Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዕለተ-ናይል

0 654

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ዕለተ-ናይል

ዳዊት ምትኩ

የካቲት 15 ቀን 2010 ዓ.ም በመዲናችን የናይል ቀን በምስራቅ አፍሪካ አገራት አማካኝነት ለ12ኛ ጊዜ ተከብሯል። ዕለተ-ናይል የታሰበው በእግር ጉዞ ነው። በዕለቱ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ያደረጉትን ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የናይል ተፋሰስ አገራት ከናይል ወንዝ ለመጠቀም ይበልጥ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል። የኢንቴቤው ስምምነት ሁሉንም የተፋሰሱን አገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ፤ ስምምነቱን ያልፈረሙና በፓርላማቸው ያላፀደቁ የተፋሰሱ አገራት ስምምነቱን በመፈረም ለጋራ ተጠቃሚነት መትጋት አለባቸው።

እንደሚታወቀው ሁሉ የናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያን፣ ብሩንዲን፣ሩዋንዳን፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን፣ ኡጋንዳን፣ ግብፅን፣ ሱዳንን፣ ደቡብ ሱዳንን ኬኒያን፣ ታንዛኒያን በአባልነት ያቀፈ ነው። የናይል ተፋሰስ ትብብር ሲቋቋም ካሉት በርካታ አላማዎች መካከል አንደኛው የናይልን ውሃ የተፋሰሱ አባል ሀገራት ፍትሃዊ በሆነ ክፍፍል እንዲጠቀሙ ማድረግ ነው። ይህንን ጉዳይ እውን እንዲሆን በማድረጉ ረገድ የተፋሰሱ አባል ሀገራት ዓመታትን የፈጀ ውይይቶችንና ድርድሮችን ማድረግ ግድ ብሏቸዋል።

አስር ዓመታት ከፈጁ ድርድሮች በኋላ የመጨረሻ እ.ኤ.አ በ2010 መግባባት ላይ ተደርሶ ሀገራቱ የጋራ ትብብር ሰነድን መፈረሚያው ጫፍ ላይ ሲደርሱ ግብፅና ሱዳን ራሳቸውን አገለሉ። በጊዜው ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት በሰነዱ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል። በቅኝ ግዛት ዘመን እ.ኤ.አ ግብፅና እንግሊዝ በደረሱበት ስምምነት መሰረት በእንግሊዝ ቅኝ ሥር የነበሩ ሀገራት የናይል ውሃን ለመጠቀም የግድ የግብፅን ፈቃድ መጠየቅ ይጠበቅባቸው ነበር።

እርግጥ የጋራ ትብብሩ ከስምምነቱ እውን መሆን በኋላ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል። ከሰራቸው ሥራዎች መካከልም ሀገራት ወንዙን በጋራ በመጠቀሙ ረገድ የጋራ ድንበር ተሻጋሪነት ጥቅም ያላቸው ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ አደርጓል። የጋራ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት እንዲኖር እንደዚሁም የተፋሰሱን ሀገራት ውሃውን በአግባቡ የመጠቀም አቅም መገንባቱ ላይም ሥራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል። እ.ኤ.አ ከ1999 በፊት ግን የተፋሰሱ ሀገራት በናይል ዙሪያ የሚወያዩበት ምንም አይነት የጋራ መድረክ አልነበራቸውም። ዛሬ ይህ ተቀይሮ ዕለተ-ናይልን እስከ ማክበር ደርሰዋል።

እርግጥ ኢትዮጵያ በመገንባት ላይ የምትገኘው የህዳሴ ግድብ የቀጣናውን አገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ የናይልን ውሃ በጋራ ተጠቃሚነት መመልከቱ ለሀገራቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ከዚህ ቀጣናዊና የተፋሰሱ ሀገራት ተጠቃሚነትና በኢኮኖሚ የማስተሳሰር ፍላጎቷ በመነሳትም ሀገራችን ለዘመናት ተገድቦ የቆየውን ሀገሪቱ በተፈጥሯዊ ውኃ ሃብቷ የመጠቀም መብቷን አሳልፋ ልትሰጥ አትችልም። እናም የራሷን ፕሮጀክት በራሷ አቅም በመገንባት ላይ ያለች እንዲሁም ከድህነት ለመውጣት ስትል የምትገነባቸውን ማናቸውንም የልማት ግድቦችን ለአፍታም ቢሆን የማታቆም መሆኗን መገንዘብ ይገባል። ብሔራዊ ጥቅሟን ለማንም አሳልፋ የማትሰጥ መሆኑንም ጭምር መረዳት ያስፈልጋል።

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ ነፃነቷንና ሉዓላዊነቷን ለድርድር አቅርባ የማታውቅ የጥቁር ህዝቦች መኩሪያ ሀገር ናት። ከባርነት፣ ከጭቆና እና ከቅኝ ተገዢነት ለመላቀቅ ብርቱ ትግል ላደረጉ በርካታ የዓለማችን ህዝቦች አርአያና ምሳሌያቸው እስከ መሆንም ደርሳለች።

ዛሬ የሀገራችን ህዝቦች የራሳቸውና የቀጣናው ሀገራት ድህነት፣ ኋላቀርነት፣ ረሃብና ጦርነት ማብቃት አለበት ብለው ቆርጠዋል። ‘ዋነኛው ጠላታችን ማነው?’ ብለው ጠይቀው “ድህነት” የሚለውን ትክክለኛ ምላሽም አግኝተዋል።

ጎረቤቶቻቸውን፣ በተለይም የተፋሰሱን ሀገራት ተጠቃሚ ለማድረግ በእኩልና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተ የግንኙነት ፖሊሲን ቀርፀውም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ‘ድህነትንም እንዴት እናስወግዳለን?’ ብለው መክረው መፍትሔ ካበጁም ቆይተዋል።

በሁሉም መስክ ፈጣን ልማትን ሊያመጡላቸው የሚችሉ አቅጣጫዎችን መከተል ብቸኛ አማራጫቸውን ከማውጣትም ባሻገር፤ በትግበራ ሂደቱ ላይ የጋራ መግባባትን እየፈጠሩ ነው። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ይህን መግባባታቸውን በጠነከረ መሰረት ላይ ያኖረ ነው ማለት ይቻላል። የህዳሴው ግድብ ግንባታ መላው ኢትዮጵያዊ አሻራ ያረፈበት ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ግድቡን የደገፈው በሞራል ብቻ አይደለም። በጉልብቱም፣ በዕውቀቱም፣ በገንዘቡም በፀሎቱም ጭምር ነው።

እንደ እውነቱ ከሆነ የሰው ስጋና ደም ለግንባታው የሚያገለግል ቢሆን ኖሮ፤ ይህን በመከወን ግድቡን ለማሳለጥ የተዘጋጁ እልፍ ናቸው ብል እንደ ማጋነን የሚቆጠርብኝ አይመስለኝም። የህዳሴው ግድብ ግንባታ አንድነታችንን ይበልጥ ያጠበቀ ነው። መቻልን የቻልንበት፣ አንድ ከሆንንና ከተባበርን የማንወጣው ፈተና አለመኖሩን ያየንበትም ይሁን ያሳየንበት ጭምር ነው፤ ለወዳጆቻችንም ይሁን ለጠላቶቻችንም።  

የናይል ተፋሰስ የትብብር ስምምነት ማዕቀፍ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ከ7 ነጥብ 10 ቢሊዮን ኪዮቢክ ሜትር ተጨማሪ ውሃን ማስገኘት እንደሚችል ጥናቶች አረጋግጠዋል። ሁሉንም ነገር በጥርጣሬ የሚመለከቱት አንዳንድ የውጭ ፖለቲከኞች የ“ይጎዳናል” ያረጀ አስተሳሰብን በማራመድ ጉዳዩን የፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረጉት ነው፡፡ ይህ ግን ተቀባይነት የለውም።

የአባይ ተፋሰስ ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የኢንቴቤው ስምምነት ከዳር ለማድረስ አስር ዓመታት መፍጀቱ ምን ያህል ጥረት እንደጠየቀ ለመረዳት የሚያዳግት አይደለም፡፡ ምክንያቱም በአባይ ተፋሰስ የጋራ ተጠቃሚነት ዙሪያ የነበረው አስተሳሰብን መቀየሩ ብቻ የሚጠይቀውን ጥረት መገመት ስለማይከብድ ነው፡፡

አገራችን ከዚህ የተፋሰሱን ሀገራት ተጠቃሚነትና በኢኮኖሚ የማስተሳሰር ፍላጎቷ በመነሳትም ለዘመናት ተገድቦ የቆየውን ሀገሪቱ በተፈጥሯዊ ውኃ ሃብቷ የመጠቀም መብቷን አሳልፋ ልትሰጥ አትችልም።

በመሆኑም የራሷን ፕሮጀክት በራሷ አቅም በመገንባት ላይ ያለች እንዲሁም ከድህነት ለመውጣት ስትል የምትገነባቸውን ማናቸውንም የልማት ግድቦችን ለአፍታም ቢሆን የማታቆም መሆኗን መገንዘብ ይገባል።

አብዛኛዎቹ የተፋሰሱ አገራት ስምምነታቸውን የገለፁበት የኢንቴቤው ስምምነት የቀኝ ገዥዎችን ስምምነት የሻረ ነው። ይሁንና ሀገራት በውሃው አጠቃቀም ዙሪያ መተማመን መፍጠር ይችሉ ዘንድ ያለውን የመረጃ ክፍተት የመሙላት ሥራ እየተከናወነ ነው። ዕለተ ናይል ሲከበር በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፤ በተፋሰሱ ሀገራት መካከል ግጭቶች ቢነሱ የትብብሩ ሚና ምን ሊሆን ይችላል? የሚለው አንዱ ነው። ትብብሩ ወደ ኮሚሽንነት ካላደገ በስተቀር በአባል ሀገራት መካከል ለሚነሱ አለመግባባቶች የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ተጠቅሞ መፍትሄ ለመስጠት አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችልም በወቅቱ ተገልጿል። ይሁንና ዕለተ-ናይል በተፋሰሱ አገራት በተለይም በታችኛዎቹ የተፋሰሱ አገራት መተማመንን በመፍጠር ወደ ኢኒሼቲቩ እንዲቀላቀሉ ማድረግ ያስፈልጋል። ካልሆነ ግን በአብዛኛው የተፋሰሱ አገራት የተፈረመው የኢንቴቤው ሰነድ ገዥ ሆኖ ይቀጥላል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy