Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከውጤታማነት ባሻገር

0 208

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከውጤታማነት ባሻገር

ዳዊት ምትኩ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬታማ የሆነ መንግስታዊ ተቋም ነው። አየር መንገዱ አሁን ለሚገኝበት ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ የበቃው መንግስት በሚያደርገው ሁለንተናዊ ድጋፍና አመራር እንዲሁም በአገሪቱ የተፈጠረው አስተማመኝ ሰላም ብሎም ፈጣንና ተከታታይነት ያለው ልማት በመኖሩ ነው።

አየር መንገዱ በአቪየሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንግሥት ንብረት ቢሆንም፤ እስካሁን ድረስ ቀጣይነት ያለው ዕድገት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል። ይህም መንግስትን በሁሉም ዘርፎች እየሰጠ ያለው ጠንካራ አመራር ማሳያ ይመስለኛል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጥንካሬ የሚያሳይ አንድ ምሳሌ ላንሳ። አየር መንገዱ በቅርቡ ከአፍሪካ ቀዳሚው አየር መንገድ መሆኑ ተገልጿል። እንደሚታወቀው ሁሉ የዛምቢያ መንግስት በቅርቡ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት በመፍጠር የአገሪቷን አየር መንገድ እንደገና አዋቅሯል። እንደ አዲስ በተዋቀረው የዛምቢያ አየር መንገድም ኢትዮጵያ 45 በመቶ ድርሻ መውሰዷን መረጃዎች ይጠቁማሉ። የህም አየር መንገዱ ምን ያህል ጥንካሬ ያለው መሆኑን የሚያሳይ ነው።

የጋና መንግስት በምዕራብ አፍሪካ አገራት በአዲስ መልክ ለመጀመር ላቀደው የበረራ አገልግሎት በአጋርነት አብረውት እንዲሰሩ ከመረጣቸው ሶስት አየር መንገዶች መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንዱ መሆኑን የአገሪቱ አቪየሽን ሚንስትር ሲሲሊያ ዳፓህ ሰሞኑን መግለፃቸውን እናስታውሳለን። ይህም ሌላኛው የአየር መንገዳችንን ጥንካሬ የሚያሳይ ክስተት ይመስለኛል።

አሁን ባለው መረጃ የአፍሪካዊያን አየር መንገዶች ከ10 ዓመት በፊት በአህጉሪቱ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ላይ የ40 በመቶ ድርሻ የነበራቸው ቢሆንም፤ አሁን ላይ በአውሮፓዊያንና ገልፍ አገራት አየር መንገዶች ተጽዕኖ ምክንያት ድርሻቸው ወደ 20 በመቶ ዝቅ ብሏል።

ታዲያ ይህን ችግር ለመቅረፍ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ነው። በተለይ በናይጀሪያ የንብረት አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሚመራው ግዙፍ የግል አየር መንገድ ለሰራተኞቹ ደመወዝ መክፈል ተስኖት ከአገልግሎት ውጭ ለመሆን እየተቃረበ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አየር መንገዱን ለማስተዳደር ያቀረበው ጥያቄ የናይጄሪያ መንግስት የማስተዳደሩን ሃላፊነት አየር መንገዳችን እንዲወጣ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። ይህም አየር መንገዱ ምን ያህል ጠንካራ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

የእነዚህ ተግባሮች ማሰሪያ ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ አገራችን ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እየገነባች ያለችው መንግስት በሁሉም መስኮች የሚከተላቸው ትክክለኛ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲሁም እነርሱን ተከትሎ የሚሰጠው ቀጥተኛ አመራር መሆኑ ነው። ይህም በሁኩም መስኮች የስኬቶቻችን መሰረት ሆኗል።

የኢፌዴሪ መንግስት በህገ መንግስቱ ላይ የተቀመጡት የልማት ዓላማዎች እንዲሳኩ ላለፉት 26 ዓመታት ቀጥተኛ አመራር ሲሰጥ ቆይቷል። ይህንን ዓላማ ለማረጋገጥ መንግሥት ዜጎች በአገሪቱ የሚገኘውን ሀብት በፍትሃዊነት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሠራር ቀይሶ ተፈጻሚ እያደረገ ይገኛል።

ዛሬ በልማት ወደ ኋላ የቀሩ ክልሎች በመንግሥት ልዩ እገዛ ተደርጐላቸው ጭምር የልማቱ ተጠቃሚነታቸው እየተረጋገጠ መጥቷል። ህገ መንግሥቱም በግልጽ ለነዚህ መብቶች ዋስትና ሰጥቷል። መንግሥት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብቶችን በሕዝብ ስም በይዞታው ሥር በማድረግ ለዜጎች የጋራ ጥቅምና ዕድገት የማዋል ኃላፊነቱንም እየተወጣ ነው።

ዛሬ በኢትዮጵያ ሁሉም ዜጋ በማንኛውም የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ውስጥ የመሰማራትና ለመተዳደሪያው የመረጠውን ሥራ የመከወን መብት አለው። ሁሉም ዜጋ በመንግሥት ገንዘብ በሚካሄዱ ማህበራዊ አገልግሎቶች በእኩልነት የመጠቀም መብቱ ተረጋግጦለታል።

እነዚህን መብቶች ለማረጋገጥ መንግስት ቀጥተኛ አመራር እየሰጠ አገሪቱ በልማት ጎዳና እንድትራመድ ማድረግ ተችሏል። ለልማቷ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ጭምር ቀጥተኛ አመራር እየሰጠ የሚገኘው መንግስት ለዕድገታችን አንድም ስንዝር ቢሆን ዋጋ ያለውን ማናቸውንም የልማት ክንዋነኔዎችን እያከናወነ ይገኛል።

መንግስት በሚሰጠው ቀጥተኛ አመራር ኢትዮጵያዊያን በሁሉም ዘርፎች በርካታ ድሎችን ጨብጠዋል። የድል ፍሬዎቹንም ማጣጣም ይዘዋል፡፡ ሕይወታቸው ተለውጧል። ከዚህ ማዕድ ላይ የሚያፈናቅላቸውን በዋዛ ያልፉታል ተብሎ አይጠበቅም።

በህገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች መሠረት ሕዝቦች የኑሮ ሁኔታቸው የመሻሻልና የማያቋርጥ ዕድገት የማግኘት መብት እንዳላቸው በተግባር እየታየ መጥቷል፡፡ በብሔራዊ ልማት የመሳተፍ፣ በሚቀረፁ ፖሊሲዎችና ኘሮጀክቶች ላይ አስተያየት የመስጠት መብት ዜጎች እንዲሳተፉ ማድረግ ተችሏል።  

የልማት እንቅስቃሴው ዋና ዓላማም የዜጐችን ዕድገትና መሠረታዊ ፍላጐቶችን ማሟላት በመሆኑ መንግሥት የሚያወጣቸው ፖሊሲዎችና የሚያደርጋቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የአገሪቱን ሕዝቦች ተጠቃሚነት መብት የሚያስከብሩ በመሆናቸው ተጠቃሚነታችን እየጎለበተ ነው።

የፌዴራል መንግሥት ፍትሃዊ የልማት እንቅስቃሴ ከማረጋገጥ በተጨማሪ በልማት ወደ ኋላ የቀሩ ሕዝቦች መላ አቅማቸውን አሟጠው እንዲጠቀሙ ለማስቻል ልዩ ድጋፍ እየሰጣቸው ይገኛል።

የህገ መንግሥቱ ምጣኔ ሀብታዊና ማህበራዊ ድንጋጌዎች ተጠቃለው ሲታዩ በነጻ ፍላጐት፣ በህግ የበላይነት፣ በእኩልነት፣ በጋራ ጥቅምና በራስ ፈቃድ ላይ የተመሠረተ አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ በጋራ የመገንባት ወሣኝነትን ያላቸው በመሆናቸው ይህን ለመተግበር መንግሰት ረጅም ርቀት ተጉዟል። በሚሰጠው አመራርም ሁሉም በየደረጃው ተጠቃሚ እየሆነ ነው።

በዚህም ዜጐች ንብረት የማፍራት፣ በመረጡት የሥራ መስክ የመሰማራት መብቶች በማረጋገጥ በነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ሥርዓት የሚመራ ፈጣንና ፍትሀዊ ልማት ማምጣት የቻለ መንግስት ነው።

ይህን አመራር የሚሰጠው መንግስት የሕዝቦችን ልማታዊ አቅም በማሳደግ ለአገር ግንባታ ወሣኝ ሚና እየበረከተ ነው። የዜጐችን የልማት ባለቤትነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የልማት እንቅስቃሴዎችንም እያሳለጠ ይገኛል። የኢትዮጰያ አየር መንገድ የዚህ ተግባሩ አንድ ማሳያ ነው። እዚህ ሀገር ውስጥ እየተካሄደ ያለው ልማት፣ የተፈጠረው አስተማማኝ ሰላምና ሁለንተናዊ ለውጦች ለአየር መንገዱ ውጤታማነት ምክንያቶች ናቸው። ነገም በሀገራችን ውስጥ ያለው እነዚህ ሁኔታዎች ተጠናክረው እስከቀጠሉ ድረስ አየር መንገዳችን ይበልጥ ውጤታማ የማይሆንበት ምክንያት የለም።  

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy