት ተደንግገዋል። እርግጥ በህገመንግስት መደንገጋቸው በራሱ የመብቶቹን ተግባራዊነት አያረጋግጥም። መንግስት እነዚህን ህገመንግስታዊ መብቶች ሊጥስ የሚችልባቸው ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ። በተጨባጭ በሃገሪቱ ያለውን ሁኔታ ስንመለከት ግን ዜጎች የተቃውሞ አመለካከታቸውን ወይም አቋማቸውን በሚዲያ፣ በስብሰባ፣ መደበኛ ባልሆነ ሁኔታ ወዘተ የመግለጽ መብታቸው መረጋገጡን ማየት ይቻላል። በይፋ በገለጸው የተቃውሞ አመለካከትና አቋም ተይዞ በቁጥጥር ስር የዋለ ወይም አፍ እላፊ ተናግሯል ተብሎ የተከሰሰ ወይም እከሰሳለሁ የሚል ስጋት ያለበት ሰው የለም። በየደረጃው ያሉ የመንግስት ተቋማት በሚጠሯቸው ስብሰባዎች፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚጠሯቸው ስብሰባዎች ላይ የሚነሱ ጠንካራ የተቃውሞ ሃሳቦች፣ ትችቶችና ከገዢው ፓርቲ የተለዩ አቋሞች ለዚህ አስረጂነት ሊጠቀሱ ይችላሉ። ይህን በማድረጉ በቁጥጥር ስር የዋለ ወይም የታሰረ ሰው የለም።

ከ1984 ዓ/ም ጀምሮ ምንም ቅድመ ምርመራ ሳይደረግባቸው እየታተሙ ሲሰራጩ የኖሩ የግል ሚዲያዎች ላይ የሚወጡ የዜጎችና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች አቋሞችና አመለካከቶችም ለዚህ አስረጂነት ሊጠቀሱ ይችላሉ። በሚዲያ በገለጹት አመለካከት ምክንያት ብቻ በቁጥጥር ስር የዋሉ ወይም የተከሰሱና ቅጣት የተላለፈባቸው ዜጎች የሉም። በአመለካካት ወይም በጋራ ፍላጎት ላይ በመመስረት በፖለቲካ ፓርቲነት ወይም በማንኛውም አይነት ማህበር በመደራጀታቸው ምክንያት የታሰሩ፣ የተከሰሱና የተፈረደባቸው ዜጎችም የሉም። በሃገሪቱ ውስጥ እውቅና አግኝተው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሞያና ሃገር በቀል ሲቪል ማህበራትን ለዚህ አስረጂነት መጥቀስ ይቻላል። ህገመንግስቱና ከህገመንግስቱ በመነጩ ህጎችና ማስፈጸሚያ ደንቦች መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በመጠየቃቸውና በማድረጋቸው ብቻ የታሰሩና የተፈረደባቸው ዜጎችም የሉም። በመሆኑም በሃገሪቱ አሁንም የፖለቲካ ወይም የህሊና እስረኞች የሉም።

እርግጥ በተለይ በታችኛው የመንግስት መዋቅር የእርከን ደረጃ ያሉ አንዳንድ ባለስልጣናት በተለይ ራቅ ባሉ ገጠራማ አካባቢዎች ከግንዛቤ እጥረት ሰዎችን በአመለካከታቸውና በተቃውሞ አቋማቸው ምክንያት ብቻ ለአንድ ለሁለት ቀን ያሰሩበት ሁኔታ ሊኖር ይችል ይሆናል። እነዚህም ቢሆኑ ግን ያሰሯቸውን ሰዎች ፍርድ ቤት አቅርበው ማስቀጣት የሚያስችላቸው የህግ አግባብ ስለሌለ ከቀናት በኋላ ከመፈታት ውጭ አማራጭ የላቸውም። ይህ መሆኑ ትክክል ነው ወይም በይቅርታ የሚታለፍ ነው፣ እንደ መብት ጥሰት ሊቆጠር አይችልም አያልኩ እንዳልሆነ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ። እነዚህ ጥፋቶች በሃገሪቱ የዴሞክራሲ አመለካካት ካለመጎልበቱ የመነጩና የስርአቱ ዋና መገለጫ አለመሆናቸው ግን እውነት ነው።

ስራቸው ፖለቲከኛ የሆኑ በተለይ በተቃውሞው ፖለቲካ ጎራ የተሰለፉና በአመራርነት ደረጃ ያሉ፣ ፖለቲካዊ ከሆኑ እንቅስቃሴዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ሰዎች የታሰሩበት፣ ክስ ተመስርቶባቸው በይፋ የፍርድ ሂደት ጥፋተኛ ተብለው ቅጣት የተወሰነበት ሁኔታ ግን አለ። አነዚህ ፖለቲከኞች ወይም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሳተፉ ሰዎች ግን የታሰሩት ከላይ በስፋት የተነሳውን በህገመንግስት የተረጋገጠ ፖለቲካዊ ወይም ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በመጠቀማቸው ሳይሆን፣ በህገመንግስቱና ህገመንግስቱን መሰረት በማድረግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቁ ህጎች ድንጋጌዎችን በመተላለፍ ነው። ህግን መተላለፍ ደግሞ ወንጀል ነው። ፖለቲከኛ መሆን ከህግ በላይ የመሆን መብት አያሰገኝም።

እናም በሃገሪቱ ህግን በመተላላፍ የታሰሩ ወንጀለኞችና የወንጀል ድርጊት ተጠርጣሪዎች እንጂ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀማቸው ብቻ የታሰሩና የተከሰሱ የፖለቲካ/የህሊና እስረኞች የሉም። እርግጥ በሃገሪቱ የፖለቲካ እስረኞች አሉ፣ የፖለቲካ እስረኞች የፈቱ . . . የሚሉ ድምጾች በሃገር ውስጥም ይሁን በውጭ ሃገራት ይሰማሉ። አነዚህ በአብዛኛው የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ትኩረት እነዲያገኙ ለማስቻል የሚደረጉ ናቸው። ህገመንግስታዊ ስርአቱን በተገኘው መንገድ ሁሉ መናድ የሚፈልጉ ቡድኖች ደግሞ የስርአቱን ገጽታ ለማበላሸትና ውዥንብር በመፍጠር በሃገር ውስጥ ተቃውሞ ለመቀስቀስ ዓላማ የሚያደርጉት እንደ ትግል ስልት የተያዘ አካሄድ ነው። እነዚህ ወሬዎች በሃገሪቱ ያለውን ተጨባጭ እውነታ አይወክሉም።

ያም ሆነ ይህ፣ በጽሁፉ መግቢያ ላይ አንደተገለጸው የኢህአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በወንጀል የተፈረደባቸውና በወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው የፖለቲካ ፓርቲ አባላትና ሌሎች ግለሰቦች በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ የሚል ሃሳብ አቅርቧል። መንግስትም ይህ ሃሳብ ተገቢ መሆኑን ሰላመነ ህግ በሚፈቅደው መሰረት ተግባራዊ ማደረግ ጀመሯል። በዚህም መሰረት የፍርድ ሂደታቸው በመታየት ላይ የሚገኙ 528 ተጠርጣሪዎች ክስ እንዲቋረጥ መደረጉን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ሰሞኑን አስታወቀዋል። ክሳቸው እንዲቋረጥ ከተደረገ ተጠርጣሪዎች መሃከል 115ቱ በፌደራል ደረጃ ሲሆኑ፣ ሌሎቹ 413 ደግሞ ከደቡብ ክልል የቀረቡ ናቸው። ሌሎች ክልሎች ክሳቸው ሊቋረጥ ይገባል ብለው ያመኑባቸውን ተጠርጣሪዎች የማጣራት ስራ እንዳጠናቀቁ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጥፋተኝነታቸው በማስረጃ ተረጋግጦ የተፈረደባቸውና በሃገሪቱ የይቅርታ ህግ በሚያዘው መሰረት በማረሚያ ቤት፣ በአቃቤ ህግ አቅራቢነት በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ውሳኔ የሚፈቱትን በተመለከተም በተቀመጡት መስፈርቶች መሰረት እንዲፈቱ ጥያቄ የሚቀርብባቸውን የመለየቱ ስራ መጀመሩን ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አስታውቀዋል። የመለየቱ ስራ ጊዜ እንደሚወስድም አመልክተዋል። በይቅርታ ጥያቄው ውስጥ የሚካተቱት፣ በተፈፀሙ ችግሮች ሰው ያልገደሉና ከባድ የአካል ጉዳት ያላደረሱ፣ ትላልቅ የኢኮኖሚ አውታሮችን በማውደም እንቅስቃሴ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያልነበራቸው፣ ህገመንግስታዊ ሰርዓቱን ለመናድ በተካሄዱ የወንጀል እንቅስቃሴዎች ውስጥ ቁልፍ ሚና ያልነበራቸው፣  መንግስት መስራት ሲገባው ባላከናወናቸው ተግባራት ምክንያት ተገፋፈተው በግጭትና ሁከት ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦች መሆናቸውንም ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አስታውቀዋል። 

እንግዲህ፣ የተመሰረተባቸው የወንጀል ክስ ተቋርጦም ይሁን በፈጸሙት ወንጀል ተፈርዶባቸው በይቅርታ ነጻ ከሚሰናበቱት ግለሰቦች  መሃከል የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ አመራሮችም ጭምር ይገኙበታል። እነዚህ ፖለቲከኞች በይፋ በሚያራምዱት አቋም ደጋፊዎች አላቸው። በፓርቲያቸው ህጋዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ወሳኝ ድርሻ ያላቸውም አሉበት። በመሆኑም አሁን ሃገሪቱ ከገጠማት ችግርና የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት እንዲሁም የሁሉም ዜጎች ድምጽ በመንግስት ውስጥ ሊሰማ የሚችልበትን ሁኔታ ከማመቻቸት አኳያ እነዚሀ ግለሰቦች ወደፖለቲካ ህይወታቸው እንዲመለሱ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ይህ ሁኔታ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ከመደገፍ ጎን ለጎን በሁሉም ዜጎች ዘንድ መተማመንና ሃገራዊ ግባባት ይፈጥራል የሚል እምነትም አሳድሯል። መንግስት በነበረበት የመልካም አሰተዳደርና የፍትህ መጓደል፣ የስራ እድል ፈጠራ ወዘተ ባደረባቸው ቅሬታ በህግ የተከለከለ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሳተፉ ዜጎችን መፍታትም በተመሳሳይ ከሞራልም ከፍትህም አንጻር ተገቢ ነው። ሃገራዊ መግባበቱንም ያጎለብታል።

በአጠቃላይ፣ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ክስ የማቋረጡና የፍርደኞችንም ቅጣት በይቅርታ የማንሳቱ ዓላማ የሁሉምዬጎች ድምጾች የሚሰሙበትንና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቀሴ ተሟሙቆ አማራጮች የሚሰፉበትን ሁኔታ በመፍጠር የሃገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር ማስፋት ነው። ይህ ሁኔታ ሃገራዊ መግባባትን የማጎልበት፤ እነዲሁም አሁን የተፈጠረውን ያለመተማመንና የስጋት መንፈስ የማርገብ አቅም ይኖረዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy